Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 8 እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ • 99

ባለፈው ክፍለ ጊዜ (እኛ የምንዋጋው ጠላት) በሚለው ትምህርት ውስጥ የጠላትን ባሕርያት ተምረሃል። በዚህ በክፍል ውስጥ እግዚአብሔር መልካሙን የእምነት ገድላችንን እንድንዋጋ የሰጠንን “የእግዚአብሄርን የጦር ዕቃ ሁሉ” በእምነት እንዴት መጠቀም እንዳለብን ትማራለህ። የክርስቲያን ሕይወት እውነተኛ ተፈጥሮ ጦርነት ነው ይህም ከሰዎች ጋር ሳይሆን እኛ የክርስቶስ ስለሆንን የእኛን ስራ ከሚቃወሙት መንፈሳዊ ኃይላት ጋር ነው። ጠላት የማያቋርጥ መሆኑን ፈጽሞ ልንደነቅበት አይገባም፤ የእሱ ጥቃትም ጨካኝና የማያቋርጥ ነው። እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ውጊያ እንድንጠቀምበት የተሟላ የጦር መሳሪያን ሰጥቶናል። እየተጋደልንበት ያለነው ውጊያ እምነታችንን እንድናቆም ለማድረግ፣ ለክርስቶስ ያለንን መሰጠት በመተው በዓለማዊነትና በጥፋት በመተካት እንድንኖር ከሚዋጉ መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የጠላት ውሸትን እንደ ሚያቃጠሉ ሚሳይሎች፣የክፉው ፍላጻዎች በእምነት ጋሻ ብቻ ሊጠፋ የሚችል እንደሆነ አድርጎ በስዕላዊ መንገድ እድርጎ ያቀርበዋል። በእግዚአብሄር አምላክ ላይ ያለን እምነት “ከክፉው” ማለትም ከሰይጣን ከሚያድነን ጋሻ ሆኖ ተገልጿል። ኢየሱስ ጌታችን ነው፤ በመስቀል በኩል እና ከሞት መነሣቱን ጠላትን በታላቅ ድል ያሸነፈ. መለኮታዊ ተዋጊ ነው። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቁ ድል ውስጥ አሸናፊዎች ሆነናል፣ ክሪስተስ ቪክቶር፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ። ስለዚህ አማኞች መንፈሳዊ ተዋጊዎች፣ የክርስቶስ ወታደሮች፣ ከጠላት ጋር በሚደረገው ሃሰትን በመዋጋት ውጊያ ውስጥ ምን እንደተከሰተ የሚያውቁት ጀግኖች ናቸው። ጠላት ለመዋጋት፣ እኛ በምናደርገው ሁሉ ክርስቶስን በማክበር እንድንወክለው አቋም መውደድ አለብን፤ እናም በፍጹም በሆነ እምነትን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባትነት ላይ በመደገፍ በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ሁሉን ፈጽመን መቆም አለብን። በእሱ አማካኝነት ጠላት በእኛ ላይ የሚያደርገውን ማንኛውንም ነገር መቋቋም እንችላለን። የዲያቢል በጣም የተለመደው ዘዴ እኛን መዋሸት ነው፤ የእኛ ታላቁ የጦር መሣሪያ ደግሞ እውነትን መቀበል እና ውሸት ማመንን ማቆም እንዲሁም እኛን ለማሸነፍ በምንፈተንባቸው ውሸቶች ላይ ነቅቶ መኖር ነው። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ በመሠረታዊ እውነትነት በእግዚአብሔር ወደ ክርስቶስ እውነት ያገናኘናል። ለዚህም ነው ስለ ተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማር ያለብን ምክኒያቱም በቋሚ ልምምድ በጠላት ላይ በተሳካ ሁኔታ ልንጠቀማቸው እንችላለን። የበለጠ ስንሳተፍ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወታደሮች በተሻለ እንዋጋለን።

ይዘት

ሰይጣንም ወደ አትክልት ስፍራ መጣና ለአዳምና ለሔዋን አንሾካሾክ ነበር- እናም በእነርሱ ውስጥ ለሁላችንም - “የእግዚአብሔርን ልብ ልታምኑት አይገባም. . . እሱ በእጁ ይዞባችኋል ... ነገሮችን በእናንት ቁጥጥር ስር ማደረግ ይጠበቅባቸኋል። “

~ John Eldredge. Epic: The Story God Is Telling. Nashville: Thomas Nelson, Inc., 2004, p. 55.

Made with FlippingBook - Online magazine maker