Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

140 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

ተጨማሪ መግለጫዎች 14 በክርስቶስ ያገኘናቸው ሠላሳ- ሦስት በረከቶች ሬቨ. ዶ/ር ዶን ኤል. ዳቪስ

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመኑበት ወቀት በህይወቶ እነዚህ 33 ነገሮች እንደተከሰቱ ያውቃሉ? የዳላስ ቲኦሎጂካል ሴሚናሪ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት የነበረው ሉዊስ ስፔሪ ቻፈር በተዋቀረ ሥነ መለኮት መጽሐፉ፣ ጥራዝ 3 (ገጽ 234-266) ውስጥ እነዚህን የመዳንን ጥቅሞች ዘርዝሯል። እነዚህ ነጥቦች ከአጭሩ ማብራሪያዎቻቸው ጋር ዳግም የተወለደ ክርስቲያን በህይወቱ/በህይወቷ ውስጥ ስለተከናወነው የጸጋ ሥራ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ስለ አዲስ ህይወቱንህይወቷ አድናቆት እንዲሰማቸው ያደርጋል።

1. በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ውስጥ አማኙ የሚከተሉተን ነግሮች ነው:

ሀ. አስቀድሞ የታወቅ ነው - ሐዋርያት ሥራ 2፡23; 1 ጴጥ. 1፡2, 20። እግዚአብሔር በአጠቃላይ የዓጽናፈ ዓለም ውስጥ እያንዳንዷን ፕሮግራሞች በሙሉ ያውቃል።

ለ. አስቀድሞ-የተወሰነ ነው - ሮሜ. 8፡29-30። የአንድ አማኝ ዕጣ ፈንታ በእግዚአብሄር ቅድመ- ዕውቀት የታወቀና ሁሉንም የእግዚአብሔር የጸጋ ሀብቶች እስከማወቅ ድረስ መድረስ ነው።

ሐ. የተመረጠው ነው - ሮሜ. 8፡38; ቆላ 3፡12። እርሱ/እርሷ በዚህ ዘመን በእግዚአብሄር የተመረጠ እና የእግዚአብሔርን ጸጋ ለወደፊቱ ያሳያል።

መ. የተለየ ነው - ኤፌ. 1.4. እግዚአብሔር አስቀደሞ ያውቃቸውን እና የመረጣቸውን ለራሱ ይሆኑ ዘንድ ለያቸው።

ሠ. የተጠሩ ናቸው - 1 ተሰ. 6፡24. እግዚአብሔር የሰውን ልጆች የመዋጀቱን ዓላማዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጋብዟቸዋል። ይህም ቃል እግዚአብሔር ለመዳን የመረጣቸውን ሰዎች ሊያጠቃልል ይችላል ነገር ግን አሁንም ባልተመለሰ ሁኔታቸው ውስጥ ያሉትን ሊያካትት ይችላል።

2. አንድ አማኝ ቤዛነትን አግኝቷል - ሮሜ. 3፡24። እሱ /እርሷም ከኃጢአት ነጻ እንዲሆን የተፈለገው ዋጋ ተከፍሏል።

3. አንድ አማኝ ከክርስቶስ ጋር ታርቋል - 2 ቆሮ. 6.18, 19; ሮም. 5፡10። እሱ/እርሷ ሁለቱም ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንዲያደርጉ እና ከእግዚአብሔር ጋር በኅብረት እንዲኖሩ ታርቀዋል። 4. አንድ አማኝ በክርስቶስ ማዳን በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት አለው (ሮሜ. 3.24-26. እሱ/እርሷ በልጁ በኢየሱስ ሞት አማካኝነት ለኃጢአተኞች እግዚአብሔር ከሚሰጠው ፍርደታ ነጻ ሆኗል።

5. አንድ አማኝ በደሉ ሁሉ ይቅር ተብሏል። - ኤፌ. 1.7. ሁሉም ኃጢአቶቹ/ኃጢአቷ - ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱ በሙሉ ዋጋ ተከፍሏል።

Made with FlippingBook - Online magazine maker