Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
106 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ዕቃ ስንይዝ ማለትም የቅዱስ ቃሉን እውነቶች ስንማር እና እግዚአብሔር ስለ እኛ ከመሰከረው ምስክርነት ጋር የተስማማ ህይወት እስከኖርን በእምነት እየበሰለን እንኖራለን።
ዲያቢሎስ እርስዎን ለማነሳሳትና ሊያበሳጭዎት ይሞክራል ይሁን እንጂ ለመጸለይ በጀመራችሁ ጊዜ ከእናንት ይሸሻል። ከሁሉም በላይ ደግሞ መልካም ስራ በመስራት ይጠመዱ። እንዲህ በሚያደርጉ ጊዜ ዲያቢሎስ ወደ እናንተ እንዳይደርስ ተከልክሏል።
~ Thomas á Kempis. Richard J. Foster and James Bryan Smith, Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups. Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993. p. 152.
ይሄ እንዴት ይሆናል? የጠላት በጣም የተለመደው ዘዴ እኛ የምንሰማቸውን ውሸቶች እንድናምን እና እነርሱንም በተግባር እንድንተገብር ማድረግ ሲሆን፤ የእኛ ታላቅ የጦር ዕቃ (እኛ የእርሱን ጥቃት የምንከላከልበት ትልቁ የጦር ዕቃ) የእግዚአብሄርን እውነቱን ማጽናት ወይም ማረጋገጥ ነው። እያንዳንዱ አማኝ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ መልበስ፣ የሚያጋጥሟቸውን ውሸቶች በንቃት መከታተልና እና እነዚህን ውሸቶች የክርስቶስን እውነት በመድገም እና በመቀበል መቃወም እና መቋቋም አለብን። ዛሬ በህይወትህ ውስጥ የትኞቹ ጉዳዮች ከእግዚአብሄር ብርሃንና እውነት አንጻር እንደገና ማገናዘብ እና መታየት ይገባቸዋል ማለትም ቅዱሳት መጻሕፍት ስለዚህ ጉዳይ ምን ብለው ያስተምራሉ? ከክርስቶስ እውነት ጋር የማይጣጣሙ ነገሮች ምንድን ናቸው? ጳውሎስ በእውነት ውስጥ ስለመኖር ከገለጣቸው ሦስት ስትራቴጂዎች በመነሳት ሃሳብህን ያካፍሉ፡ እርግጥ ነው ይህ ክርስቶስን የተማራችሁበት መንገድ አይደለም!–በእርግጥ ስል እርሱ ሰምታችሁታልና እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ አሮጌን ልብስ አውልቆ እንደማስውገድ በሚያታልል ምኞት ኑሮአችሁን የሚጠፋውን የቀድሞ ኑሮአችሁ ክፍል የሆነውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ። ይልቁንም በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ በእግዚአብሄር እውነት የታደሰውን አዲሱን ሰው ልበሱ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ይህ ጽሑፍ መልካም የሆነውን የእምነትን ገድል ውጤታማ በሆነ መንገድ መዋጋት የምንችልበትን መንገድ ያሳየናል። አንደኛ አሮጌው ሰው (በውሸትና በማታለል) ማስወግድን፣ ሁለተኛ በአዕምሮዎ መንፈስ መታደስን (ስለዚያ ሁኔታ እውነታውን ይንገሩ) እና ሶስተኛ አዲሱን ሰው መልበስ (እንዴት ማሰብ፣ መናገር እና በህይወቶ ዙሪያ ማድረግና አዲስየአኗኗር ዘይቤን እስከሚገነቡ ድረስ ከእውነት ጋር የሚጣጣም እርምጃን ይራመዱ)። ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በሰጠው መመሪያ ላይ በየዕለቱ ያሰላስሉ ተግባራዊም አድርጉ። “አሮጌውን ሰው (ከነውሸቱና ከነማታለሉ)” በመጣል ረገድ በህይውታችሁ የትኛው ክፍል ላይ ትግል አለባችሁ? ከእነዚህ የህይወት ከፍሎች ላይ “ምን ማስወገድ” አለብህ? ዓእምሮዎን እንዴት ማደስ ይችላሉ? ታዲያ “አዲሱን ሰው መልበስ” የሚቻለው እንዴት ነው? መንፈሱ ቅዱስ ጥበብን እና ፀጋን እንዲሰጥዎት ይጠይቁ እና በነዚህ የህይወት ክፍሎችዎ ላይ በእውነት እንዲታገሉ ጥልቅ ማስተዋል ይሰጥዎታል። ~ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች (ኤፌ 4,20-24)
Made with FlippingBook - Online magazine maker