Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

የትምህርት 4 ተቀበልነው ስጦታ: - • 51

በልሳን በመናገር* እንደሚገለጥ ነገራት። ወጣቷ እህትም እንዲህ አለችው “ባለፈው ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተምሬአለሁ ንስሐ የገባና በጊታ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሰው ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ የታተመ እና በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ እንደሚኖር ተምሬያለሁ። በተጨማሪም ሌሎች ክርስቲያኖችን በክርስቶስ አካል ውስጥ ማገልገል እንዲችሉ ስጦታዎች ሁሉ እንደሚሰጥ እና በልሳናት መናገርም ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ እንደሆን ተምሪአለሁ-ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ክርስቲያን እያንዳንዱን ስጦታዎች ሊኖራቸው ይገባል? እንዴት ይሄ ሊሰራ ይችላል? “ ይህች እህት ስለ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ ለማወቅ ፈልጋለች - ይህንን በይበልጥ ለመረዳት እንዴት መማር ይኖርባታል? ባለፈው ክፍለ ጊዜ (የምናገኘው መግቢያ ) እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን በክርስቶስ እንደ ተጠመቅን እና በክርስቶስ በርካታ በረከቶችን እንደወረስን ተምረናል። አሁን መደግሞ መጽሃፍ ቅዱስ ስለመንፈስ ቅዱስ በአማኞች ህይወት ውስጥ ስላለው ሥራ እና በረከቶቹ እንዲሁም እርሱ እኛን ለማገዝ እና ለማበረታት እንዲያግዙን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እና ችሎታዎች እንዴት እንደሚሰጠንና በዚህም በተለየ የጌታ ታሪክ ውስጥ ማለትም መልካሙን የእመነት ገድል ለመጋደል ባለን ተሳትፎ ውስጥ ያለውን ድረሻ እንመለከታለን። መንፈስ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ መንግሥቱን ለመመሥረት በሚመለስበት ጊዜ እኛ ክርስቲያኖች የምንቀበለው የወደፊቱ ውርስ መቀበያ (የርስታችን መያዣ ) ነው። መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን አማኝ በአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሌሎችን ማለትም የክርስቶስ አካላት ለማነጽ (ለመገንባት) የሚያስችል መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጣቸዋል። መንፈስ ቅዱስ የመጣው በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ለመኖር ነው። ማንንም አይተውም ማንንምም አያገለም ምክንያቱም የክርስቶስ አካል በሙሉ የአካል ክፍሎች ተሳትፎን እና አስተዋጽኦን ስለሚፈልግ ማንም አልተገለለም አይገለልምም። በእርሱ ጸጋ እግዚአብሔር ከኃጢአት ከጥፋተኝነት እና ከኩነኔ ምህረትንና ነጻነትን ይሰጠናል እናም ሌሎችን በክርስቶስ ስም በድፍረት እና በነጻነት ማገልገል እንድንችል አቅምን ይሰጠናል። በእግዚአብሔር ቃል (ስነ መለኮት) ላይ ስናሰላስል ስሙን በቃሉ እና በጌታ እራት (አምልኮ) ከፍ ከፍ ስናርግ በመንፈሳዊ ሥነ-ስርዓቶች (ደቀመዝሙርነት) ውስጥ ስንጓዝ እና መልካሙን የምስራችን ቃል ቅዱሱን ወንጌል በቃልና በተግባር ስንመሰክረው (ምስክርነት) መንፈሳዊ ዕድገትን ይሰጠናል። እኛ እግዚአብሔርን የማምለክ ችሎታችን እየጨመረ ሲሄድ እና ይህን ውጊያ በመዋጋት ስንቀጥል በእምነታችን እንጠነክራለን ሌሎች አማኞችን ማስታጠቅ እንችላለን። ብዙ አማኞች ወደ መንፈሳዊ ጉልምስና ሲያደጉ በቤተክርስቲያን ውስጥ አንድነትና ህብረት ይጠነክራል፤ ይህም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ደስ የሚያሰኝ ነው።

ጭብጥ

* በልሳናት መናገር - ቤተክርስቲያ በመንፈስ ቅዱስ መምጣት በተወለደች ጊዜ (ሐዋ. 2) አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ አማካኝነት እነሱ በተለምዶ ሊናገሩባቸው ከሚችሉት ቋንቋዎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ለመናገር የሚያስችል ስጦታዎችን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ተቀብለዋል። ይህ ስጦታ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አማኞችን ለማነጽ እንደሚጠቅም ተጠቅሷል (1 ቆሮ 12፡ 1-31) በሌላ አጋጣሚ ደግሞ አዳዲስ አማኞች ይህ ያልተማሩበትን ቋንቋ መናገር የሚችሉበትን ችሎታ ክርስቶስን በእምነት በተቀበሉ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ( ለምሳሌ ሐዋ. 10.44-46)። ዛሬ በአንዳንድ አብያተክርስቲያናት ዘንድ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከዚህ በፊት በማያውቁት ቋንቋ የመናገር ስጦታን መቀበል አለበት የሚለውን አካሄድ አጽንዎት ሲሰጡ ሌሎች አብያተ-ክርስቲያናት ይሄ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው እግዚአብሄር ይህንን ስጦታ ለተወሰኑ ሰዎች ይሰጣል እንጂ ለሁሉም አይሰጥም ብለው ሲያምኑ፤ ሌሎች ደግሞ በልሳናት መናገር ለጥንቷ ቤተክርስቲያን ብቻ እንደሆነና ይህ ስጦታ ዛሬም ለአማኞች እንዳልተሰጠ ያምናሉ።

Made with FlippingBook - Online magazine maker