Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
የትምህርት 4 ተቀበልነው ስጦታ: - በመልካሙ የእምነት ተጋድሎ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሚና
እግዚአብሄር ለቤተክርስቲያን ስጦታዎችን ማለትም አንዳንዶችን ሐዋርያት ነቢያት ወንጌላውያን* ሌሎቹም እረኞችና* አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ዓላማውም አማኞችን ሁሉ ለአገልግሎት ለማነጽና የክርስቶስን አካል ለመገንባት ነው። የእግዚአብሄር ሐሳብ እኛ ሁላችንም እንደ አማኞች የእምነትን አንድነት ለመጠበቅ እና ስለ እግዚአብሔር ልጅ ስለ ክርስቶስ የጠለቀ እውቀት እንዲኖረን በመንፍሳዊ ህይውታችንም የበሰልን እንድንሆንና ወደ ክርስቶስ ሙላት መጠን ልክ እንድንደረስ ነው። እግዚአብሄር በእነዚያ ምግባረ ብልሹ በሆኑ ሰዎችና እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሚኖሩ በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን እንደ ሕፃናት እንድንሆን አይፈልግም። ይልቁንም እግዚአበሄር እውነትን በፍቅር መናገርን እንድንማርና በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንድናድግ ይፈልጋል። በዚህ ክፍለ ጊዜ መገባደጃ ላይ የተቀበልነው ስጦታ የሚለውን ሃሳብ የሚከተሉትን ዋና ዋና ሃሳቦችን በመረዳትና በማመን ይጨብጣሉ። • መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ይኖራል፡ አካሉንም ለማገልገል የሚያስችልን ልዩ ስጦታን ለእያንዳንዱን አማኝ ይሰጣል፡፡ • የተሰጡንን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን እርሱ በሚሰጠን ዕድሎች ሁሉ ለማገልገል እድንችል በክርስቶስ ኢየሱስ ነጻነት ተሰጥቶናል። • በመንፈስ ቅዱስ አመራር ስጦታዎች እና ብርታት አማካኝነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ሌሎች አማኞች ጋር በጠንካራ ጥምረት ለመኖርና በብስለትና በህብረት ለማድግ በቂ ጉልበት እናገኛለን። የጳውሎስ መልዕክት ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡11-15
የትምህርቱ ዓላማ
ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32.8)
የመግቢ ጸሎትያ- ለጥበብ
* ወንጌላውያን የሚለው ለጠፉት ሰዎች ወንጌልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተላለፍ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን የተሰጣቸውን ያመለክታል። ሁሉም አማኞች ወንጌልን እንዲካፈሉ ቢታዘዙም አንዳንዶቹ በዚህ ረገድ የበለጠ ተሰጥዖ እና ስጦታ ያላቸው እና የክርስቶስን አካል ለማነፅ የሚያገለግሉና የሚረዱ ናቸው። * መጋቢዎች መንጋውን ለመንከባከብ የተመደቡ “እረኞች” ናቸው፤ ማለትም በአከባቢ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ በማገልገል የክርስቶስን መንጋ የሚመግቡ ናቸው። መጋቢዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎቻቸው በአምላካዊ ምክሮቻችው እና ማበረታታት በጎችን ከአደጋዎች ይጠብቃሉ እንዲሁም መንጋው በማኅበረሰባቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲሰሩ ያስተምራቸዋል ይመሯቸዋልም።
49
Made with FlippingBook - Online magazine maker