Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

116 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

ነበር። እነዚህ የክስተቶች ዑደት ይህን ወጣት የክርስቶስ ወታደር ተስፋ ለማስቆረጥ የጀመሩ ሲሆን እርሱም “በትክክለኛው መንገድ ክርስቶስን ተቀብዬዋለውን?” በማለት መጨነቅ ጀምሮ ነበር። እርሱ ብዙ ጉዳዮች እያጋጠሙት ስለነበር “እኔ በተሽከርካሪ (ሮለር-ኮአስተር) ላይ እየተጫወትኩ ይሰማኛል - ወደ ላእወጣለሁ ወደታች እወርዳለሁ፤ ወደላይ እወጣለሁ እናም ወደ ታች እወርዳለሁ።” እኔ አሁን በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። አንድ የተሳሳተ ነገር እያደረግኩ እንደሆነ አስባለሁ። እኔ የማውቃቸው ብዙ ክርስትያኖች አሁን አሁን እኔ እንደማልፈው እያለፉ እንዳልሆነ አስባለሁ።” እስካሁን ባጠናሃቸውት ጥቅሶች በመመርኮዝ ለዚህ አዲስ ክርስቲያን እያለፈበት ስላለው ሁኔታ እና ምን ማድረግ እንዳለበት ምን ዓይነት ምክር ይሰጡታል? 2. “ያለ እግዚአብሔርን ሕዝብ እንዴት ላደርገው እንደምችል አይታየኝም! እነሱ ይህንን ሁሉ ልዩነተ እንዳመጣ ረድተውኛል።” አንድ ጥሩ የሆነ ወንድም በእስር ቤት ውስጥ ወደ ክርስቶስ ከመጣ በኋላ እና ከእስር ከተፈታ በኋላ ወዲያውኑ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ራሱን በቁርጠኝነት ሲሰጥ የተናገረው ንግግር ነው። በዚያ ጉባኤ ውስጥ ከሚገኙት አማኞች ጋር በተቻለው አቅም ሁሉ ብዙ ጊዜ ያሳልፍ ነበር። በየአገልግሎቶቹና በትምህርት ሁሉ ላይ እየተካፈለ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ሌሎች ወንድሞች ጋር በፍጥነት ጓደኛ ሆነ። በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በተለያዩ የመስክ የወንጌለ ስርጭት ውስጥ በፈቃደኝነት ያገለገለ ሲሆን በግል ሕይወቱ ውስጥ ለሚገጥሙ ጉዳዮች የፓስተሩን ምክር ይፈልግ ነበር። ለበርካታ አመታት ይህ የአብያተክርስቲያናት ጉባኤ የእርሱ መኖሪያ ቤት ሆኖ ነበር፤ በቀጥታ ከመኖሪያ ቤቱ ርቆ ይገኛል፤ እናም በህይወቱ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ፓስተር እና አማኞችን እንዴት እንደጠቀሙት በማሰብ “”ያለ እግዚአብሔርን ሕዝብ እንዴት ላደርገው እንደምችል አይታየኝም! እነሱ ይህንን ሁሉ ልዩነተ እንዳመጣ ረድተውኛል።የእነሱን ድጋፍ፣ ፍቅር እና ምክር ዛሬ ጌታን እንዳገለግለው ምክንያት ናቸው።” ይህ ምሳሌ በእምነታችን እንድንጸና ሌሎች አማኞች ያላቸውን ሚና እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 3. “መቼ ነው ነገሮች ሊለወጡ የሚጀምሩት? ከእንዲህ ዓይንት መከራ ጋር ለረዥም ጊዜ ስፈተንና ስታገል ነበር። በጣም ብዙ መጠበቅ ያለብኝ ይመስለኛል።” አንዳንድ ጊዜ የክርስቲያን ሕይወት አስደሳችና አዳዲስ ትምህርቶች እና ድሎች በተደጋጋሚ የሚያመጣ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለረዥም ጊዜ በማይረሱ ችግሮችና ፈተናዎች ተሞልቶ በብስጭትና በሀዘን ስሜት ውስጥ በመጨመር ሊጓዙ እና አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አማኞች ለረዥም ጊዜ በህመም ሲሰቃዩ፣ የሚወዱትን ሰው በሞት ሲያጡ፣ ወይም ከሥነ ምግባር ውድቀት ጋር በመታገል ከፍተኛ ሥቃይ ሲደርስባቸው በፍጥነት ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። ለክርስቲያናዊ ጉልምሳ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ትምህርቶች አንዱ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዴት መጠበቅ እንዳለበት መማር ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ እኛ መቋቋም እንድንችል የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልገናል። ለዚህ ነው የክርስቲያን ሕይወት ልምምዶች ወይም ዲሲፕሊኖች በጣም አስፈላጊ የሆኑት። የቱንም ያህል ቢሰማንም ወይም ነገሮች የተገላቢጦሽ ቢሆኑም በጸሎት መፅናትን፣ በአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ከክርስቶስ ተከታዮች ጋር ህብረት ማድረግን፣ በእግዚአብሔር ቃል መጽናትን እና ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ መልመድ ይኖርብናል። እኛ እየደረሰብን ያሉት ነገሮች በፍጹም ተስፋ እንዳያስቆርጡንና የመጨረሻውን ውሳኔ እንዳይኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በመንፈሳዊ ዲሲፕሊናችንም ሆነ ከሌሎች የክርስቲያኖች ኅብረት ጋር በምንጓዝበት ወቅት ስሜቶችን እና ለሁኔታዎቻች የምንሰጠው ምላሽ ክርስቶስን ለመከተል እንዴት እንደምንወስን እንዲፈቅዱ ማድረግ አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው?

Made with FlippingBook - Online magazine maker