Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 8 እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ • 103
መ. በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳንሆን ምን ማደረግ አለብን? (ቁጥር 8)
ሠ. እነዚህን ባሕርያት ባላሟላ ሰው ውስጥ ያለው ምንድን ነው? (ቁጥር 9)
በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን እያንዳንዱ አማኝ ከዓለም፣ ከሥጋ እና ከሰይጣን ጋር ይዋጋል። ይህ በሰዎች ላይ ወይም በስጋዊ አካል ያለ አካላዊ ውጊያ አይደለም፤ ነገር ግን ውሸትን እና ማታለልን በመጠቀም ሊያታልሉ፣ ሊያዛቡ እና ሊያጠፉ ከሚሞክሩ የክፋት ኃይላት ጋር ነው። ዲያቢሎስ ልክ እንደ የሚያገሳ አንበሳ የሚውጠውን ሰው ይፈልገዋል (1 ጴጥ .5.8-9)፤ እናም የእርሱን ዕቅድ እና መሳሪያዎች እናውቅ ዘንድ ንቁዎች በአእምሯችን እና በልባችን ላይ የታጠቅን መሆን አለብን። እርሱ የሚሰነዘረው ጥቃቱ የማያወላውል እና የማያቋርጥ ሊሆን ይችላል። በጦርነት ቀን ጠላቶቻችንን ለመቋቋም እንድንችል እና እኛን በመንፈሳዊ ውጊያ ለማስታጠቅ የሚያስችለንን ሰማያዊ የጦር ዕቃ ማለትም “የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ሁሉ “ ሰጥቶናል። የጠላት የጦር መሳሪያ ምርጫዎች ደግሞ ውሸት ነው፤ ያም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሚንበለበሉ የክፉ ፍላጾች ብሎ የገለጸው ነው እሱም በእምነት ጋሻ (የእግዙአብሔር የጦር ከሆኑት አንደኛው) ብቻ ሊጠፋ የሚችል ነው። በተጨማሪም የእውነት መታጠቂያን፣ የጽድቅን ጥሩርን፣ የሰላም ወንጌልን ጫማ፣ የመዳንን ራስ ቁር እና የመንፈስ ሰይፍ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ተስጥቶናል። በዚህ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ስትሳተፉ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፤ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ መልካም ወታደር ሆናችሁ መከራና እና ስቃይን ተካፈሉ። ምንም ዓይነት ወታደር በጦር ሰራዊት እያለ የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን የዕለት ተዕለት ጉዳዮች ላይ አያጠላልፍም (2 ጢሞ 2፡3-4)። ቋሚ የሆኑ የጠላት የማጥቂያ ስልቶች ውሸት፣ ውንጀላ፣ ክስ፣ ውግዘት እና አሉታዊነት ናቸው። ለመዋጋት መማር ጽኑ መሆንን፣ ዲሲፕሊን መሆንን እና ታማኝ መሆንን መማርን ያካትታል።. ከጠላት ውሸቶች ጋር በሚያደርጉት ውጊያ የእግዚአብሔርን የጦር ሁሉ በቋሚነትና ይበልጥ በተጠቀላችሁ መጠን በእርሱ ላይ ድልን የበለጠ ትቀዳጃላችሁ። ታገሱ እናም ጌታ ጠብቁ።
ማጠቃለያ
ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ነገሮች ማጥናትና ማሰላሰል የሚረዱ ተጨማሪ መግለጫዎች የሚከተሉት ናቸው
ተጨማሪ መግላጫዎች
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር እንዴት እንደሚጀምር (ተጨማሪ ማ. 3) መጽሐፍ ቅዱስን በከፊል እና በሙሉ መረዳት (ተጨማሪ ማ. 13) የመጽሐፍ ቅዱስ መጻህፍት አጭር መግለጫ (ተጨማሪ ማ. 17) የአዲስ ኪዳን የዘመን ቅደም ተከተል ሰንጠረዥ (ተጨማሪ ማ. 18) መሲሁን ለሌሎች ማስተላለፍ-የወንጌላት ግንኙነት (ተጨማሪ ማ. 19) እግዚአብሔር ይነሣ! የጌታን መሻት እና የእርሱን ምህረትን መፈለጊያ ሰባት “ሀ”ዎች (ተጨማሪ ማ. 23)
Made with FlippingBook - Online magazine maker