Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
104 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
የክርስትና ሕይወት እውነተኛ ችግር የሚጀምረው በየማለዳው ከእንቅልፍዎ በሚነሱበት ወቀት ነው። ለዕለቱ ያልዎት ምኞትዎ ሁሉ እና ተስፋዎ እንደ ዱር አውሬዎች በፍጥነት ወደ እርስዎ ይሮጣሉ። እናም በየማለዳው የርሶ ተግባር ሁሉንም ወደ ኋላ መገልበጥን፣ ሌላውን ድምጽ ማዳመጥን፣ ሌሎች እይታዎችን መመልከትን፣ ሌላውን ትልቁን፣ ጠንካራውን እና ጸጥታ የሰፈነበትን መፍቀድን ይጠይቃል። ቀኑን በሙሉ እንደዚህ ይቀጥላል። ለጊዜው አንዳንድ ጊዜ ብቻ ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜያት በኋል አዲሱ ህይወት በህይወት ስርአታችን ውስጥ ይሠራጫል፤ ምክንያቱም እኛ አሁን በትክክለኛው መንገድ እርሱ በእኛ ክፍል ውስጥ እንዲሠራ ፈቅደንለታልና ነው። በንድፍ ላይ እንዳል ልዩነት ነው ይህም ውጫዊ ክፍል ላይ ብቻ የተቀመጠው እና በቀስታ እና በጥልቀት በተቀመጠው መካከል ያለው ልዩነት ነው።
~ C. S. Lewis. Richard J. Foster and James Bryan Smith, Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups. Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993. p. 9.
የምንጋደልባቸው የጦር ዕቃዎቻችን ከዚህ ዓለም አይደሉም (2 Corinthians 10.4).
ቁልፍ መርሆች
ከዚህ በታች በተመለከቱት ፅሁፎች ላይ በመመርኮዝ የሚከተሉትን ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦች ያንብቡና ያብራሩ መልስም ይስጡ።
የናሙና ጥናቶች
1. “ወደ አዕምሯችሁ የሚመጡ ነገሮች ሁሉ ከጌታ አይደሉም። ምንጮቹን መፈተሽን ይማሩ! “አዲስ አማኞች አዕምሮአቸው የመንፈስ ውጊያው የጦር ሜዳ መሆኑን መረዳት መማር አለባቸው። ጠላት ሀሳባችን ላይ መድረስ ይችላል እናም ውሸቶችን፣ የሃሰት ሃሳቦችን ወይም የተዛባ መረጃን በመስጠት አማኞችን ማሳሳት ይችላል። እነዚህ ማጭበርበሮች የሚታመኑ ከሆነ ስሜታዊ ጉዳትን፣ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና ወደ ጎጂ ባህሪያትና ልማዶች ሊመሩ ይችላሉ። ምንም እንኳን መለኮታዊ መሳሪያዎች እኛ የያዝን ቢሆንም የተሳሳቱ ሀሳቦች እና አመለካከቶችን ለመቋቋም “ለዲያብሎስ መልስ መስጠት” መማር አለብን ማለትም ጠላት በእኛ ላይ የሚያመጣውን ውሸት ለመመከት መጽሃፍ ቅዱሳችንን መጠቀም መማር አለብን። ጌታ ኢየሱስን ከዲያብሎስ ጋር ያደረገውን የፈተና ታሪክ ዳግመኛ በማቴ. 4፡1-11 አንብብ። ጌታ የዲያብሎስን ፈተና እንዴት ሊቋቋመው ቻለ? የእሱ መሳሪያ ምን ነበር? ሰይጣን በምድረ በዳ በነበረበት ወቅት ለጠየቀው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር? ይህ ዛሬ ስለእኛ መንፈሳዊ ውጊያ ምን ያስተምረናል? 2. “ከዚህ አሰልቺ የማይለወጥ ልምምድ ውስጥ መውጣት ፈጽሞ አልችልም። በጭራሽ!” ዛሬ ባለው ፈጣን ሞገድ ባለበት ዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው በፍጥነት እና በቀጥታ የሚፈልጉትን የማግኘት ልምምድ አላቸው። ማንም ሰው የሚፈልጉትን ወይም የሚሹትን ወይም የሚያስፈልጋቸው ከመሞከር በፊት ረጅም ጊዜን፣ የጉልበት ትዕግስት የሚጠይቅ ስራን መለማመድን አይወደድም። እነዚህ አይነት አመለካከቶች የክርስትናን ሕይወት በእጅጉ ሊጎዱ ይችላሉ። ምንም እንኳን ድላቸን፣ ነጻነታችን እና ጥበቃችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለን እምነት
Made with FlippingBook - Online magazine maker