Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 9 እኛ የምናሳየው ጽናት • 117

በእርግጥ ወደ ክርስቶስ የማደግ መሰረታዊ መርህ መፅናት፣ ንቁ መሆን፣ እና ከመንፈሳዊ ጥበቃ አለመጉደልን መማር ማለት ነው። ምንም ያህል ከባድ የሆነ ነገር ቢገጥመንም ሽልማታችንን ለመቀበል ወደ ፊት መግፋትና መቀጠል አለብን። ግን ይህን ብቻችንን አናደርግም። መልካሙን የእምነትን ገድል በምንጋደልበት ወቅት በቀጣይነት ጸንተን እንድንቀጥል እና ለጥሪያቸን ታማኝ ሆነን እንድንቆም የሚያግዘን ብዙ ሀብቶች አሉን። የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታታናል-እርሱ ዘወትር በእኛ ውስጥ በመኖር፣ ሌሎች ስጦታ ካላቸው አማኞች ጋር እንድንሰራ ያበረታታናል፣ እናም በአስፈላጊ ጊዜ እኛን ያበረታናል። እያደገ የሚሄድ አንድ ክርስቲያን ውጥረትንና ትግልን፣ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚደርስባቸውን ፈተናዎች እየተቋቋሙ በጽናት መቀጠልን መማር ይኖርባቸዋል። የጸሎት ጊዜዎችህን፣ በቃሉ፣ እና በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ያለህን ተሳትፎህን ገምግም። በሁኔታዎችዎ ውስጥ የመፅናትን ችሎታን ለማዳበር እንዲችሉ መንፈስ ቅዱስ ምን ምን ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈልጋል? አንድ ወይም ሁለት ነገሮችን ይምረጡና ለጌታ አሳልፈው በመስጠት በጌታ ኃይል መከራዎችን ለመቋቋም እንዲችሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን ይውሰዱ። አስታውሱ እናንተ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ አልተረሳችሁምም፤ ሁሉም ደቀ መዛሙርት መፅናትን በመማር ላይ ናቸው (2 ጢሞ 3፡ 12) እና ጌታም ከቶ አይተዋችሁም ወይም አይጥላችሁም (መዝ 27፡1-3)። በጌታ እና በእርሱ ብርታት መከራዎችን በመጽናት እና በሁሉም ነገሮች ክርስቶስን ማክበር ይችላሉ። ብዙ የጭንቀት እና የስሜት መቃወስ በሽታዎች የሚከሰቱተ ለአመታት ራስን በራስ ለማስደሰት ወይም ራስ ወዳድነት በሆነ መንገድ ኑሮን ለመኖር በሚደረግ ጥርቅም ውጤት የሚከሰት ነው። ይህንን ጉዳይ ስለ ሰካራሞች ወይም ነጻ ነን ብለው ስለሚያምኑ ሰዎች አይደለም ይህንን የምለው፤ ይልቁነም አልኮል መጠጣትን ወይም የጾታ ብልግናን የመፈጸም ሐሳብ እንኳን ማሰብ እጅግ አሰቃቂና ኢ-ስነምግባራዊ እንደሆነ ለሚያስቡ መልካም ክርስቲያኖች ጭምር ነው። ነገር ግን እነሱ ያልተገሩ እና ያልሰለጠኑ ድክመቶቻቸው በፈተና እና በመከራ ውስጥ ይገለጣሉ። ከችግሮች መራቅ፣ ከማይጣጣሟቸው ሰዎች መራቅ፣ ቀላልና አቋራጭ መንገድን መፈለግ፣ ነግሮች ሻካራና ጠንካራ እየሆኑ ሲመጡ ትቶ መሄድ ወይም ማቆም፣ አድሎአዊነት እና አቅመቢስነት የሚታይባቸው የህይወት ዘይቤ ነው። ብዙ መጻሕፍት ሊነበብ ይችሉ ይሆናል፣ብዙ ዶክተሮች እና ሰባኪዎች አማክረዋል፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጸሎቶች ሊደረጉ እና ሃይማኖታዊ ቁርጠት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፣ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ህክምናዎች እና መደሃኒቶች በከፍተኛ ወጪ ምክር ሊያገኙ ይችላሉ፤ ይሁንና እነዚህ ሁሉ የችግሩን ትክክለኛውን መንስኤ ማከም አይችሉም ምክንያቱም ትክክለኛው ችግር የዲስፕሊን እጥረት ወይም ስድነት ነውና። እናም ትክክለኛውና እውነተኛው ፈውስ ስርዓት ያለው ወይም የዲስፕሊን ሰው መሆን ነው።

ተዛምዶ

~ Richard Shelly Taylor. The Disciplined Life: Studies in the Fine Art of Christian Discipleship. Kansas City, MO: Beacon Hill Press, 1962, pp. i-ii.

ምንም እንኳን ተቃውሞዎችን ብጋፈጥም ሁል ጊዜ ንቁ እንደሆን እስከ መጨረሻው ለመፅናትና ሌሎች አማኞችም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ለመርዳት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሰጥቶኛል።

ማጽናት

ጆን ዌስሊ (1703-1791) ከሳሙኤል እና ሱዛን ዌስሊ (በእምነት አስደናቂ ጀግና ከሆነችው) የተወለዱ ከ 19 ልጆች አንዱ ነበር።ወጣት የኮሌጅ ተማሪ በነበረበት ጊዜ እርሱ እና ጓደኞቹ የተቀደሰ ህይወት ለመኖር እና እርስበር ለመበረታታት ተሰባስበው ይፀልዩና መጽሐፍ ቅዱስን ያጠኑ ነበር፤ እናም ሌሎች ይህንን የእምነት ዘይቤአቸውን “ሜቶዲስትስ” በሚል መጥሪያ ይጠሯቸው ነበር። የታሪክ

ጸሎት

Made with FlippingBook - Online magazine maker