Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

16 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቅሃለሁ አሜን!

1. በዓጽናፈ ዓለም ውስጥ የምንኖር እኛ ብቻ ነንን? ብዙዎቹ የሆሊዉድ ፊልሞች አብዛኛውን ጊዜ ከአሉታዊ ወይም መጥፎ ነገሮች ጋር የተዛመዱ እንግዳና ያልተለመዱ ፍጥረቶችን ያሳዩናል። ምንም እንኳን ይህ ሕይወት የት እንደሆነ ወይም ምን እንደ ሆነ ባያውቁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዓጽናፈ ዓለም ውስጥ ብቻችንን እንዳልሆንን ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ የሰው ዘር በራሱ በጠፈር ውስጥ ካሉ የሰማይ አካላት ላይ ከሚገኙት የፀሐይ ግዑዝ ጨረሮችና የሰማይ ጋላክሲ ብቻ እንደሚኖር ያምናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በተራ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ሌሎች ደግሞ በመለኮታዊ* አሰራር አማካይነት የተፈጠርን ነን ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ማንም ሊያውቅ እንደማይችል አጥብቀው ይናገራሉ። ከልጅነትዎ ጀምሮ ከየት እንደመጣን በተመለከተ የእርስዎ አመለካከት ምን ነበር? ስለ ሰማይና ስለ ዓለም መገኛ ምን ዓይነት አስተምሮዎ ነበርዎት? 2. “ከዕለታት አንድ ቀን . . . !” አብዛኞቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የጨዋታ ዘፈኖቻችን ለልጆች የተፈጠሩ ተረቶችን እና የተለያዩ ታሪኮችን በቤት ውስጥም ሆነ በቤተክርስቲያን አልያም በትምህርት ቤት እየሰማን ነው ያደግነው፡፡ በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ታሪኮችን መስማት እና መተረክን ይወዳሉ። በፊልሞች በመጽሃፎች በኮሜዲዎች በቴሌቪዥን ትርዒቶች በዘጋቢ ፊልሞች በማህበራዊ ሚዲያዎች በጋዜጦች እና በሬዲዮ - በየቀኑ በደርዘን የሚቆጠሩ ታሪኮችን እንሰማለን፤ አንዳንዶቹ እውነተኛ አንዳንድ ሐሰተኛ ፤ አንዳንዶቼ አነሳሽ ሌሎች ደግሞ አሳፋሪዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ቅዱሳት መፅሐፍቶችን የያዘ አንድ ትልቅ ቤተ-መፅሐፍ ነው( ከ 1500 ዓመታት በላይ በበርካታ ደራሲዎች የተጻፉ 66 ቅዱሳት መፅሐፍትን የያዘ) ነገር ግን ስለ አንድ ወጥ ታሪክ - ስለ እግዚአብሄር እና እርሱ ፍጥረቶቹን ለማዳን ስላለው ፍላጎት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ታሪኮችን በተመለከተ ምን ያስባሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ማዳኑ ወጥ ታሪክን እንደሚናገር ሰምተው ያውቃሉ? በበርካታ ታሪኮች ወይም ባነበብናቸው ታሪኮች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልዩነቶች እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ደራሲዎች ስለ እግዚአብሔር እና ለዓለም ድኅነት የመሰጠትን ወጥ ታሪክ መካከል ምን ልዩነቶች አሉ? 3. “እስከሚገባኝ ድረስ ግልጽ የሆነ አንድ ዕቅድ አይታይኝም።” ከክርስትና እምነት ጅማሮ ማለትም ከሐዋርያት ዘመን ብዙም ሳይቆይ አማኞች መሠረታዊ የክርስትና እምነቶቻቸውን የሃይማኖት መግለጫ በሚል ስያሜ አንቀጾችን በማዋቀር እምነታቸውን በአጽንዎት አረጋግጠዋል። በታሪክ ውስጥም ሆነ እስከ ዛሬ ድረስም ከሚታውቁት እና በተደጋጋሚ ከተጠቀሱት የሃይማኖት መግለጫዎች ውስጥ የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እና የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ዓብይና በዋናነት የታወቁ ናቸው (አባሪውን ይመልከቱ)። እነዚህ ሁለት ግልጽ የእምነት መግለጫዎች እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ፣ በክርስቶስ በኩል የሰራቸውን ስራዎች እንዲሁም በእግዚአብሔር ጊዜና ጥበብ አሰራር መሰረት እርሱ ፍጥረታቱን እንዴት ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመልስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታን አጠቃልለው ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ የማያምኑ ሰዎች ኮስሞስ (አጽናፈ ዓለም) ያለምንም ዓላማና ፈጣሪ ባጋጣሚ የተፈጠረ ወይም ወደ ሕልውና የመጣው ነው ብለው ይከራከራሉ። ሁሉንም ነገር አንድ ላይ የሚያገናኝ ምንም ዕቅድ እንደሌለ ይናገራሉ፤ እንዲሁም ይህ ለምን እንዲህ እንደሆነ፣ እኛ እዚህ ለምን እንደምነኖር የት እንደምንሄድ እና ሁሉም ነገር እንዴ ትፍፃሜን ደሚያገኝ ለማወቅ የሚረዳን አንድም ማብራሪያና ማሰርጃ ማግኘት እንደማይቻል ይከራከራሉ። ኤቲስቶች

ግንኙነት

*መለኮታዊ ፦ መለኮታዊ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ኃይሎች ናቸው ወይም ታላቅ ኃይል ያላቸው አማልክት ናቸው።

Made with FlippingBook - Online magazine maker