Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 9 እኛ የምናሳየው ጽናት • 115

ላይ መታመን ማለት ነው። ፈተናዎችን በምንፈታበት ጊዜ እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን በሌሎች አማኞች፣ ስንጸልይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝንት፣ እንዲሁም በቅዱስ ቃሉ ማበረታታት ይሰጥናል። ይሄንን ኮርስ ሲጨርሱ ይሄ ጅማሬ እንደሆነ ይወቁ። ለማቆም ጊዜው አይደለም፤ ለማመቻመችም እንዲሁ. ጸንተው በስፍራዎ ያለመናወጥ ይቁሙና ጌታን ይጠብቁ፤ እርሱ ፍላጎትዎን ያሟላል።

ከዚህ ትምህርት ጋር በመያያዝ ሊያጠኗቸውና ሊያሰላስሏቸው ይሚገቡ ትምህርቶች የሚከተሉት ናቸው:

ተጨማሪ መግለጫዎች

ሃምፕ (ተጨማሪ መግለጫ 15) ለመወከል ብቁ መሆን: የእግዚአብሔር መንግሥት ደቀ-መዝሙር ማብዛት (ተጨማሪ መግለጫ 20) የአዲስ ኪዳን ሥነ-ምግባር፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ መኖር (የመመለስ መርህ) (ትግበራ 21) እግዚአብሔር ይነሣ! ጌታን የመሻት እና የእርሱን ምህረትን የመፈለግ ሰባቱ “ሀ” ዎች (ተጨማሪ ማብራሪያ 23) አሁኑ እንደግና ያግኘነው፣ በተጨባጭ ተነሳሽነትም የተገነዘብነው ለሳይንስ፣ ለአትሌቲክስ እና ለሙዚቃ ሞያ ተግባራዊ መሆን የሚችል እንዲሁም ለሃይማኖታዊ ልምምዳችን ተመሳሳይ የሆነ መርሆዎችን ነው። አንድ ጊዜ በእንደዚህ ያሉ ጉዳዮች ላይ ፍጹም ነፃነት ማሳየ የተለመደ ስታይል ነበር ማለትም ተጨባጭ በሆነ ሕግ ላይ ተወስነው ባልተሟሉ ሁኔታዎች ውዝግብ ተሞልቶ ነበር ነገር ግን እንዲህ ያለው ደካማነት አሁን ጊዜው ያለፈበት ነው። በመሠረቱ እኛ ልንረዳቸው አንችልም ነገር ግን ስልጣን ያላቸው ሰዎች የበለጠ ኃይል ያላቸው ይመስላል። . . . . ክርስትያኖች ድንቅ የሆነውን እውነት ማየት ጀምረናል ይህም ክርስቲያን ማለት ነው የክርስቶስን ቀንበር በመሸከም ባዶ የሆኑ ነጻነቶችን በመካድ የሚኖር ማለት ነው። በክርስቲያኖች ትምህርት ውስጥ መሰረታዊ የሆነ አዲስ ትርጉም ያለው ትምህርት እንመለከታለን ይህም ወደ ጥፋት የሚያደርስው መንገድ ሰፊ መሆኑን እና ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ግን በባህሪው ጠባብ መሆኑ ነው። እኛ አሁን የምናውቀው ክርስቲያን እሱ ደስ ያሰኘውን የሚያደርግ ሳይሆን ይልቁንም በሁሉ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚፈልግ መሆኑን ነው።

~ Elton Trueblood. The Yoke of Christ. Waco, TX: Word Books Publisher, 1958, pp. 130-131.

እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ (የዮሐ. ራዕይ ምዕራፍ 2፡ 10)

ቁልፍ መርህ

ከዚህ በታች በተመለከቱት ፅሁፎች ላይ በመመርኮዝ የሚከተሉትን ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦችን ያንብቡና እና ያብራሩ እንዲሁም መልስ ይስጡ።

የናሙና ጥናቶች

1. “እኔ በተሽከርካሪ (ሮለር-ኮአስተር) ላይ እየተጫወትኩ ይሰማኛል - ወደ ላእወጣለሁ ወደታች እወርዳለሁ፤ ወደላይ እወጣለሁ እናም ወደ ታች እወርዳለሁ።” ጌታን ከጥቂት ወራት በፊት የተቀበለ ወጣት በችግሮች እና በፈተናዎች ሲናወጥ የተፈጠረበትን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሲገልጽ የተናገረው ነበር። በቤት ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ጋር አለመግባባት፣ በሥራ ገበታው ሰዎች ሊረዱት አለመቻላቸው እና ከመቼውም ጊዜ በላቀ ፈተና እና ጫናዎች ይገጥሙት ጀምሮ

Made with FlippingBook - Online magazine maker