Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
100 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ ትምህርት 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን አጠር ያለ መልስ ይስጡ። 1. በዓለም ውስጥ ስንኖር በዓለም ደረጃ መመዘኛዎች መንፈሳዊ ጦርነትን አንዋጋም ምክኒያቱም የጦር መሣሪያዎቻችን በመንፈሳዊ ውጊያዎች ውጤታማ እንድንሆን ከሚያሠለጥነን ከእግዚአብሔር ነውና። 2 ቆሮ 10፡3-5 ያንብቡ እና በመንፈሳዊ ውጊያ ስለምንጠቀማቸው የጦር መሳሪያዎችን በተመለከተ ባዶ ቦታዎችን ይሙሉ።
ሀ. እግዚአብሔር የሰጠን የጦር መሣሪያዎቻችን ____________ አይደለም።
ለ. እነዚህ መለኮታዊ መሣሪያዎች ______________ ለማጥፋት መለኮታዊ ኃይል አላቸው።
ሐ. በእነዚህ መሳሪያዎች አማካኝነት ________________________ እና በእግዚአብሔር እውቀት ሁሉ ላይ የሚነሳውን __________________________________ እናፈርሳለን።
መ. የጦር መሣሪያዎቻችን መጠቀማችን __________________________________________________________ __________________________ያስችለናል።
2. እግዚአብሔር አማኞችን በማስፈራራት እና በመጉዳት ውሸትን የሚጠቀመው የጠላት የዲያቢሎስ መርሃግብሮቻችን እና ስልቶችን ለመቃወምና ሁሉን ፈጽመው ለመቆም እንዲቸሉ ተገቢውን የጦር መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል። የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ከትክክለኛው ገለጻቸው ጋር አዛምዱ
ሀ. ሮሜ 13፡11-12 ___ የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃዎች ጠላትን ለመግጠም እንድንቆም ይረዱናል
ለ. ኤፌ. 6፡11-12
___ የጨለማውን ሥራ አስወግዳችሁ የብርሃንን ትጥቅ ታጠቁ
ሐ. 1ተሰ. 5፡8
___ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር እንዲሁም የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እንልበስ።
3. አማኞች በውጊያ ውስጥ ያሉት ከዲአቢሎስ ጋር ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ “ዓለም” እና “ሥጋ” (የእራሳቸው ኃጢአተ ባህሪያት) ከሚለው ጋርም ጭምር ነው። ሰይጣን በዚህ ዓለም ሥርዓት በመጠቀም በውጭ በኩል አማኞችን ያጠቃል እንዲሁም በውስጣቸው ደግሞ አማኞች ለኃጢአታቸው ዝንባሌዎቻቸው እንዲሰጡ በማድረግ ይፈትናቸዋል። ከዚህ በታች ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከትክክለኛው ትርጓሜዎ ጋር ያዛምዱ፡
ሀ. ያዕቆብ 4፡4
___ ጠላት ለክርስቶስ መሰጠታችንን ለማዳከም ይፈልጋል
ለ. ይሁዳ 3-4
___ የዓለም ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው
Made with FlippingBook - Online magazine maker