Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
40 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
እንግዲያው የሐዋርያው ጳውሎስን ለፊልጵስዩስ ሰዎች የተናገረውን መልዕክት እናዳምጠው እናም በክርስቶስ ለምናደርገው ጉዞአችን ተግባራዊ እናድርገው፡፡
እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም እነዚያን ዝቅተኛና አቅመ ደካማ የሆነውን የሰውነት አካላችንን ሁሉ ክቡር ወደሆነው አካል ምስል ጋር በማስተካከል ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራሩ የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።
~ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች (ፊል 3: 20-21)
በዕርግጥ እያንዳንዱ አማኝ ሰማያዊ ዜጋ ነው እንዲሁም እያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያንም ለትምህርት፣ ለስብሰባ፣ ለአምልኮ፣ ለመንፈሳዊ ትስስር እና ከሌሎች አማኞች ጋር ለክርስቶስ አገልግሎት ለማድረግ የሚሰራ የእግዚአብሔር ኤምባሲ ነው። ቤተክርስቲያን በተመሰረተችብት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ህዝብ ምን ማመን እንዳለባቸውና እንዴት ማምለክ እንዳለባቸው እና ቅዱሳን መጻሕፍት ምን እንደሚሉ በትክክል መሰረቱን እንዲመሰርቱ መጣ። እነዚህ ዋነኛ የእምነት መሰረቶች በሁሉም ቦታ የሚገኙ አማኞችን ለመቅረፅ የመጣ ሲሆን ታላቁ ባህል ይባላሉ። ይህም የሚያመለክተው በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፉት ትምህርቶች እና ልምምዶች በታላቁ የሐይማኖት መገለጫዎች ውስጥ የተካተቱና በታሪክ ውስጥ በአማኞች ተጠበቀው አዚህ የደረሱ ናቸው ። (ወደ ኋላ ተመልሰው ወደ ፊት መሄድ የሚለውን እና የኒቂያውን የሃይማኖት መግለጫን በተጨማሪ መግለጫ በሚለው ስር ያለውን ይመልከቱ)። ቤተክርስቲያን በተሰበሰበች ቁጥር ሁሉ. . . የዓለምን ፍጻሜ እና የዚህን ዓለም ውድቀት ታውጃለች። ይህ ዓለም ለሰዎች ህላዌ የህይወት መሰረት ትክክለኛ ነው ብለው የሚቀርቡትን ማስረጃና ትምህርትን ሁሉ ትቃወማለች እንዲሁም ዓለማዊ ስርዓቱን ትሽራለች። በተቃራኒው እሷ ማለትም ቤተ-ክርስቲያን የተሰራችው በተጠመቁ አማኞች ስለሆነ የህይወታቸውን ፍቺ ከሞት ባሻገር እንደሆነ ያዩታል እንጂ በዚህ ዓለም መመዘኛና ማስረጃ አያዩትም. . . በመሆኑም የክርስትና አምልኮ የሰዎችን ማንነት በዓለም አቆጣጠር ውጤታማ እና በቂ የሆነ የኑሮ አስተማማኝ መረጃ ለመሰጠት በሚሞክር ሥርዓት መካከል ፊት ለፊት የሚቀርብ ኃይለኛ ተቃውሞ ነው። በዓለም ላይ ያለው የኩራት እና የተስፋ መቁረጥን በጠንካራ ሁኔታ መቃወም የሚችል ከቤተክርስቲያን አምልኮ ውጪ ምንም ለም።”
~ ዣን-ጃክ ቮን አለንሜ፡፡ አምልኮ: - ሥነ መለኮት እና ልምምድ ለንደን: - Lutterworth, 1966, p. 63.
የምናገኘው መግቢያ ትምህርት 3 የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ካነበባችሁ በኋላ እያንዳንዱን ጥያቄ ከመፅሃፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር በማዛመድ ግልፅ በሆን መንገድ ይመልሱ።
1. በጊታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት እግዚአብሔር ህያው ተስፋ እና የዘለአለም ህይወት ሰጥቶናል። 1ኛ ጴጥ 1፡ 3-12ን አንብብ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker