Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
102 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
6. መንፈሳዊው ወታደር የእግዚአብሔርን ጋሻ መያዝ አለበት እንዲሁም እርሱን ከመከተል ከሚያግዱ ማናቸውም ነገሮች ራሱን ወየም ራሷን ማጽዳት ይኖርባቸዋል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6 ፡ 11-16ን አንብብ። መልካሙን የእምነት ገድል ለመጋደል ምን ክትትል ማድረግ ይኖርብሃል?
7. ኃጢአት በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ውጤታማነታችንን የሚያደናቅፍ ከመሆኑም በላይ ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርገን ይችላል። ሆኖም ኃጢአትን ብናደርግ በእግዚአብሔር አብ ፊት የሚወክለን ጠበቃ አለን። 1ዮሐንስ 2፡1-2 ያንብቡ። ኃጢአት ከሠራን ስለእኛ ሆኖ መከላከያ የሚያቀርብልን ጠበቃችን ማን ነው?
8. ከኃጢአት ጋር የምናደርገው ውጊያ የቱንም ያህል አስቸጋሪና ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፍቅር በመጨረሻው ድል ማድረግ እንደምንችል ዋስትና ይሰጠናል። ሮም 8፡ 28-39ን አንብብ። ባዶዎቹን ሙላ:
ሀ. እግዚአብሔርንም ___________________ እንደ _______________________ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን (ቁ. 28) ።
ለ. እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን _________________________ ይችላል? (ቁጥር 31)።
ሐ. ከክርስቶስ ________________ ማን ሊለየን ይችላል? (ቁ .35).
መ. በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ውስጥ በወደደን በእርሱ ከ___________________________ እንበልጣለን (ከቁ 37)።
ሠ. በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የማይችሉትን ነገሮች ሁሉ ይዘርዝሩ (ቁ .38-39)
9. የመንፈስ ሰይፍ የእግዚያብሄር ቃል ነው ፤ እኛን በክርስቶስ ባለን ጥሪ በብቃት ለማዘጋጀት እና ውጤታማ ሆነን ለመፅናት እና ለማፅናት እግዚአብሄር እስትንፋሱን እፍ ያለበትን (መነዳት ያለበትን) ቃሉን ሰጥቶናል። 2 ጢሞ 3፡16-17ን አንብብ። ለመልካም ሥራ ሁሉ እኛን ለማስታጠቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቀምባቸውን ሦስት ነገሮች ዘርዝሩ
10. በመንፈሳዊ ውጊያ ውጤታማ ለመሆን በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ፍሬያማና የሚያደርጉንን እግዚአብሔርን የመምሰል ባሕርያትን በእምነታችን ላይ መጨመር አለብን። 2ኛ ጴጥ 1፡3-11ን አንብብ እና የሚከተሉትን ይመልሱ
ሀ. መለኮታዊ ኃይሉ ምን ይሰጠናል? (ቁጥር 3)
ለ. ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ስለሰጠን ምን እንካፈላለን? (ቁ 4)
ሐ. በእምነታችን ላይ በጎነትን ከጨመርን በኋላ ሌላ ምን መጨመር አለብን? (ቁ 5-7)
Made with FlippingBook - Online magazine maker