Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 3 የምናገኘው መግቢያ ህይወታችንን በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ህይወት ጋር ማዛመድ

በእነዚህ ትልልቅ እውነቶች ምክንያት ይህን ለታውቁ ይገባል እርሱም በእግዚአብሄር መንግስት ራሳችሁን እንደ እንግዶች ወይም ባይተዋሮች መቁጠር እንደሌለባችሁ ማወቅ አለባችሁ። ይልቁንስ እንደ እግዚአብሄር ቅዱሳንና ሰማያዊ ዜጎች ተብለው እንደተቆጠሩት አማኞች ራሳችሁን እንድትቆጥሩ - በዕርግጥ እናንተ የእግዚአብሄር ብቸኛ ቤተሰብ አባሎች ናችሁ! ይህም የሆነው በሐዋርያትና እና በነቢያት መልዕክቶት ላይ በተመሰረተውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ በሆነበት ቤት በመታነፃችሁ ነው። በእሱ ውስጥ የቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ መዋቅር እያንዳንዱ አባል እርስ በእርስ ተያይዞ በጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ቤተመቅደስ ለመሆን ያድጋል። በክርስቶስ ሁላችንም በአንድነት ተያይዘን የእግዚአብሔር መገኛ ለመሆን እንሰራለን ይህም ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ እኛ የምናገኘው መግቢያ የሚለውን ሃሣብ የሚከተሉትን ሃሳቦች በመረዳት ይቀበላሉ: • በእምነታችን ከኢየሱስ ጋር እንደተዛመድን (ማለትም አሁን እኛ “በክርስቶስ” ነን) እርሱ የሆነውን የሰራውን እና የሚያቀርብልን ሁሉ እንደምንለማማድ በማመን • በመንፈስ ስቅዱስ አማካኝነትና አሰራር የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ በሆነባት እና በሐርያቱና በነቢያቱ መሠረት ላይ በታነጸች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል መሆናችንን በማመን • እያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ኤምባሲ ሲሆን ይህም የመንግሥተ ሰማያትን ፍላጎቶች እና ዓላማዎች የምታስፈጽምና አማኞችም ይህንን ለማስፈጸም የሚሰሩ የመንግሥቱ አምባሳደሮች እና ወኪሎች መሆናቸውን በማመን ዘለአለማዊው አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32.8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። ~ ጳውሎስ ለኤፌሶን (ኤፌ 2,19-22)

ዓላማ

የመግቢያ ፀሎት ለጥብብ

37

Made with FlippingBook - Online magazine maker