Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
42 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ሐ. ከኃጢያት እና ከኃጠያት ኃይል ጋር በተገናኘ እኛ ራሳችንን እንዴት መቁጠር አለብን? (ቁ 11-13)
4. በሁሉም ነገሮች ውስጥ ልንከተለው የሚገባን የክርስትና ሕይወት ማዕከል የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። ቆላስይስ 2፡1-10ን አንብብ።
ሀ. ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን “የእግዚአብሔር ምሥጢር” እርሱም የጥበብና የእውቀት ውድ ሃብት ሁሉ የሚገኘው በእርሱ ነው ብሎ የገለጸው ለምንድን ነው? (ቁጥር 3-4)
ለ. የቆላስያስ ክርስቲያኖች ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው ከተቀበሉ በኋላ ለክረስሰቶስ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ የሚሞግታቸው እንዴት ነው? (ቁ. 6-7)
ሐ. ቅዱሳን ራሳቸውን መጠበቅና መጠንቀቅ ያለባቸው ከምንድን ነው? (ቁ. 8)።
መ. ቁጥር 10 የክረስቶስን ማንነት (ፍፁም አምላክነትና ሰውነት) በተመለከተ እንዴት አድረጎ ይገልጠዋል?
5. አማኞች “በክርስቶስ” በተትረፈረፈ ሞገስና በረከቶች ተባርከዋል ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡3-14፡፡
ሀ. “በክርስቶስ” በመሆንዎ ምክኒያት ካገኙዋቸው በረከቶች በትንሹ አምስቱን ይዘርዝሩ።
i.
ii.
iii.
iv.
v.
ለ. ክርስቶስን ካመንን በኋላ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ ምን ስራን ይሰራል (ቁ. 13-14) አንብቡ? ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ ወደ እኛ ሊመጣ ካለው በረከት ጋር ያለው ዝምድናና ግንኙነት ምንድን ነው?
6. በአንድ ወቅት ከእግዚአብሄር ርቀን የነበርን እኛ አሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን በክርስቶስ ደም ቀርበናል። ኤፌሶን 2፡13-22 አንብቡ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker