Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
114 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
8. የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን ልክ እንደ ወታደር፣ አትሌት እና ገበሬ መከራን መቋቋምን መማር አለብን። 2ጢሞቴዎስ 2፡1-8ን ያንብቡና የሚከተልውን ዓረፍተ ነገር ከመግለጫው ጋር ያዛምዱ። እነዚህ ምሳሌዎች የክርስትናን ሕይወት ሁኔታ በደንብ እንድንረዳ እንዴት ያግዙናል?
ሀ. አንተ የሰማኸኝ ነገር
___ እንደ ህጉ የተሾመ
ለ. መከራን አብረኽኝ መከራን ተካፈል ___ በታማኝነት ማስተማር ለሚችሉት ለሌሎች ታማኞች አካፍላቸው።
ሐ. እንደ አትሌት ተወዳደር
___ የፍሬውን የመጀመሪያ ድርሻ ይካፈላሉ
መ. ታታሪ ገበሬ
___ ጥሩ የክርስቶስ ወታደር ነው
ሠ. ኢየሱስ ክርስቶስ አስብ
___ የዳዊት ዘር
9. መከራዎችን በጽናት ስንወጣ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም ይልቁነም እኛን ለማጠንከር እግዚአብሔር እንደሚጠቀምባቸው እናውቃለን። በመሆኑም በሚያጋጥመን ነገር ሁሉ መሄድ እንድንችል ጥበብን ይሰጠናል። ያዕቆብን 1፡2-8 ያንብቡና የሚከተሉትን ይመልሱ
ሀ. ልዩ ልዩ ዓይነት ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ምን ማድረግ ይኖርብናል? (ቁ 2)
ለ. ትዕግሥት ወይም ጽኑ መንፈስ ሙሉ በሙሉ ሲፈጸም ምን ይሆናል? (ቁ 4)
ሐ. ችግሮችና መከራዎች ሲያጋጥሙን ጥበብ የጎደለው ከሆነ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ ይመክረናል? (ቁጥር 5-8)
መልካሙን የእምነት ገድል የምንጋደል እንደመሆናችን መጠን እስከ መጨረሻው ድረስ በትዕግስት እንድንፀና ተጠርተናል። መጽናት ማለት አንድን ነገር በመቋቋም በውስጡ ማለፍ፣ መጽናት፣አለመደበቅ ወይም አለመሸሽ ማለት ነው። ክርስቶስን በጥላቻ በተሞላ ዓለም ውስጥ እንድሚያገለግሉ ክርስቲያኖች፤ የዚህን ዓለም ሥርዓት የማያቋርጥ ፈተና፣ በውስጣችን አፍራሸ የሆነው የኃጢያት ተፈጥሮ እና የጠላት ዲያቢሎስ ውሸት ዘወትር በቋሚነት ይፈታተኑናል። ውጥረት ውስጥ ነን፤ ችግሮች ተጋርጠውብናል እንዲሁም ሌሎች እኛን በተሳሳተ መንገድ ተረድተውናል። በእነዚህ ሁሉ ፈተናዎች መካከል መፅናትና ጌታን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን እና በገባው የተስፋ ቃል ላይ በመተማመን እንድንኖር እንደሚያስተምረን ስለምናውቅ እንደ ሙሉ ደስታ መቁጠር አለብን። መጽናት ማለት በእምነታችንን በግትርነት መቆም ማለት ነው ይሁን እንጂ ነገር ግን በቅድስና እና በራስ መተማመን መሆን አለበት። ብዙ ጊዜ ለደረሰብን መከራዎች ምክንያት ግንዛቤ ላይኖረን ይችላል ነገር ግን እግዚአብሔርን እንተማመናለን። የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወይም በጌታችን ላይ ጀርባችንን እንድንጥል የሚደረግብንን ማንኛውንም ነገር መተውና መቃወም ይኖርብናል። መፅናት ማለት ለመንፈሳዊ ውሳኔዎቻችን መሰጠታችን ታማኝ በመሆን በእግዚአብሔር ሀይል እና አቅርቦት
ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Online magazine maker