Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ተጨማሪ መግላጫ • 141
6. አንድ አማኝ አሮጌው ሰው ወድ ፍርድ ለማምጣት “በአዲስ ህይወት ለመራመድ” እንዲችል ከክርስቶስ ጋር ተጣምሮአል ሮሜ. 6፡1-10. እሱ / እርሷ ከክርስቶስ ጋር በአንድነት እንዲኖሩ ተደርገዋል።
7. አንድ አማኝ “ከሕግ ነጻ ነው” -ሮሜ. 7፡2-6. እሱ/እርሷ ለተከሰሰበት ክስ ሙት ሆኗል እንዲሁም ከህግ ሥልጣን ነጻ ወጥቷል
8. አንድ አማኝ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኗል - ገላ. 3.26. እርሱ/እርሷ በመንፈስ ቅዱስ ዳግም የመወለድ ኃይል ወደ አዲስ ህይወት እግዚአብሔር የመጀመሪያውና ህጋዊ አባት ወደሆነበት እንዲሁም የዳኑት በሁሉም መብት እና ስልጣን የእግዚአብሄር ሀጋዊ ልጅ - የእግዚአብሔር ወራሽ እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወራሽ እንዲሆን ተወልዷል።
9. አንድ አማኝ በእግዚአብሄር ቤት እንድ ጎለመሰ የማደጎ ልጅ ተደርጎ ተወስዷል ሮሜ. 8፡15, 23።
10. አንድ አማኝ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል - ኤፌ. 1.6. እርሱ/እርሷ ጻድቃን ሆነዋል (ሮሜ 3 22) ፣ ተቀድሰዋል (ተለይተዋል) ስፍራቸው ተለይቷል (1 ቆሮ 1, 30, 6.11); በአቋሙ/ በአቋሟ ዘለዓለም ፍጹማን ተደርገዋል (10፣14) እና ለዘላለም በተወደዱት ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል (ቆላ 1 ÷ 12).
11. አንድ አማኝ ጻድቃን ሆኖአል - ሮሜ. 5.1. እሱ/እሷ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጻድቅ ሆነው ተቆጥረዋል።
12. አንድ አማኝ “በክርስቶስ ቀርቧል” - ኤፌ. 2.13. የቅርብ ወዳጅነት በእግዚአብሔር እና በአማኝ መካከል ተመስርቷል።
13. አማኝ ከጨለማው ኃይል ነፃ ወጥቷል -ቆላ. 2፡13። አንድ ክርስቲያን ከሰይጣን እና ከክፉ መናፍስቱ ነጻ ወጥቷል። ያም ሆኖ የክርስቶስ ደቀመዝሙርቶች እነዚህን ኃይሎች መዋጋት አለባቸው።
14. አንድ አማኝ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ፈልሷል -ቆላ 1፡13። ክርስቲያን ከሰይጣን መንግሥት ወደክርስቶስ መንግሥት ፈልሷል።
15. አንድ አማኝ በዓለቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ተተክሏል - 1 ቆሮ. 3፡9-15። ክርስቶስ እምነቱ የቆመበት መሰረቱ እና እሱ /እሷ የክርስትና ሕይወቱን/ህይወቷን የሚገነቡበት መሠረት ነው።
16. አንድ አማኝ ለክርስቶስ ኢየሱስ የተሰጠ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው - ዮሐንስ 17፡6, 11, 12, 20. እሱ/እርሷ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠ/የተሰጠች የፍቅር ስጦታ ናቸው።
17. አንድ አማኝ በስጋ ሳይሆን በክርስቶስ መገረዝን አግኝቷል- ቆላ 2፡11። እሱ/እርሷ ከአሮጌው የኃጢያት ተፈጥሮ ኃይል ነጻ ወጥቷል።
18. አንድ አማኝ የቅዱስ እና የንጉሥ ክህነት ስልጣን ተካፋይ ተደርጓል - 1 ጴጥ. 2፡5, 9። እሱ/ እርሷ ሊቀ ካህን ከሆነው ክርስቶስ ጋር ባላቸው ግንኙነት መሰረት ካህናት ናቸውን እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር በምድር ላይ ይገዛሉ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker