Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 35

መለወጥ የሚችል እና አሁን ደግም እንደ አዲስ ሰው ነፃ ሆኖ ለመኖር አዲስ ተፈጥሮን የተቀበለ፣ ከአዲስ ቤተሰብ ጋር የተቀላቀለና በአዲስ ጌታ የሚመራና የሚተዳደር ነው (ኤፌ 4፡20-24)። በዳናችሁ ጊዜ መንፈሳዊ ተጋድሎውን እንድተቀላቀሉ ከሰራዊቱ ጋር ተመዝግባችኋል፤ ለወደፊት ጉዞአችሁም ብቁ አደርጎአችኋል። ስለዚህ ተወዳጁ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆይ ወደ ቤተሰቡ እንኳን ደህና መጣችሁ እና ወደ ጦርነቱም እንኳን ደህና መጣችሁ! እስካሁን ድረስ ካልተጠመቃችሁ የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪያችሁን፣ ክርስቲያን ጓደኞቻችሁን ወይም ፓስተራችሁን መጠመቅ እንደምትሹ እና እንደሚያስፈልጋችሁ ንገሩት። የአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን የጥምቀት ሂደቱን ለመከተል ዝግጁ በመሆን በተቻለ ፍጥነት ለመጠመቅ የሚያስፈልገውን ስርዓት በመከተል ተግባራዊ አድረጉት። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ሁሉ እንዲጠመቁ ከእርሱ ጋር ያለንን አንድነት ምልክት እና ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና ለመንግሥቱ ታማኝ መሆናችንን በይፋ እንድናሳውቅ አዟል (ማር 16.14-16; ማቴ 28.18-20)። አትዘግዩ፤ ጥምቀት በተጠናቀቀው በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሥራ ላይ ለተሰጠህ ህይወትና ስጦታ ውጫዊ ምልክት ነው። እርሱን ስሙ፤ ከዚያም በቅርቡ ተጠመቁ!

በእምነት ለእግዚአብሄር የምህረት ጸጋ ምላሽ ሰጥቻለው፣ ነቀፋ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ሆኛለሁ፣ ከጨለማው ኃይል ግዛት ወደ ልጁ መንግሥት ገብቼኣለሁ።

ማረጋገጫ

ይህ ጸሎት የቴ ዴም ላውዝሙስ ከ4 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ ክርስቲያኖች ያነበቡት ጸሎት ነው። እሱም ከ335-414 ለዳኪያ ጳጳስ ለነበረው መታሰቢያነት የተሰጠ ነው፤ ሆኖም ግን በአፈ ታሪክ አውጉስቲን ሲጠመቅ አምቤሮስ ድንገተኛ የስንብት ስብስብ አድርጎ ተጠቅሞበታል ይባላል።

ፀሎት

አንተ አምላክ ነህ (ቴ ዴም ላውዝሙስ)

አንተ አምላክ ነህ: እኛ እናመሰግንሃለን; አንተ ጌታ ነህ፡ እኛ ባንተ እንደነቃለን አንተ ዘለአለማዊ አባት ነህ፤ ፍጥረት ሁሉ ያመልክሃል እናንተ መላዕከት ሁሉ፤ የሰማይ ኃይላት ሁሉ ኪሩቤልና ሱራፌል እልል በሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኃይል አምላክ በሰማይና በምድር ምስጋና ላንተ ይሁን። ክቡር የሆነው የሐዋርያት ማህበርህ ያወድሱሃል የነቢያቶች ክቡር ህብረት ያወድሱሃል ሰማዕታት ነጭ ልብሳቸውን አንጥፈው ያወድሱሃል በመላው ዓለም ያለችው የተቀደሰች ቤተክርስቲያን ታከብርሃለች ግርማ ሞገስ ለተላበስክ አባት፣ የአንተ እውነተኛ እና አንድ ልጅ ለሆነው ለጠበቃችን እና መሪአችን መንፈስ ቅዱስ አምልኮ ሁሉ ይገባል። አንተ ክርስቶስ የክብር ንጉሥ ነህ፣ የዘለአለማዊ አባት አንድያ ልጅ ነህ እኛን ነፃ ለማውጣት ሰው ስትሆን የድንግል ማህፀንዋን አላስቀሩህም የሞትን ኃይል አሸንፋህ መንግሥተ ሰማያትን ለሁሉም አማኞች ከፍተሃል በእግዚአብሔር ቀኝ በክብር ተቀምጠሃል አንተ በክብር ዳግም እንደትመጣና እንደምተፈርድ እናምናለን

Made with FlippingBook - Online magazine maker