Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
134 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
• ዮሐ 8.31-32 - እኛ በእርሱ እና በቃሉ ውስጥ መኖራችንን ስንቀጥል የክርስቶስ ደቀመዛሙርት መሆናችንን እናሳያለን እናም እንዲህ በማድረጋችን እውነትን እናውቃለን፤ እውነትም አርነት ያወጣናል። • ገላ. 5፡13 - በክርስቶስ እንደ ወንድሞችና እኅቶች ሆንን እኛ ሁላችን ለነጻነት ተጠርተናል፤ ነገር ግን ነፃነታችንን ሥጋዊ ምኞታችንን ለማድረግ ፍቃድ አይደለም ይልቁንም በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ለመሆን ተጠርተናል። ይህ በነጻነት ላይ ያተኮረው ሃሳብ በአዕምሮዬ ውስጥ የምናደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ ለአዋቂዎች ወይም ለወጣቶች በሆነ ዓውድ ውስጥ ያስቀምጣል። አብዛኛውን ጊዜ ብዙ አዳዲስ ክርስቲያኖችን ደቀ መዝሙር የምናደርግበት መንገድ የተለያዩ ጥፋቶችን እና የሥነ ምግባር ጉድለቶችን ዝርዝር (ዝርዝሮችን) የያዘ ነው ይህም አንዳንድ ጊዜ ክርስትና ፀረ-ድርጊት የሆነ ሃይማኖት (ነገሮችን ያለማድረግ ሃይማኖት ነው) ብቻ እና/ ወይም ኃጢአትን ላለመሥራት ከልክ በላይ የሚጨነቅ እምነት ተደርጎ እንዲቆጠር ያደርገዋል። በእርግጥ በክርስትና ውስጥ የሞራል ስብዕና ትኩረት በነፃነት ላይ ማለትም በከፍተኛ ዋጋ በተከፈለ ነፃነት ላይ እግዚአብሔርን ለመውደድ እና መንግሥትን ለማስፋት፤ በጌታም ፊት በፍጹም መገዛት የመኖር ነጻነት ነው። የከተማ ነዋሪዎች የሞራል ግዴታ በኢየሱስ ክርስቶስ ነፃ መሆን፤ በህይወታቸው ለእግዚአብሔር ክብር በነፃነት መኖር እና ነፃነታቸውን እንደ ኃጢአት ፍቃድ እንዳይጠቀሙበት ማድረግ ነው። የትምህርቱ ዋነኛው ሃሳብ የሚያተኩረው በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ያገኘነው ነፃነት እና ከእሱ ጋር ያለን አንድነት ላይ ነው። እኛ አሁን ከሕግ፥ከኃጢአትና ከሞት ስርዓት፥ከኃጢአታችን ኩነኔ እና ከጥፋተኝነት፥እንዲሁም በእኛ ላይ ካለ የእዳ ስህፈት ነፃ ወጥተናል። አሁን እግዚአብሔርን በአክብሮትና በደስታ እናገለግላለን፤ እንዲሁም የሚጠበቅብን ሞራላዊ ግፊት በክርስቶስ ነፃነት ውስጥ መኖር ነው። ይሁን እንጂ ነፃነታችንን ተጠቅመን ዜደኛ ወይም የማይረባ ሰው ለመሆን ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማክበር እና ሌሎችን ለመውደድ እንጠቀምበታለን። ይህ የግብረ ሰዶማዊነትን፥, ውርጃን እና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮችን በተመለከተ የሚያብራራ ዐውደ-ጽሑፍ ነው። በእንደዚህ ዓይነት ድርጊት የተሳተፉ ሰዎች ነፃነታቸውን ለይስሙላ ያንፀባርቃሉ ነገር ግን በክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውቀት የሌላቸውና ፤ በእግዚአብሔር የሥነ ምግባር ፍቃዱ ወይም በፍቅሩ የማይታወቁና የራሳቸውን ውስጣዊና ስጋዊ ዝንባሌዎች የሚፈጽሙ ናቸው። በክርስቶስ ነጻነት እንደ ከተማ ደቀመዛሙርት የቅድስና እና የደስታን ኑሮ የመኖር የደስታ ጥሪ ነው። ይህ ነጻነት ክርስቲያኖች በተለምዶ “ነጻ ነኝ” በመባል የሚታወቅው ይልቁንም ወደ ባርነት፥ኀፍረት እና ጸጸት በሚዳርገው እሳቤ መካከል እንዴት መኖር እንደሚችሉ አቅምን ይፈጥርላቸዋል።
Made with FlippingBook - Online magazine maker