Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 27
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህና ጌታህ ከተቀበልክበት ጊዜ ጀምሮ ይህ እውነት ሆኖ ያገኘኸው በምን መንገድ ነው?
ባለፈው ክፍለ ጊዜ (ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል) ውስጥ የእግዚአብሔር ድነት የሚለው ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በደንብ እንደተብራራና በህይወት ውስጥም ለሚነሱ ትልልቅ ጥያቄዎች መልስ እንዴት እንደሠጠ ተምረናል። ነገር ግን ይህ አስገራሚ የእግዚአብሄር ታላቅ ታሪክ ልክ እንደ ፊልም ወዲያው ታይቶ ለመዝናናት እና ከዚያም ለመርሳት እንደሚሆን መሆን የለበትም። ይልቁንም ይህንን ትልቅና አስደናቂ ታሪክ ማለትም እግዚአብሄር ፍጥረትን በክርስቶስ ለማዳንና ለማደስ ያለውን ሃሳብ ስንሰማ ከእግዚአብሔር ጋር ለመተባበር ውሳኔ ማድረግ አለብን። የእርሱን ታላቅ ስራ ታሪክ ምስክርነት ስንሰማ እውነት እንደሆነ መቀበል የራሳችን ታሪክ ማድረግና ከዚያም በዚህ መልካሙን የእምነት ገድል ውስጥ መሳተፍ መጀመር አለብን። መደባችንን በመለየት እና በፈቃደኝነት ወደ ጌታ ሰራዊት በመቀላቀል መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል አለብን። በራሳችን መልካምነት ምንም የሚሆን ነገር የለንም ይልቁንም በክርስቶስ ምትክነት (“በእኛ ቦታ በመሞቱ”) በእርሱ በኩል ብቻ ለእኛ በተገለጠ በእግዚአብሄር ምህረት ሰዎች ሁሉ ወደዚህ ታላቅ ተጋድሎ እንዲሳተፉ ጥሪን እናቀርባለን። የመዳን ግብዣው ጥሪ ለጦርንት የክተት ዘመቻ ጥሪ ነው- ከጨለማው መንግሥት ወደ ብርሃን ምንግሰት ለእኔነት ብቻ ከተደረገ ኑሮ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምባሳደር ለመሆን የሚደረግ ጉዞ እንዲሁም እረሱን በዚህ በጠማማ እና በተበላሸ ዓለም ውስጥ በጽድቅና በእውነት መከተል ማለት ነው። ዓመፀኝነትህንና ኃጢአትህን በመናዘዝና ንስሐ* በመግባት ከእርሱም ምህረትንና ይቀርታን ብትጠይቅ እግዚአብሄርን በመስቀል ላይ በሞተውና ደሙን ባፈሰሰው በክርስቶስ በኩል ይቅር ይለሃል ያነፃሃልም እንዲሁም ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዲኖርህ ያደርጋል። የእግዚአብሔርም ቤተሰብ ወደሆነችው ወደ ክርስቶስም አካል ወደቤተክርስቲያንም ያስገባሃል። ድነትን በመቀበላችን ምክንያት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤቱን በእኛ ውስጥ አድርጓል እግዚአብሔርን ለማክበር ክርስቶስን ለማገልገል እና ሥራውን ለማከናወን በየዕለቱ ኃይል ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመለስበት ጊዜ ወደ እኛ ይዞ የሚያመጣውን የእግዚአብሔር ሙሉ ስጦታ መያዣ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ለወደፊቱ በክርስቶስ ለምንቀበለው ውርስ እንደ ዋስትና ይሆነናል። ከኃጢያት መመለስ እና በእምነት ከክርስቶስ ጋር መጣበጥ ማለት ለሰይጣን መንግሥት ካለን ታማኝነት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መመለስና መለወጥ ማለት ነው። ይህን ስናደርግ በእምነት እግዚኣብሄርን ካመኑት እና ከሚመጣው ቁጣ ለማማለጥ ከተባረኩት ሁሉ ጋር እንገናኛለን ወይም እንተባበራለን። የውኃ ጥምቀትም* ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉ አማኞች ያዘዘው ሲሆን ይህም መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ለሰራው የፀጋ ስራ ማለትም እኛን ጌታችንና መሪያችን ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ያቆራኘንና ለትንሳኤው ጌታ ያለንን ታማኝነታችንን በይፋ እና ባደባባይ የምናውጅበት ውጫዊ ምልክት ነው።
ይዘት
*ንስሀ መግባት - ማለት ሃሳብን መቀየር፣ መመለስ እና በሌላ ተቃራኒ መንገድ መሄድ እና እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መመላለስ ማለት ነው። ንስሀ ስትገባ በተሳሳተ ጎዳና ላይ እንደሆንክ እና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ለመኖር ባህሪህን እንደምትለውጥ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማትህን መግለፅህ ነው።
*ጥምቀት - አማኞች ወደ ክርስቶስ አካል ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግና ለመተባበር ውሃን በመጠቀም የሚፈፀም ሃይማኖታዊ ስርዓት ነው። ይህም በውሃ ውስጥ በማጥለቅ አሊያም በራስ ላይ በማፍሰስ ሊፈፀም ይችላል። ጥምቀት የሚለው ቃል “ባፕቲዞ/baptidzo” ከሚለው ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም “ወደ ውስጥ መግባትወይም መሸፈን” ማለት ነው። ስለዚህ ጥምቀት ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም የመንፈሳዊ እውነታ ማለትም አሁን እናንተ ክርስቶስ ውስጥ እንደሆናችሁ የሚያመለክት ውጫዊና ይፋዊ መግለጫ ነው። እያንዳንዱ አማኝ መጠመቅ አለበት ምክንያቱም ኢየሱስ ሁላችንም እንድናደረገው አዞናል በማድረጋቸንም ለእሱ ያለንን ታማኝነት እናሳያለን።
Made with FlippingBook - Online magazine maker