Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
44 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
በመሆኑም እኛ ለሠራነው ብዙ ዓመፃዎና ኃጢአቶች (የእግዚአብሄር ትዕዛዛት በመጣስ) ቅጣት ይመጣብናል ብለን አንፈራም። እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካኝነት ከእርሱ ጋር ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆነ ደረጃ እና ህብረትን(ግንኙነት) ሰጥቶናል፤ እናም በክርስቶስ እጅግ ብዙ፣ አስደናቂ ፣ ዘለአለማዊ በረከቶችን እና የተትረፈረፉ ፀጋዎችን በመስጠት ባርኮናል። ከተቀበልናቸው እጅግ ብዙ ድንቅ ስጦታዎች አንዱና እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነው የእኛ የክርስቶስ አካል በሆነችው ቤተክረስቲያን ያገኘነው አዲስ አባልነት እና ስፍራ ነው። እግዚአብሔር ሁላችንንም በክርስቶስ አስተሳስሮናል እናም አሁን ከሌሎች አማኞች ሁሉ ጋር እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ አብረን እንድንኖርና እንደ ክርስቶስ አካል (ሮሜ 12፡4- 8) እና እንደ መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ (1 ቆሮ. 3፡ 16-17) እንድናድግ ልዩ ዕድል መብት እና ኃላፊነት ሰጥቶናል (1 ዮሐንስ 3፡1-3)። የሰው የአካል ክፍል እግር ወይም እጅ ከሰውነት ተለይቶ ለብቻው መኖርና መስራት እንደማይችል ሁሉ አንዲሁ እኛም የክርስትና ሕይወታችንን በግላችን ተነጥለን እንድንኖር እግዚአበሄር አልሰራንም። በፍፁም! ሁሉም የአካል ክፍሎች እርስ በእርስ ለማደግ እና ለመጎልበስ እንዲሁም የተሰጠንን ስራ ለማከናወን እና ለመፈጸም እንዲሁ አስፈላጊ ናቸው። እያንዳንዳቸው አማኞች ራሱን/ራሷን እንደሰማያዊ ዜጋ ማለትም ከክረስቶስ ጋር የተባበሩና በሕያው ተስፋም እርሱን የሚጠባበቁ አማኞች እንደሆኑ የተረዱ ናቸው። በዚህ ሁኔታ እያንዳንዱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሄር መንግስት ኤምባሲ፤ የሰማያዊው ዓለም መገለጫ አማኞችም ከሌላው ክርስቲያኖች ጋር ለማደግ፣ ለማምለክ እና ጌታን ለማገልገል የሚሰበሰቡበት ህብረት አድርጎ መረዳት ይቻላል። ከመጀመሪያው አንስቶ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ ህዝብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጸውና በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ለዓመታት ሲያስተምራቸው የቆዩትን ዋና ዋና አስተምህሮዎችና ልምምዶችን ለይቶ በማወቅ ለማስተማርና እና ለመከላከል እንዲችሉ መርቷቸዋል። ይህ ታላቅ ልምምድ፤ ወሳኝ የሥነ-መለኮት እና ልምምዶች፤ ክረስቶስ ጌታና መሲሁ እንደሆነ በሚያውጁ በዓለም ዙሪያ ባሉ በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ውስጥ ታምኗል ተሰብዃል ደግሞም ታውጇል። የምናገኛው መግባት ማለትም እኛ ባመንን ቅፅበት በክረስቶስ አካል በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖረን አባልነት ከእውነተኛ መጋቢዎችና እና ከእውነተኛ ሰዎች ጋር ሆነን የምናድግበት የምናመልክበትና የምናገለግልበት አባልነት ነው።
የሚከተሉት ተጨማሪ ሃሳቦች ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውና ለማጥናትና ለማሰላሰል የሚረዱ ተጨማሪ ሃሳቦች ናቸው
ተጨማሪ ቅፅል
በክርስቶስ ውስጥ ያገኘናቸው ሠላሳ ሦስት በለከቶቸ (ተጨማሪ አባሪ 14) በክርስቶስ (ተጨማሪ አባሪ 8) የናዝሬቱ ኢየሱስ-የመጪው ጊዜ ህልውና (ተጨማሪ አባሪ 4) ወደ ኋላ መለስ በማለት ወደ ፊት መጓዝ: ወደ ታላቅ ታዋቂነት የወንጌል ምርምር (ተጨማሪ አባሪ 16) የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ (ተጨማሪ አባሪ 24 እና 25) የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ (ተጨማሪ አባሪ 26)
በክርስቶስ ሁሉንም መንፈሳዊ በረከት አግኝተናል (ኤፌሶን 1:3)
ቁልፍ መርሆች
Made with FlippingBook - Online magazine maker