Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
46 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ወደ ክርስቲያናዊ ጉልምስና በምናደርገው ጉዞ ውስጥ “የቤተ ክርስቲያንትን ዘላንነ” ለምን የህይታችን መርህ አናደርገው?
በዚህ ሳምንት ውስጥ አሁን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ እንደተጠመቀ አማኝ ያላችሁን በረከቶችንና ውርሶችን የሚናገሩትን የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችነ በየዕለቱ ከልሷቸው አሰላስሏቸውም። ምን እንደሆኑ በግልጽ ካለተረዳችኋቸው እና ለክረስቲያን ህይወታችሁ አስፈላጊነታቸውን እና ያላቸውን ጠቀሜታዎች ካልተገነዘባችሁ በኑሮአችሁ ልታንጸባርቋቸውም ሆነ ልታውጇቸው አትችሉም! በመሆኖም በአባሪው ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን “በክርስቶስ ያሉን 33 በረከቶችን” አጥኑ እናም እነዚህን እውነቶች በጥልቀት ተረዱ። እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምንነት በበለጠ በተረዳችሁ መጠን ከራሳችሁ ውስጣዊ ማንነታችሁ ጋር ታዋዋህዷቸዋላችሁ እንዲሁም የእናንተ አካል እንዲሆኑ ማድረግ ትችላላችሁ፤ እናም የጸሎታችሁ ክፍል በመሆን ለእግዚአብሄር ምስጋናን ለማቅረብና ልመናችሁን ከምስጋና ጋር ለመስታወቅ ይረዳችኋል። እስካሁን ድረስ በአከባቢያችሁ ከሚገኝ የአንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን (ማለቴ የእግዚአብሔር መንግሥት ኤምባሲ!) አባል ካለሆናችሁ በሚቀጥት ቀናቶችና ሳምንታት ጌታ ወደ ትክክለኛዋ አጥቢያ ቤተክርስቲያን (ቤተክረስቲያኖች አላልኩም!) እንዲመራችሁ ጠይቁት። ይህም በመልካምና ጤናማ መጋቢ መንፈሳዊ ስልጣን ስር መሆን፡ ከሌሎች ለጌታ ከተሰጡ አማኞች ጋር ህብረት ማድረግ እና እግዚአበሄር የሰጣችሁን ስጦታዎችና ክህሎቶች ሌሎችን ለማገልገልና ለማነጽ መጠቀም የምትችሉባቸውን መንገዶች ለማግኘት ይረዳችኋል። ዋናው ቁልፍ ነገር ወደ ጉባአኤዎቹ ወይም የአምልኮስፍራዎቹ መሄድና አባል ብቻ ለመሆን አይደለም ነገር ግን አባል መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ህያው የአካሉ ክፍል በመሆን ከሌሎች ጋር ህብረትን ለማድረግ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ መጀመሪያ ላይ አስቸጋሪ ወይም የብቸኝነት ስሜት ቢሰማችሁ ተስፋ አትቁረጡ፤ በፅናት ተሳትፎአችሁን በመቀጠል እና በጌታ በመታመን እግዚአበሄር ጥሩ የወዳጅነት ህብረትን እና የአገልግሎቶችን በር እንዲከፍትላችሁ በእምነት ተመላለሱ። እግዚአብሔር ይመራችኋል እናም ትዕግስት ካለ ብዙ ፍሬዎችን ታፈራላችሁ (ገላ 6.7-9)።
ተዛምዶ
እኔ በጊታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኜ የተጠመቅኩ ስለሆነ በሁሉም ቦታ እና በየትኛውም ጊዜ ካሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ጋር ሁሉንም የክርስቶስን በረከቶች፣ ክብር ፣ ተስፋ እና መከራን ሁሉ እካፈላለሁ።
ማረጋገጫ
በ 1880ዎቹ ታዋቂው ብሔራዊ የቤዝ ቦል ተጫዋች የነበረው ቢሊ ሰንዴይ በ20ኛዉ ክፈለዘመን የመጀመሪያዎቹ ሁለት አሥርት ዓመታት ታላቅ ተደማጭነት እና ከፍተኛ ተጸዕኖ ፈጣሪ ወንጌላዊ ነበረ። የእሁድ ሰንበት ስብከት ስብሰባዎቹና ጉባኤዎቹን በአንዳንድ የአሜሪካ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ በርካታ ሰዎችን አስደምመውና ወደጊታ አምጠተው ነበር። ቢሊ ሰንዴይ በአንድ ታዋቂ ስብከቱ ውስጥ የጊታ ኢየሱስሁሉን ክርስቶስ ልዕልና እና የበላይነት ከፍ በሚያደርግ ሁኔታ በዚህ ግጥም ለእርሱ ክብርን ሰጥቶ ነበር። *
ፀሎት
* አንዳንድ ምንጮች “ያልታወቀ ደራሲ” ይላሉ አንድ ድረ-ገጽ ደግሞ በሴይንት ፓትሪክ እንደተገለፀ አድረጎ ያቀርበዋል ነገር ግን አብዛኞቹ ደግሞ ቢል ሰንዴይ እንዳለው ያምናሉ።
ክርስቶስ የእኔ ሁለንተና
ክርስቶስ ለታመመ ፡ ክርስቶስ ለጤንነት ክርስቶስ ለድህነት፡ ክርስቶስ ለሀብት ክርስቶስ ለደስታ፡ ክርስቶስ ለሐዘን ክርስቶስ ለዛሬና ክርስቶስ ለነገ፤
Made with FlippingBook - Online magazine maker