Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 9 እኛ የምናሳየው ጽናት የቅዱሳን ጽናት
በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፣ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ ሁሉንም አይነት ልመናን እና ጸሎትን እያቀረባችህ በመጽናት ሁሉ ትጉ። ይህንም በሙሉ ልባችሁ በማኖር ከጽናት ጋር ስለ እግዚአብሄር ቅዱሳን ሁሉ ምልጃን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ።
~ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች (ኤፌ 6፡18)
በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ የሚከተሉትን በማመን ስለምናሳየው ጽናት ይገነዘባሉ። • ወደ ክርስቶስ የማደግ ማዕከላዊ መርህ በመጽናት፣ ንቁ በመሆን እና ከወጥመድ መያዝ ውጭ መኖርን በመማር ፤ ምንም ያህል ከባድ የሆኑ ነገሮች ቢመጡም ሽልማቱን ለማግኘት ወደፊት መግፋትና ወደፊት መቀጥል እንዳለብን ያካትታል:: • መንፈስ ቅዱስ እኛ በምናደርገው መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ በጸሎት እንድንፀና ለጥሪያችን ታማኝ እና የተሰጠን እንደንሆን እኛን በማገዝ ሃይልን ይሰጠናል። • ለክርስቶስ እውነተኛ እና ለጥሪያችን ደግሞ ታማኝ ሆነን ስንቆም ሌሎች ውጊያቸውን ሲጋደሉ ለማገዝ እግዚአብሄር ሊጠቀምብን ይችላል። ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።
ዓላማዎች
የመግቢያ ጸሎት ለጥበብ
በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።
109
Made with FlippingBook - Online magazine maker