Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 3 የምናገኘው መግቢያ • 45
ከዚህ በታች የተመለከቱትን የማሳያ ፅሁፎችን ያንብቡና በፅሁፎቹ ላይ በመመርኮዝ የሚነሱትን ሃሳቦችና ድምዳሜዎች ላይ ያሎትን ምልከታና ዕይታ ያብራሩ እና መልስ ይስጡ።
የናሙና ጥናቶች
1. “እኔ ለመጠመቅ አያስፈልገኝም, አይደል? አንድ ጊዜ አድርጌዋለሁ።” በቅርቡ ጌታን የተቀበለችት አንዲት እህት ከመጋቢዋ ጋር ሁለተኛ ወይም ዳግመኛ ስልመጠመቅና አለመጠመቅ ትወያይ ነበር ምክንያቱም እሷ በልጅነቷ ተጠምቃ ነበርና። እርግጥ ነው ከብዙ አመት በፊት ስትጠመቅ ስለጥምቀቱም ሆነ ሕይወቷን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስለመስጠቷ ምንም መረዳቱም ሆነ እውቀቱ ምንም ፍንጭ አልነበራትም - የ12 አመት ልጅ ነበረችና፤ እና አሁን ግን በልጅነቷ በተጠመቀች ጊዜ በክርስቶስ ምንም እምነት እንዳልነበራት እርግጠኛ ናት። እና አሁን ለዚህች አዲስ አማኝ ምን ትመክሯታላችሁ - እንደገና ለመጠመቅ መፈለግ አለባት፤ በርግጥ ግን በዚህ ጊዜ ጥምቀቱ ምን ማለት እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ ለማመን እና ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታና አዳኝ ስለመሆኑ ግልፅ የሆነ እምነትና መሰጠት አላት? 2. ጓደኞቼ የእግዚአብሔርን በረከቶች ለመቀበል “በአዎንታዊነት ስሙን ማወጅና የራሴ እንደሆነ መቁጠር ይገባኛል” ይላሉ። ይህ ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ጋር እንዴት ይስማማል? አንድ አዲስ ወደጌታ የመጣች አማኝ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን በረከቶች አካላዊ ፍላጎቶቻችንን ለመሙላት ከበሽታ ለመፈውስ እና በመከራ ውስጥ ሞገስን ለማግኘት “ማወጅንና የራስ እንደሆነ መቁጠርን” አለብን ብለው በሚያበረታቱና በሚለማመዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተገኝታ ትካፈል ነበር። በዚህ ልምምድ ውስጥ የሚሳተፉ አማኞች በአብዛኛው ትኩረት የሚደረጉት በአካላዊ በረከቶች (ገንዘብ ጤና እና ንብረት) ላይ ነው እናም “በክርስቶስ ውስጥ” ስላሉና ስላገኘናቸው እውነተኛ መንፈሳዊ በረከቶቻችን አነስተኛ ትኩረት ይሰጣሉ። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በክርስቶስ ሁሉንም መንፈሳዊ በረከቶች እንዳገኘን በተነገረው የበረከት ቃልና (ለምሳሌ ኤፌ 1፡3) በብዙ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ የእግዚአብሔርን በረከትና ሞገስን በሕይወታቸው አካላዊና ቁሳዊ ነገሮች (ማለትም “በጤና እና የሀብት” ጉዳዮች ላይ) በመጥቀስ ሰፊ አጽንዖት በሚሰጡ የእምነት ተቋማትና ልምምዶች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት ልንረዳ ይገባናል? በእነዚህ ሁለት የእግዚአብሔር የበረከት ግዛቶች እና እንክብካቤዎች መካከል ያለውን አፅናዖት በሚገባ እንዴት ልንገነዘብ እንችላለን? 3. የሚያስፈልገኝን መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ከአንዲት የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ማግኘት አልችልም። በከተማችን ዙሪያ ካሉ የተለያዩ አብያተ-ክርስቲያናት የምፈልገውን ማግኘት እችላለሁ - አምልኮን ከ”ሀ” ቤተ ክርስቲያን፤ ከቤተ ክርስቲያን “ለ” ደግሞ ትምህረትን እንዲሁም ከቤተክረስቲያን “ሐ” የወንድሞች ህብረትን ማግኘት እችላለሁ። ስለዚህ ይህንን ባደርግ ችግር አለው? “የቤተክርስትያን-ዘለላ” ወይም “መንፈሳዊ ዘላልነት” ዛሬ በብዙ የክርስቶስ ተከታዮች የተለመደ ክስተት ነው። በርካታ ክርስቲያኖች በአንድ የተወሰነ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለማደግ እና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ማግኘት እንደማይችሉ በማመን በተለያዩ ቤተክርስቲያናት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሚካሄዱትን የተለያዩ ትምህርቶችን ፕሮግራሞችን ወይም የአምልኮ ኮንፍረንሶችን ለማግኘት በመዞር ቤተክርስቲያንን ወደ “ቤተ-ክርስቲያን ፑልነት” ለውጠዋታል። የምንኖረው ሁሉም ሰው ከተለያዩ ምንጮች “የሚፈልውን ማግኘት አለበት” በሚል መፈክር በተቃኘ ዓለም ውስጥ በመሆኑ አማኞችም ወደ ቤተ-ክርስቲያን ሲመጡ ተመሳሳይ አመክንዮ/ሎጂክ/ ተግባራዊ ያደርጋሉ። ይህም በተለምዶ እንደሚጠቀሰው አንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የአንድ አማካይ ክርስቲያንን ወይም የክርስቲያን ቤተሰብን ፍላጎቶችን ለማሟላት እትችልም ከሚለው እሳቤ የመነጨ ሐሳብ ነው። ይህንን የሚቀበሉ ሰዎች ከአንድ ጉባኤ ጋር አምልኮን በሌላ ጉባኤ ውስጥ ደግሞ ስብከትን በማዳመጥ እና በትንሽ የተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ ቡድን ውስጥ ከሌላው ጋር ህብረትን በማድረግ የተለያ ልምዶችንና ጥቅሞችን ሊያገኙ እንደሚችሉ ይከራከራሉ። በመሆኑም ጤናማ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄር መንግሥት ኤምባሲ ከሆነ ታዲያ
Made with FlippingBook - Online magazine maker