Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

112 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

የምናሳየው ጽናት ትምህርት 9 የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን አጠር ያለ መልስ ይስጡ። 1. እንቅፋቶች እና ጠላቶች አማኞች ወደ መንፈሳዊ ብስለት እንዳይደርሱ እና ለክርስቶስ ፍሬ እንዳያፈሩ የሚከላከሉ ተግዳሮቶች ናቸው። ማቴዎስ 13፡1-9፣ እና 13፡18-23ን ያንብቡ። የዘሮቹን አራት ወቅቶች ይዘርዝሩ እና መግለጫውን ከማብራሪያው ጋር አዛምድ።

ሀ. በመንገድ ላይ የወደቁት ዘሮች

___ በቀሉ፣ ጠወለጉና ደረቁ

ለ. በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘሩ ዘሮች

___ በመካከላቸው ባለ እሾህ ታነቁ

ሐ. በእሾህ መካከል የወደቁ ዘሮች

___ ወፎች መጥተው ዘሩን ለቀሙት

መ. በመልካም አፈር ላይ የወድቁ ዘሮች

____ አድገው 30፣ 60 እና 100 እጥፍ አፈራ

2. በእምነታቸው በታማኝነት በጸኑ ብዙ በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ ። ዕብራውያን 12፡1-11ን አንብብና ባዶዎቹን ሙላ:

ሀ. በፊታችን ያለውን ሩጫ ____________________ እንሩጥ(ቁ .1).

ለ. መከራ መንፈሳዊ ዲሲፕሊንን ስለሚሰጠን መከራን በጽናት እንታገሳለን፤ ምክኒያቱም እግዚአብሄር ሲቀጣን እንደ _______________________ እያደረገ ነው (ቁ. 7) ።

ሐ. ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት _____________________(ቁ. 11)።

3. በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ልዩ ተጽኖዎች የተገፉ የአማኞችን ታማኝነት በማስታወስ፤ እኛም ልዩልዩ ፈተናዎች ሲደርስብን መጽናትን መማር እንችላለን።

ሀ. 1ቆሮ. 10፡1-13 አንብብ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጡ አማኞችን ምሳሌነት በመመልከት እንዴት ነው በእምነት ውስጥ ስለ መጽናት ትምህርት ልናገኝ የምንችለው?

ለ. ኢዮብ 23: 8-14ን አንብብ። ኢዮብ መከራና ፈተና ሲደረሰበት ካሳየው ተገቢ አመለካከት በመነሳት፤ እኛ ፈተናና መከራ ሲያጋጥመን ምን ትምህርት ልናገኝ እንችላለን?

4. ጸሎት ሰዎች በአስቸጋሪ ጊዜያት ወይም ችግር ውስጥ ሲገቡ እራሱን ወይም እርሷን የሚያቀርቡበት የእግዚአብሄር ማርከሻ እና አቅርቦት ነው። የሚቀጥሉትን ጥቅሶች ከትክክለኛው ገለፃ ጋር ያዛምዱ።

ሀ. የሉቃስ ወንጌል 18፡1-8 ___ በጸሎት ለምኑ፣ ፈልጉ፣ አንኳኩ እግዚአብሄር ይመልሳልና።

Made with FlippingBook - Online magazine maker