Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
38 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።
በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።
1. “ለምንድን ነው አሁን እኔ ባለሁበት ሁኔታ እና መጽሐፍ ቅዱስ እኔ በእግዚአብሔር ፊት ባለኝ ስፍራ መካከል እንዲህ ዓይነት ልዩነት የማየው?” በርካታ አዳዲስ አማኞች መፅሐፍ ቅዱስ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ስላላቸው ስፍራ በሚናገረው (ለምሳሌ ይቅር እንደተባሉ፣ እንደታረቁ፣ የእግዚአብሄር ልጆች ስለመባላቸውና በእግዚአብሔር በመመረጣቸው) እና ነገሮች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ስለሚሆኑበት ሁኔታ (ለምሳሌ እንደ ጥርጥር፣ ጭንቀት፣ ብስጭት፣ እራስን መኮነን እና ፍርሀት) መካከል ሰፊ ልዩነት ያያሉ። በሁለቱ የክርስትና ሕይወት ዕይታዎች (ማለትምመጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው እና በየቀኑ በሚሰማኝ ነገር) መካከል እርስ በእርሳቸው የማይጣጣሙና እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ይመስላል። የእኛን ክርስቲያናዊ ህይወት በየቀኑ ስንኖር መፅሀፍ ቅዱስ እኛ በክርስቶስ ውስጥ ስላለን ማንነትና እኛ ስለ ራሳችን በሚሰማን ስሜት መካከል ያለውን ውጥረት እንዴት ልንረዳ ይገባናል? 2. “እኔ መጽሐፍ ቅዱስ ም በሚነግረኝ ማንነቴና ልኬት መመላለስ የምጀምረው መቼ ነው?” ውጤታማ የሆነ የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ህይወት ከክርስቶስ ጋር ከመገናኘታችን በፊት በነበርን ህይወት እና አሁን እኛ በተካፈልነውና ባመነው ህይወት ማካከል ያለውን ውስጣዊ ግጭት የመፍታት አቅም አለው። ብዙውን ጊዜ ጌታን ከማወቃችን በፊት የነበረን ማንንት ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም አስተማሪዎቻችን እና መጋቢዎቻችን ስካስተማሩን ይልቅ ጠንካራ ትክክለኛ እና አስተማማኝ የሆነ ሊመስለን ይችላል። አዲስ ወደጌታ የመጣ ክርስቲያን ቀድሞ የነበው አሮጌው ሰው ብቅ እያለ ትክክለኛና “የተፈጥሮ” ማንነቱ እስከሚመስል ድረስ እና ይህ / እኔ / ነኝ ብሎ የተቀበለው ማንነቱ በጣም ምቹና የበለጠ እውነት በሚመስልበት በዚያ ሁኔታ ውስጥ፤ ከዚያ ይልቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እና አዋጆች ጋር ራሱን እንዴት ሊያጣምር ሊቆጥርና ሊያቆራኝ ይችላል? 3. “እኔ በግሌ በቤቴ በመሆንና በመቆየት ከጌታዬ ጋር በራሴ እጓዛለሁ።” በአንድ ወቅት በአደንዛዥ ዕፅ እስራት ውስጥ ይኖር የነበረ በቅርቡ ግን ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙና መድሐኒቱ አድርጎ ተቀብሎ በክርስቶስ አዲስ ህይወትን ለመኖር ጉዞውን የጀመረ አዲስ አማኝ የተናገረው ነው። ለችግሩ ምክንያት የሆነው በአብዛኛው ጎዳና ላይ ስለኖረው ህይወት ማለትም በራሱ በቤተሰቡ እና ከሌሎች ጋር በነበረው ግንኙነት ላይ ሌሎችን ስለጎዳበት ጉዳት በክርስቲያኖች መካከል ሲኖር ያልተለመድና እንግዳ የሆነ ጥልቅ ስሜት ስለተሰማው በጣም ግራ ተጋብቶ ነው። አንድ ቀን ተስፋ ቆርጦና ተበሳጭቶ እንዲህ ብሎ ነበር “ያ ነው እንግዲህ! በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ክርስቲያናዊ ሕይወቴን መኖር እችላለሁ ብዬ አላስብም። እነርሱ ጥሩ እና መልካም ሰዎች ጥሩ ናቸው ነገር ግን አሁን እኔ የመጣሁበትን ዓለምና እኔ የመጣሁበትን ሁኔታ ሊያውቁ አይችሉም፤ ስለዚህ እቤት ውስጥ እቆያለሁ፤ ብቻዬንም ከክርስቶስ ጋር መጓዝ እጓዛለሁ።” ስለ ውሳኔው ምን ልትነግሩት ትችላላችሁ - ውሳኔው ጥሩ ነው? ካልሆነስ ለምን?
ግንኙነት
በመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ( ወዶ ዘማችነታችን ) ከጣዖታትና ከኃጢአት (ንስሓ) ወደ እግዚአብሔር ስንዞር እና ከሙታን የተነሳው ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ስናምን(እምነት) በዚያው ቅፅበት
ይዘት
Made with FlippingBook - Online magazine maker