Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 3 የምናገኘው መግቢያ • 39
በጌታ ሰራዊት ውስጥ ለመሳተፍ ውሳኔ አስተላልፈን ከሰይጣን መንግሥትም ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት እንደግባን ተመልክተናል።
አሁን በእምነትን ከክርስቶስ ጋር ህብረትን ስላደረግንና “በክርስቶስ” እንደምሆናችን መጠን በእርሱ ያገኘናቸውንና ያሉንን መንፈሳዊ ሃብቶችን እንመረምራለን። በእምነት በክርስቶስ ጋር ህብረትን ማድረጋችን በእግዚአብሄር ፊት አዲስ ማንነትና ከእርሱ ጋር ያለን ህብረት(በእርሱ ዘንድ ያለን ስፍራ) የሞገስ፣ የልጅነት እና የእርሱ መንግሥት ዜጋ እንደመሆናችን መጠን የእርሱን በረከቶች እንቀበላለን። ከዚህም በተጨማሪ “በክርስቶስ” መሆናችን መልካሙን የእምነት ገድል በምንጋደልብት ወቅት ዕለት ዕለት በእርሱ ድል እየነሳን እንድንመላለስና - በመንፈስ ቅዱስ ለመራመድ ኃይልን እንቀበላለን(ይህም እውነታችን/our Reality/ ነው)! በአዲስ ኪዳን እንደተጠቀሰው በጌታ በኢየሱስ የሚያምን ሰው ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ አሰራር በክርስቶስ አካል ውስጥ ተጠምቋል (1 ኛ ቆሮንቶስ 12፡13-ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በአንዱ የእግዚአብሔር መንፈስ በሚሠራው አሰራር ሁሉም አንድ አካል ለመሆን ተጠምቀዋል- እስራኤላዊ ቢሆን አልያም አህዛብ፣ ባሪያ ቢሆኑ ወይም ጨዋ ሰው፣ ወንድም ቢሆን ሴትም፤ ሁሉም አንድ አካል ለመሆን ተጠምቀዋል። በክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሁሉ አንዱን መንፈስ ጠጥተዋል።) መንፈስ ቅዱስ በጌታ በኢየሱስ ያመንነውን ሲያጠምቀን (በክርስቶስ አካል ውስጥ ሲያስገባቸው) ከዘላለም ከእግዚአበሄር ቁጣ መዳንና በፊቱ የዘላለም ደስታን ብቻ ሳይሆን የሰጠን በፊቱ አዲስ ማንነትና ከእግዚአብሄር ጋር ልዩ የሆነ ህብረትና ግንኙነትን ሰጥቶናል።ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል በመሆናችን ይህ ተሰጥቶናል። (በተጨማሪ “33 በረከቶች በክርስቶስ” የሚለውን በቅጥል ውስጥ ተመልከቱ) በእርግጥ ለድነታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በመታመናችን በብዙ በረከቶች ተባርከናል። ኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ተብሏል (ኤፌ 1፡7 ቆላ. 1፡ 13) ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፣ ከእሱ ጋር ኅብረትን አግኝተናል (2 ቆሮ 6፡18-19) እና በእግዚአበሄር በአባታችን ቤት ለመኖር አዲስ ልጅነትን አግኝተናል (ሮሜ 8 1፡ 14-15, 23)። በክርስቶስ በመሆናችን ካገኘናቸው እጅግ በጣም ብዙ አስደናቂ በረከቶች አንዱ የክርስቶስ አካል በሆነው ቤተ ክርስቲያን ያገኘነው አባልነት እና ቦታ ነው። በእምነት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ከሚገኙ አማኞች ጋር ህብረት አድረገናል፤ ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በእርስ ተያይዘናል፣ እናም እንደ አንድ ህዝብ የእግዚአብሔርን መንግሥት በመተማመን ለማደግ እና የማገልገል ዕድል ተሰጥቶናል። መልካሙን የእምነት ገድል እኛ ብቻችንን እንደ ገለልተኛ ህዝብ በራሳችን ችሎታና ጥንካሬ ስለማንጋደል እግዚአብሔርን እጅግ አድርገን አናመሰግናለን። ከመጀመሪያው እስካሁን ድረስ ያመኑት ሁሉም አማኞች በአንዱ አስገራሚ የክርስቶስ አካል ውስጥ ገንብተዋል። ብዙ ትላልቅ ስብሰባዎች እና በአጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት (ቤተ ክርስቲያን/church/ በትንሹ «c» ) ቢኖሩም በኢየሱስ እና በሐዋሪያቱ የተጀመረ አንድ ቤተክርስቲያን (ቤተ-ክርስቲያን/ Church/ በካፒታል « C ») ብቻ ነው ያለው:: የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ቤተ ክርስቲያንም አንዲት ቅድስት ሐዋርያዊትና ካቶሊካዊት * (ሁሉን አቀፍ) የሆነች አንዲት ቤተክርስቲያንን እንዳልችና በመላው ዓለም ውስጥ በየአካባቢው ባሉ በርካታ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና በታሪክ ሂደት ውስጥ ሁሉ የተገነባች ናት በማለት ያውጃል።
*ካቶሊክ - ካቶሊክ ማለት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ማለት አይደለም ነገር ግን “ዓለምአቀፍ” ማለት ሲሆን በየትኛውም ዘመን በየትኛውም ነገድ ቋንቋ ሕዝብ እና አገር ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ክርስቲያኖች ለማመልከት የሚውል ቃል ነው። በሐዋርያት እና በኒቂያ የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ ካቶሊክ የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሁሉም ዘመናት እና በሁሉም ጊዜያት በሁሉም ቋንቋና ህዝቦች ውስጥ የቤተክርስቲያንን ሁለንተናዊነት የሚያመለክት ሲሆን ምንም የተለየ የሆነ ባህላዊ ወይም ክፍለ-ሃይማኖታዊ ዓረፍተ ነገርን አያመለክትም (ለምሳሌ በሮማ ካቶሊክ)።
Made with FlippingBook - Online magazine maker