Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 8 እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ • 105
የተረጋገጠ ቢሆንም (I ቆሮ 15፡57; ዮሐንስ 5፡24; ሮሜ 8፡35-39; ኤፌ 1፡3) መዋጋትን እና ድሉን መጠበቅን መማር ይጠበቅብናል።
ወጣት ክርስቲያኖች በቀላሉ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ይጀምራሉ በተለይም በተሻለ ሁኔታ ጀምረው ከዚያም ተመልሶ ሲመጣ ወዲያው ይረታሉ። ችግሮች፣ ተግዳሮቶ እና ፈተናዎች አስቸጋሪ እና አድካሚ ሊሆኑ ይችላሉ፤ እናም እኛንም ሊያሳዝኑን ይችላሉ። በጣም ጠንካራ የሆኑ ክርስቲያኖች እንኳ ሳይቀሩ ሊታለሉ እና ለጠላት ሽንገላዎች እና ውሸቶች ሊረቱና ሊቀበሉ ይችላሉ። አንድ አማኝ ሲሸነፍ እና ከችግሮቻቸው መውጣት ማለትም መልሶ መላልሶ ሃጢአትን ማድረግ እንደገና ይቅርታ መጠየቅ፤ አሁንም ሃጢአትን ማድረግ እንደገና ይቅርታ መጠየቅ ሲሆንባቸው ምን ማደረግ እንዳለባቸው ያምናሉ? አንድ በእምነት የጎለመሰ ክርስቲያን አንድ የህይዎት ሁኔታ ወይም ጉዳይ በጣም ከባድ ስሆነባቸውና ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲያምኑ ምን ልትነግሩት ትችላላችሁ? 3. “በውጊያው ስኬታማ ለመሆን ቁልፉ ጽናት ነው:: የመጀመሪያውና የመጨረሻው ትምህርት ፈጽሞ ተስፋ መቁረጥ የለብንም የሚለው ነው። “ በገላትያ አማኞች መካከል ስለነበረው የስጋና የመንፈስ ትግል ሲናገር ጳውሎስ ትምህርቱን በዚህ መንገድ ጠቅለል አድርጎ ገልጿል፡ ራሳችሁን አታሞኙ ወይም አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም ወይም አይቀለድበትም። አንድ ሰው ለመዝራት የሚመርጠውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋዊ ፍላጎት እና መሻት የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን፣ ጥፋትን እና መፍረስን ያጭዳልና፥ ነገር ግን በመንፈስ ፍቃድ የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ስለዚህ ሳንዝል፣ ሳንታክት እና ተስፋ ሳንቆርጥ መልካም ሥራን መሥራትን እንቀጥል ምክኒያቱም በጊዜው በርግጠኝነት እናጭዳለንና። እንግዲያስ መልካም ለማድረግ ዕድሉን እና ጊዜን ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ(ገላትያ 6:7፟-10)። ጳውሎስ በጎ ነገርን ለማድረግ ደካሞች መሆን እንደሌለብን ተናግሯል። በሌላ አነጋገር እንደ መንፈሳዊ ሰው አነጋገር ግባችን ላይ ከመድረሳችን በፊት ተስፋ መቁረጥ የለብንም ማለት ነው። የገላትያ አማኞች ተስፋ ሳይቆረጡ ለሚያደርጉት መሥዋዕትነት ሽልማት ወይም ብድራትን እንደሚያገኙ ቃል ገባቶላቸዋል። በጦርነቱ ውስጥ ያሉት ነገሮች ሁሉ የተማሯቸውን ልምምዶች ተግባር ላይ በማዋል እና ጳውሎስ ያስተማራቸውንም የእምነት ትምህርቶች በተግባር ላይ በማዋል ላይ የተመሠረተ ነው። ለማቆም እምቢ ቢሉና ቢቀጥሉ ለሚያደረጉት ጥረት ሽልማታቸውን እንደሚያጭዱ ቃል ገብቷል። ስለራስዎ በሚያስቡበት ጊዜ ከሁሉም በላይ የሚያስጨንቁዎት ነገሮች ሁሉ ከየትኛውም ነገር በላይ ተስፋ ለመቁረጥና ትጥቆትን ለመፍታት አልያም ለመተው ምክንያት የሆኑት ምንድን ናቸው? በመንፈሳዊ “ውጊያ ውስጥ” ውጊያውን ለመቀጠል ለኃጥያት፣ ውሸቶች እና ፈተናዎች ለማሸነፍ እና ፈተናዎችን ለመቋቋም ምን ማድረግ ይችላሉ? በርግጥ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ከጨለማ መንግስት ሥልጣን ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ፈልሰናል። በዚህም ምክንያት መንፈሳዊ ተዋጊ፣ የክርስቶስ ወታደር እንዲሁም “በዚህ ዓለም ባለው የጨለማ ሃይል” ጠላት ሆናችኋል። ምንም እንኳን እነኝህ ጠላቶች በሐሰት፣ በውሸታቸው እና በማጭበርበራቸው ለማጥመድ እና ሊያጠቃችሁ ቢፈልጉም በእምነትና በተግባር እነሱን ለመረዳት እና ለማሸነፍ ትማራላችሁ። ዘወትር በማስተዋል መልካሙን እና ክፉውን እንዴት መለየት እንደምትችሉ መማር ትችላላችሁ (ዕብ 5.11-14)። አትፍሩ። የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር
ማዛመድ
Made with FlippingBook - Online magazine maker