Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

50 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ።

አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።

በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።

1. “ሐዋርያትና ሌሎች ቁልፍ መሪዎች በሙሉ አሁን የሉም?” የኤፌሶን መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠና አንድ አዲስ ክርስቲያን አባል ኤፌሶን 4:11-15ን አነበበና እንዲህ ብሎ ጠየቀ “ሐዋርያትና ነቢያት እንዲሁም እነዚህን የመሳሰሉ ስጦታዎች ያላቸው ሰዎች አሁን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደሌሉ አስባለሁ። ታዲያ ይህ ክፍል ምን ማለት ነው? ዛሬ እንደ ሐዋርያ እና ነብያቶች የሚሠሩ/የሚያገለግሉ ሰዎች አሉን? እናስ ከሆነ የት ነው ያሉት? ጳውሎስ የሚናገረውን እንደተረዳሁት እነዚህ አገልጋዮች እኛ ሌሎች ሰዎችን እንዴት ማገልገል እንዳለብነ ለመርዳት እግዚአብሔር የሰጠን ስጦታዎች ናቸው። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም አሪፍ ነው! “ ይህ ክፍል ለእኛ ዛሬ ምን የሚለን ይመስላችኋል - ዛሬም እግዚአብሄር እንደነዚህ ዓይነት ሥጦታ ያላቸውን መሪዎች ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ ውጤታማ አገልጋዮች እንዲሆኑ ለማነጽ ስጦታዎቹን በማቅረብ እየቀጠለ ይመስላችሃል? 2. “ፓስተሬን ማን እንደሆን እንኳ አላውቀውም” በጎልማሶች የጸሎት ስብስብ ውስጥ በፓስተሩ ስልጣን እና ስልጠና ሥር የመሆንን አስፈላጊነት በተመለከተ የሚዳሥ ሃሳብ መጣ። ይህንን የሰማ አንድ ሰው እንዲህ አለ “አዎ እግዚአብሔር ከስህተት አሰራሮችና ከመንፈሳዊ አደጋዎች ሊያስመልጡንና ሊመግቡን ፓስተሮችን ሰጥቶናል። እነርሱ እኛን እንደ ክርስቶስ በጎች ለመርዳት በሚገባ እንዲመግቡን እና ብርቱ አገልግሎት ለመስጠት እንድንችል ዝግጁ እንድንሆን ከጌታ ዘንድ ስልጣን የተሰጣቸው የእግዚአብሔር እረኞች ናቸው። አንድ አዲስ ክርስቲያን እንዲህ አለ “የምትናገሩትን እሰማለሁ ነገር ግን በርግጠኝነት ለመናገር በዚህ ዙሪያ ሃሳቤን በሙላት መናገር አልችልም ምክኒያቱም መጋቢዬን ያናገረኩት አንዴ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው (ከረጅም ጊዜ በፊት ወደ ቤተክርስቲያን እንደመጣሁ አካባቢ ነበር)። እውነቱን ለመናገር መጋቢዬ ማን እንደሆነ አላውቅም።እሱን የማላውቀው ከሆነ እንዴት ነው ሊጠብቀኝ እና እረኛዬ ሊሆን የሚችለው? “ለዚህ አዲስ አማኝ ምን አይነት ምክር ይሰጡታል? እሱ ከመጋቢው ጋር ስላለው የእግዚአበሄር ሃሳብ ምን እንደሆነ ያምናሉ? 3. “በእርግጠኝነት መንፈስ ቅዱስ እንዳላችሁ እንዴት ታውቃላችሁ?” አንዲት ወጣት ክርስቲያን በአውቶብስ ላይ ስትጓዝ “የጴንጤቆስጤ” ክርስቲያን ነኝ ብሎ ስለ ልምምዱና ስለነገራት ነገር ያደርጉት ውይይት ረብሿትና አዝና ነበር። ይህ ሰው መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዳለባትና እርሱም “የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት” እንድሆነእና በተጥመቀችምጊዜ በአዲሰ ቋንቋ ወይም

ግንኙነት/ተዛምዶ

Made with FlippingBook - Online magazine maker