Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
56 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
አብ እያንዳንዱን አማኝ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማካፈል ለህዝቡ መንፈሳዊ ጥንካሬን እና ሕዝቡንም ለማነጽ ዋስትናን ሰጥቷል። ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጡ የተለያዩ ስጦታዎች፤ አገልግሎቶች እና አሰራሮቸ ቢኖሩም፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ሌሎች ክርስቲያኖችን ለመገንባት፤ ለማነጽና ለመርዳት ልዩ ስጦታዎችን ሰጥቷቸዋል። እያንዳንዱ አማኝ ስጦታዎች አሏቸው እናም እያንዳንዱ ሰው የክርስቶስን አካል ጠንካራ እና ጎልማሳ እንዲሆኑ ለማድረግ ስጦታቸውን እንዲጠቀሙበት ጥሪ ተሰጥቷቸዋል። እኛ የእግዚአብሔርን ድንቅ የጸጋ ስጦታዎች በባለአደራነት እንድንጠቀም ተጠርተናል፤ ይህም ጌታ እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዲከበር ለእርሱ ክብር በመጠቀም ነው። በመንፈስ ቅዱስ በነጻነት ልንኖር፤ ለቀድሞው ስጋዊ ባሕሪያችን ሳይሆን ይልቁንም የመንፈስ ፍሬ የሚገልጥብን የመንፈሱ ማስተላለፊያ አሸንዳ እንድንሆን ተጠርተናል። የሚጠበቅብን ለእርሱ ብቻ መሰጠት እና በሁሉም ነገሮች እርሱን መከተል ብቻ ነው።
ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ነገሮች ለማጥናትና ለማሰላሰል እንድትችሉ የሚከተሉት ክፍሎች መመልከት ጠቃሚ ነው።
ተጨማሪ
በእርሱ ላይ መደገፌ ወይም ጥገኛ የመሆኔ መግለጫ-ነጻነት በክርስቶስ (ተጨማሪ 9) የናዝሬቱ ኢየሱስ-መጪውን ጊዜ አሁን መኖር (ተጨማሪ 4)
በዋሽንት በጡሩምባ እና በመለከት ተመሳሳይ ትንፋሽ ይነፋል ይሁን እንጂ የተለያዩ የሙዚቃ ቃና/ድምጽ እንደ የሙዚቃው መሳሪያ ዓይነት ይወጣል። በተመሳሳይም አንዱ መንፈስ በእኛ በእግዚአብሔር ልጆች ውስጥ ይሠራል ነገር ግን የተለያዩ ውጤቶች ይታያሉ በዚህም እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ባሕርይ እና ስብዕና መሠረት በእነርሱ ይከበራለ።
~ Sadhu Sandar Singh. Richard J. Foster and James Bryan Smith, Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups. Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993, p. 291.
ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። (ፊልጵስዩስ 2.13)
ቁልፍ መርህ
ከዚህ በታች በተመለከቱት ፅሁፎች ላይ በመመርኮዝ በሚከተሉት ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦች ላይ አስተያየትዎን አውዱን በመጠበቅ ያብራሩ እና መልስ ይስጡ።
የናሙና ጥናቶች
1. መንፈስ ቅዱስ ዳግም የተወለደን ክርስቲያንን ጥሎ መውጣት ወይም መሄድ ይችላልን? በየዘመናቱ እያንዳንዱ አማኝ ደህንነቱን የመጠራጠር ፈተናን ይጋፈጣል፣ አንዳንዴም መንፈስ ቅዱስም ትቶአቸው የሄደ እስከሚመስላቸው ድረስ ያስባሉ። አንዳንድ ትምህርቶችም ንስሃ የገባና በክርስቶስ ዳግም የተወለደ እና የታመነ ሰው ሆን ብሎ እግዚአብሔርን ባይታዘዝ እና ሃጢአትን ቢሰራ በክርስቶስ ያገኘውን ልጅነቱን ያጣዋል ብለው ያስተምራሉ። የሚከተሉትን መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ እና ለዚህ ጥያቄ መልስ ይስጡ: መንፈስ ቅዱስ ዳግም ከተወለድ ከክርስቲያንን ውስጥ ወጥቶ/ጥሎ ይሄዳልን?
Made with FlippingBook - Online magazine maker