Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 9 እኛ የምናሳየው ጽናት • 111

ባለፈው ክፍለ ጊዜ (እኛ የምንጠቀመው መሣሪያ) ስለ መንፈሳዊ ውጊያ መሳሪያዎቻችን ተምረናል። በዚህ በክፍል ውስጥ ደግሞ መልካሙን የእምነት ገድል ስንታገል ጽናት እና ቁርጠኝንትን እንድታዳብሩ ይበረታታሉ። የሆነ ነገርን ለመቋቋም ከእሱ መሸሽ የለብንም። በልባችን ውስጥ ከምናምነው እና ከምናውቀው ጋር የተቆራኘ ቋሚና ወጥነት የሆነ መንገድን ለመከተል መወሰን ይኖርብናል። ራሳችንን ማስማረክ ወይም መመለስ የለብንም። ምንም እንኳን አስቸጋሪ እየሆን ቢመጣም፣ ፈታኝ ሁኔታዎች እና ተስፋ የሚያስቆርጡ ሁኔታዎች ቢኖሩንም፤ አዕምሮአችንን እግዚአብሄር በገባው የተስፋ ቃል ላይ ለመታመን ፣የእርሱን መሪነት እና ጥንካሬ በመጠበቅ እና በጽናት ወደ ፊት ለመሄድና ለመገስገስ መቃኘት እና ማዘጋጀት አለብን። ስለዚህ ጽናት መከራዎች ወይም ፈተናዎችን ተስፋችንን እና እምነታችንን በመፈታተን ተስፋ እንዳያስቆርጡን እንዲሁም ከእምነታችንም እንዳናፈገፍግ የመቋቋም ቅዱስ ግትርነት ማለት ነው። ጽናት ሁልጊዜ እንዲህ ይላል “ምንም ቢሆን ለጌታ ያለኝን መሰጠት አልጥልም።” የሌሎች አማኞችን በማበረታታት፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸሎት እና በእግዚአብሔር ተስፋዎች በመታመን ክርስቶስ በኩል ግባችንን ለማሳካት ወደ ፊት ልንገፋ እንችላለን። እኛ ከጸናን ብቻ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልና መንግሥት መሰጠታችንን እና ቁርጠኝነታችንን እናሳያለን። ተስፋ ካለቆረጥን ልናሸንፍ እንችላለን። ስለዚህም መልካሙን የእምነት ገድል በጽናት በጽናት ለማሳየት ወታደሮችን፣ አትሌቶች እና ገበሬዎች በምሳሌነት ማሳየት ይቻላል (2ኛ ጢሞ 2፡1-8) ። ወታደሮች ብዙውን ጊዜ መከራን መጽናትን፣ ያለእረፍት ለረጅም ጊዜ መስራትን፣ መድከምን ወይም አሰልቺ የሆኑ ወይም ለአደጋ የተጋለጡ ሆነው መከራን መቋቋምን መማር አለባቸው። አትሌቶች በሁሉም ዓይነት የአየር ጠባይ እና ሁኔታዎች ውስጥ ይለማመዳሉ፣ በሚያሳዝን እና በሚጎዱበት ጊዜ እንኳን ራሳቸውን መገፋፋትን መማር አለባቸው። ገበሬዎች የአየሩን አይነትና ሁኔታውን እንዲሁም የሰብሎችን ሁኔታ በማይቆጣጠሩበት ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው አዝመራውን በትዕግስት ይጠብቃሉ። ልክ እንደነዚህ ምሳሌዎች ሁሉ እኛም መጽናት አለብን። ነገሮችን ለመሞከር እና ለመውደቅ ዝግጁ መሆን አለብን፤ እናም በመጨረሻም ውጊያው የጌታ መሆኑን በማወቅ እንደገና መሞከርን መቀጠል አለብን። ዘርን መዝራት እንችላለን፣ ታጋሽ እና ጌታን መጠበቅን መማር አለብን። ይህን ካደረግን እግዚአብሔር መከሩን በጊዜው ያመጣዋል። ጸሎቱ በዋነኝነት ቤተክርስቲያን ተልዕኮዋን ስታስፋፋ ከጨለማ ስልጣን እና ካለማመን ጋር ለምታደርገው ግብግብ በጦርነቱ ውስጥ መነጋገሪያ መሳሪያ ነው። እኛ ወደ ውስጥና ራስ ተኮር ለሆነ ምቾት ብቻ ጸሎትን መጠቀም ስንጀምር ጸሎት ጉልበት ማጣቱና አለመስራቱ አያስደንቅም። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ውስጥ የክርስቶስን መንግስት ለማስፋፋት ስንሄርድ ለሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ጥሪ ለማድረግ እንድንችል ጸሎትን ሰጥቶናል።

ይዘት

~ John Piper. Let the Nations Be Glad. Grand Rapids, MI: Baker Academic, 2010, p. 65.

Made with FlippingBook - Online magazine maker