Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
የትምህርት 4 ተቀበልነው ስጦታ: - • 53
ሀ. አንድ ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ድነትን አግኝቶ መንፈስ ቅዱስ ግን ላይኖረው ይችላልን? (ቁ 9-10)
ለ. በክረስቶስ ያመኑት እንዴት ከሞት ሊነሱ ይችላሉ? (ቁ .11)
ሐ. የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እንዴት እናውቃለን? (ቁ 14-15)
መ. እኛ የእግዚአብሄር መሆናችንን እንድንረዳ መንፈስ ቅዱስ እንዴት ሊረዳን ይችላል? (ቁ 16-17)
3. እግዚአብሄር አብ የክርስቶስ አንድ አካል ለማነጽ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የመንፈስ ስጦታዎችን ሰጥቶናል፡፡ ሮሜ 12.3-8ን ያንብቡና በዚህ ምንባብ የተጠቀሱትን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዘርዝሩ
ሀ.
ለ.
ሐ.
መ.
ሠ.
4. እግዚአብሄር የተለያዩ ስጦታዎችን፣ አገልግሎቶችን እና አሰራሮችን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሰጥቶናል፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ አባል ራሱንና ክርስቲያኖችን ለማነፅ የሚያገለግል የተለየ ልዩ ስጦታ ይሰጣቸዋል። 1 ቆሮንቶስ 12፡4-11ን ያንብቡና፤ የተሻለውን መልስ ይምረጡ
ሀ. መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሰጡት ለአማኞች ጥሩ ጥሩ ክብር ወይም በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡
ለ. መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሰጡት አካሉን ለማነጽ ለጋራ ጥቅም እንዲውሉ ነው።
ሐ. አማኞች የፈለጉትን ስጦታዎች እንዲኖራቸው መምረጥ ይችላሉ።
መ. አንዳንድ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታ ፈጽሞ አይቀበሉም።
5. አማኞች የእግዚአብሔርን ድንቅ የጸጋ ስጦታዎች ጌታ እግዚአብሄርን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚያስከብር መንገድ በመጠቀም ባለአደራዎች ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1 ጴጥሮስ 4፡7-11ን ያንብቡና ሐረጉን ከተጓዳኙ እውነት ጋር ያዛምዱት:
Made with FlippingBook - Online magazine maker