Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

48 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና ዘለአለማዊው አምላክ ሆይ ከልጅህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። በክርስቶስ በኩል ላገኘኋቸው ብዙ ድንቅ ስጦታዎች እና በረከቶች ሁሉ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለለሁ፤ በተለይ ደግሞ ከህዝብህ ጋር ማለትም የክርስቶስ አካል ከሆነችው ቤተክርስቲያንህ ውስጥ አባል ስላረከኝና በዚያም ስላገኘኋቸው ታላላቅ በረከቶች እጅግ በጣም አመሰግንሃለሁ። በእምነት ከሌሎች አማኞች ጋር አንድ አንድሆንና በአካሉ ውስጥ ማለትም ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ቤተሰብ እንደ ኢየሱስ አካልና እንደ መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመኖር፣ ለማደግ እና ለማገልገል ክብርን እና ሀላፊነትን ስለሰጠኸኝ እጅግ በጣም አመሰግንሃለሁ። አንተን ማወቅ ማለት ህዝብህን መውደድ ማለት ነው፣ ምክንያቱም አንተ ፍቅር ነህና። ጌታ ሆይ አንተ የእኔን ክርስቲያናዊ ህይወትን እና መልካሙን የእምነት ገድል ብቻዬን እንድኖርና እንድጋደል አላቀድክም ይህንንም እንደማትፈልግ አውቃለሁ። አንተ ወደፈቀድከው አጥቢያ ቤተክርስቲያን እንድትመራኝና በዚያም በአባልነት በአንድ መጋቢ ስር በመሆን መንፈሳዊ ከለላን እንዳገኝ፣ ነፍሴ እንድጠብቃት እናም ከሌሎች ቅዱሳን- ከእነዚህ አብረውኝ መልካሙን የእምነት ገድል ከሚጋደሉ ተዋጊዎች ጋር በመሆን- የአንተን ፍቅር ለጎረቤቶቻችንና ለሰው ልጆች ሁሉ እንድንመሰክር እና የሰጠኸኝን ፀጋ ሌሎችን ለማነፅና እንደጠቀምበት እለምንሃለሁ። ስለ ቤተክርስቲያንህ እጅግ አድርጌ እመሰግንሀለሁ። ለህዝብህ ፍሬያማ እና ደግ ሰው አድርገኝ፤ በመካከላቸው ኅብረትን ሳደርግ በእውነተኛ ህይወት እንዳድግ እርዳኝ ስለክርስቶስ ስትል ስማኝ አሜን።

የልብ ጩኸት ለጌታ

At www.tumi.org/sacredroots, we have a section dedicated to additional written and video resources.

ለተጨማሪ ጥናት ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ

John Eldridge. Epic: The Story God Is Telling . Thomas Nelson, Inc., Nashville, TN: 2004.

በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ የተቀበልነው ስጦታ የሚለውንና የሚከተሉትን ርዕሶች እንመለከታለን፡፡ 1. መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን አማኝ አካሉን ለማገልገል ስጦታ ይሰጣል 2. ስጦታችንን እንድንለማመድ በክርስቶስ ነፃነት ተሰጥቶናል 3. በብስለት እና በአንድነት አብረን ለማደግ እንድንችል ኃይልን እናገኛለን.

ለሚቀጥለው ክፍለጊዜ

ኤፌሶን 1፡3

የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት

1. እግዚአበሄር ለሠራው ስራ ሁሉ ምስጋናን የሚገልጽ ግጥም ወይም ደብዳቤ ጻፍ 2. በመጽሃፉ መጨረሻ ያለውን የኒቂያውን የሃይማኖት መግለጫ አንብቡና በኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ውስት የተገለጹትን ቁልፍ እውነቶች ጠቅለል አድርገን ግለጽ 3. አንድ በእምነት የጎለመሰ አማኝ በቤተክርስቲያን ውስጥ አግኝና ቅዱሳን የክርስትና ሕይወት ቤተክርስቲያን እንዴት መኖር እንችል እንደረዱትና ብቻውን ለመሥራት የማይቻልን ነገር እንዴት አማኞች እንዳገዙት ጠይቀው/ጠይቃት

የቤት ስራ

Made with FlippingBook - Online magazine maker