Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

36 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

እንግዲያው እግዚአብሔር ሆይ ናና ህዝብህን ዕርዳ በገዛ ክቡር ደምህ በውድ የገዛኸው ህዝብ ነውና ለዘለዓለምም ከቅዱሳንህ ጋር አምጣን

የዘላለም አምላክ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና የእኔ ፈጣሪዬ ሆይ እኛን ለማዳንውድ ልጅህን ወደ እኛ ስላክልን እጅግ አድርገን እናመሰግንሀለን። እኛ የአንተን ፍቅር እና ይቅርታ ለመቀበል የበቃን አይደለንም ነገር ግን እኛን ለማዳን፣ እወነተኛውን መንገድ እንዲያሳየን በእኛ ኃጢአት ምትክ ውድ ልጅህ መስዋዕት እንዲሆን አድርገኸዋልና ተመስገን። በመንፈስ ቅዱስህም አትመህ የአንተ ቤተሰቦች እንደንሆን ዳግም ወለድከን እናም ከሞት ፍርሃትና ከዘላለማዊ ቅጣት ነጻ አወጣኸን። አሁን ለእንደዚህ ዓይነቱ ፍቅር እና ምህረት ምላሽ ሊሆን የሚችል ምን ልሰጥህ /ላቀርብልህ/ እችላለሁ? ልቤን ህይወቴን ገንዘቤን ጊዜዬን እና ሁሉንም ግንኙነቶቼን እሰጣኋለሁ። ምንም እንኳን አንተን ለማወቅ ጊዜ እንደሚወስድብኝ ባውቅም፤ ለአዲስ ህይወት ለአዲስ አመራር እና ለአዲስ ጉዞ ዝግጁ እንደሆንኩ እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ። እግዚአብሔር ሆይ በታላቁና አስደናቂ ታሪካዊ ስራህ ውስጥ ተሳታፊ አድርገኝ፤ ኦ እግዚአብሔር ሆይ በሰጠኸኝ በመንፈስ ቅደስ ምራኝ። እኔ በምናገረውና በምሠራው ስራ ሁሉ እንዳከብርኽ እረዳኝ። በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ አሜን!።

ለጌታ የልብ ጩኸት

በ www.tumi.org/sacredroots በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ ተጨማሪ የጽሁፍ እና የቪዲዮ መርጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ ጥናት

ሮበርት ዌበር። ዓለምን ለማሳየት የሚበቃው ማን ነው። Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2008.

በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ የምናገኘው መግቢያ በተሰኘው ጥናት ውስጥ የሚከተሉትን ርዕሶች ጨምረን እንመለከታለን። 1. “በክርስቶስ” ውስጥ በመሆን በሚለው ርዕስ ውሰጥ በእርሱ የሆነውንና የተደረገውን እንለማመዳለን። 2. በሐዋርያት እና በነቢያት መሰረትንት ላይ በተገነባው በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ በመሆናችን አናመሰግናለን። 3. እያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል በመሆን እንደሚያገለግል እንረዳለን።

ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ

ሮሜ 10፡ 9-10

የመጽሐፍ ቅዱስ የቃል ጥናት

1. ካልተጠመቃችሁ ከፓስተራቹ ጋር ተገናኙና ለመጠመቅ ጠይቁ። 2. መዳን ለሚያስፈልጋቸው እና በጌታ ሰራዊት ውስጥ ለመግባት ላለበቸው ሶስት ጓደኞቻችሁ ጸልዩ እግዚአብሄርም እምነታችሁን ለእነርሱ ማካፈል እንድትችሉ እድሎችን እንዲሰጣችሁ ለምኑት። 3. ማስታወሻ ደብተር ወይም የዕለት መጽሔት መጻፊያ ደብተራችሁ ላይ እግዚአብሄር በቃሉ የሚሰጣችሁን ዕይታዎችና በጌታ የበሰሉ ክርስቲያኖችን ልትጠይቋቸው የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎችን ፃፉ።

የቤት ሥራ

Made with FlippingBook - Online magazine maker