Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 8 እኛ የምንጠቀመው መሳሪያ • 107
እግዚአብሔር ለመዋጋ የጦር መሣሪያን ሰጥቶኛልና እናም በቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ልምምዶች በማክበር፣ በራሴ እውነትን በመናገር እና ውሸቶችን ማመንን ባለመቀበል ማደግ እችላለሁ።
ማጽናት
ቴሬሳ ዴ ሴፔዳ የ አሁማዳ (1515-1582) በ 20 ዓመቷ ክርስቶስን በመንኩስና ማገልገል የጀመረች ስፔናዊት ነበረች። እሷ በጣም የተሰጠች እና ስለ መንፈሳዊ ሕይወቷ ለመጻፍ ልዩ ችሎታ የነበራት ሴት ነበረች። ስለ ጸሎት እጅግ በጣም የታወቀችው “ውስጠኛው ቤተመንግስት” በሚለው ስራዋ ሲሆን ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ የሆነ የቅርብ ግንኙነት ይመለከታል።
ጸሎት
ለመማረክ ጸልይ‹ የኦቪሏ ቴሬሳ
አቤቱ በጥበብህ ሁሉ ግዛኝ፤ ስለዚህ ነፍሴ ታገለግልሃለች እንደ እኔ ምርጫ ሳይሆን እንደ አንተ ፍቃድ ይሁን። አቤቱ አትቅጣኝ። የምሻው ወይም የምጠይቅህ ፍቅርህን የሚያስከፋ ከሆነ አቤቱ ልመናዬን አትስማ ምክንያቱም ሁልጊዜ በውስጤ ይኖራል። እንግዲያውስ እንዳገለግልህ እኔ ለራሴ ልሙት፣ እርሱ ብቻ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። አሜን!
~ Don L. Davis. A Sojourner’s Quest . Wichita, KS: The Urban Ministry Institute, 2010, p. 98.
ጌታ እና መምህር የሆንህ ዘለአለማዊው ጌታ ሆይ በዚህ ዓለም ጠላቶቻችንን ስንጋፈጥ ጥበቃ ሊያደርግልን እና ሙሉ ከለላ ሊሰጠን ትጥቅ በመስጠት እኛን ስለሚያግዘው አስደናቂ ጸጋህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። መንግስትህ በዚህ ምድር ላይ እንዲገዛ በምናደርገው በዚህ ታላቅ ትግል ውስጥ ያለምንም እርዳታ ትተኸን አልሄድክም። እኛ የአንተ ቅዱስ መንፈስ፣ የክርስቶስ ደም ይቅርታ፣ የብርሃን የጦር መሣሪያ እና የቅዱስ ቃሉ እውነት እርሱም ቃልህ አለን። በአንተ ቤተሰብ ውስጥ ተደምረናል፣ አስደናቂ ተስፋ እና የዘለአለም ህይወት ተስፋ አለን፣ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ተሰጥተውናል። አቤቱ አባት ሆይ አሁን እርዳን እነዚህን ድንቅ ስጦታዎች እንድንጠቀምባቸው፣ የዘለአለም ህይወት ተስፋችንን እንድንይዝ፣ እንዲሁም በእውነት መሰረት ለመጓዝ በምንማርበት ጊዜ ሁሉንም ውሸቶች፣ ማታለሎችና የሃሰት ምስክርነቶችን ለማምለጥ እንድንችል እርዳን። የእግዚአብሔርን የጦር እቃ ሁሉ ስንወስድ እና ተስፋ ሳንቆርጥ ይልቁንም በክፉው ቀን ሁሉን ፈጽመን ለመቆምና አንተን በአክብሮት ለመወከል እንድንችል ጥንካሬ ስጠን። በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ። አሜን!
የልብ ጩኸት ለጌታ
በዚህ የድህረ ገጽ አደራሻ www.tumi.org/sacredroots, ተጨማሪ የጽሁፍ እና የቪዲዮ መርጃዎች በተቀናጀ መልኩ ያገኛሉ።
ለበለጠ ጥናት
William J. Backus. Telling Yourself the Truth . Grand Rapids, MI: Bethany House Publishers, 2000.
Made with FlippingBook - Online magazine maker