Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
110 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
1. “ለምንድን ነውብዙ ክርስትያኖች ፓስተሮችም እንኳን ሳይቀሩ ለእምነታቸው ጀርባቸውን የሚሰጡት?” ዛሬ ኢየሱስን እንደ ጌታ እናውቃለን ብለው የሚናገሩ ብዙ ሰዎች እምነታቸውን ትተዋል፣ ቤተ ክርስቲያናትን ጥለው ሄደዋል እናም በክርስቶስ ያገኙትን መንፈሳዊ ጥሪ እምቢተኞች ሆነው ትተው ሄደዋል። ይህ እውነት በቤተክርስቲያን ደረጃዎች እና አግዳሚ መቀመጫዎች ላይ ያሉትን ብቻ ሳይሆን በመድረክ ላይ ያሉትንም ጭምር ነው። የአብያተ ክርስትያናት ቁጥሮች እይቀነስ እየተዘጉ ነው እናም ብዙ አገልጋዮች በቅዱስ ቃሉ እና በክርስቶስ ላይ ጀርባቸውን እየሰጡ ነው። ብዙዎቹ ይህንን ንድፍ ለማብራራት እየሞከሩ ነው ሌሎች ደግሞ ክርስትናን የበለጠ “አዝናኝ” እና የበለጠ “አስፈላጊ” እንዲሆን በማድረግ ይህን የውጪን ፍሰት ለማስቆም ይፈልጋሉ። ለምን ይመስልሃል በዚህ ሁኔታና እንደዚህ ባለው ጊዜ ብዙዎች ሰዎች የተደራጁ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሁም በክርስቶስ ማመናቸውን እንኳን ጥለው የሚሄዱት? 2. “በጣም ከባድ ነበር እናም በራሴ በጣም አዝኜ ነበር። ወደኋላ ለመመለስ እና ወደ አሮጌው ሕይወቴ ሄጄ ለመኖር አስቤ ሁሉ ነበር!”በርካታ ወጣት አማኞች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ለክርስቶስ ባለ ከፍ ያል መሰጠትና ፍቅር እንዲሁም በአስቸጋሪ ጊዜ ስለ ሚያምኑት ነገር ፈተናና ማመቻመች መካከል በከፍታና በዝቅታ አዙሪት ውስጥ ራሳቸውን ያገኛሉ። አንድ አዲስ አማኝ ወይም ያደገ ክርስቲያን በተደጋጋሚ ሲወድቅ ደግሞም ሲነሳ ከዚያም ቆይቶ ሲወድቅ ከዚያም ከእያንዳንዱ ውድቀት ለመነሳት ሲታገል ራሱን ማግኘት በጣም ተስፋ አስቆራጭ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ዑደት ምላሽ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል-”ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል: ከዚያም ይነሣል; ነገር ግን ክፉዎች በአስቸጋሪ ጊዜ በጥፋትና በመፍረስ በክፉ ላይ ይወድቃሉ።” (ምሳ 24.16). የክርስትና ሕይወት እጅግ ዋጋ ያለው ነው ነገር ግን ቀላል አይደለም። ላደግ ለየክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸውን ጉዞ በሚቀጥሉበት ጊዜ እራሱን ወይንም ራሷን በትዕግስት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ትምህርቶች ውስጥ አንዱ የክርስትና ሕይወት ከትግል፣ ከችግር፣ እና ከመከራ ነጻ ሆኖ አለመፈጠሩን ነው። መዝሙራዊው ምን እንደሚል ስናውቅ እንደተበደልን ሆኖ ሊሰማን ይችላል፡ “የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው: እግዚአብሔር ግን ከሁሉ ያድናቸዋል (መዝ 34:19) ።” ሐቀኞች ከሆንን ከማንኛውም ዓይነት መከራ እና ፈተና ነፃ የሆነ ህይወት መኖር እንፈልጋለን! አንዳንዶቻችን እንደ እግዚአብሔር ተወዳጅ ልጆቻችን ብዙ መከራዎችንና ፈተናዎችን ስንቋቋም አንዳንዶቻችን ስሜታችን ይጎዳኛል እንዲያውም የተታለልን ሁሉ ሊመስለን ይችላል። እናም አዲስ ክርስቲያን ሲሆኑ እንደነዚህ ባሉት ችግሮች መካከል በመተማመ መጽናት አስቸጋሪ ሊሆንብዎት ይችላል። ሆኖም ክርስቶስ ከተማራቸ ትምህርቶች እንዱ እንድሆን ቅዱሳት መጻሕፍት ያረጋግጥልናል፤ ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ ወቅት በታላቅ ድምፅ እና በእንባ ከሞት ሊያድነው ለሚችለው ለጌታ እግዚአብሄር ጸሎትን እና ልመና እንዳቀረበ ይነግረናል። ኢየሱስም እግዚአብሔርን በመፍራቱ እና በመገዛቱ ምክንያት ተሰምቷል። ምንም እንኳን ኢየሱስ በእርግጥ ልጅ ቢሆንም በተቀበለው መከራዎች አማካኝንት መታዘዝን ተምሯል (ዕብ 5.7-8)። በእምነት ጉዞችን ውስጥ የክርስቶስ ምሳሌነት እኛ ልዩ ለዩ ፈተናን ስንጋሰጥ በትዕግስት ለመወጣት እንድንችል ምን ዓይነት ተስፋን ይሰጠናል? 3. “ኢየሱስ መታዘዝን እንደፈፀመ – እኛም በምንካፈለው በመከራችን በኩል ልክ እንደርሱ መታዘዝን እንማራለን።” አንድ አዲስ አማኝ ለመማር ከሚከብዱት እጅግ በጣም አስፈላጊ
ማዛመድ
Made with FlippingBook - Online magazine maker