Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

የትምህርት 4 ተቀበልነው ስጦታ: - • 57

ሀ. 1 ዮሐንስ 5.11-13

ለ. ኤፌሶን 1.13-14

ሐ. ሮሜ 8.31-39

2. አንድ ነገር ከእኔ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እያደገና እየጎለመሰ የሚሄድ ክርስቲያን አንዱ እና ዋነኛ ሆኖ የሚያሳስባቸው ጉዳይ የራሳቸው አስተሳሰ እና ስለ ራስን-የሚነገርን ንግግር መቆጣጠር ነው። ምንም እንኳን በክርስቶስ የዳንን ለእርሱ ብንሆንም ጠላት አሁንም ሃሳባችን ላይ በመድረስ ከጌታም ያልሆነና ለእኛም ጥቅም ሊሰጡን የማይችሉ ነገሮችን ሊጠቁመን እና እንዲጠቀሙብን ሊያደርግ ይችላል። ወደ አዕምሮአችን የሚመጡ ሁሉም ሀሳቦች በሙሉ ሁሉም ከጌታ ናቸው ብሎ መደምደም አይቻልም! ዲያቢሎስ ውሸታም እና አታላይ ነው (ዮሐ 8፡44) እናም እኛ ልናሸንፈው እንችላለን ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ (በእኛ ውስጥ እንዲኖር የተሰጠን) ከእርሱ የበለጠ ብርቱ ነውና (1 ኛ ዮሐ 4.4)! መጽሃፍ ቅዱስን በመረዳት ሰይጣንን መቃወም እና በአዕምሮአችን ውስጥ ሊመጡ የሚችሉትን ሀሳቦች እና የራስ-ንግግሮችን ባለመበቀል ወይም እምቢ በማለት (ሮሜ 12፡1-2, 2ቆሮ 10፡3-5) ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል እንችላለን። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያቢሎስ መፈተኑን የሚያሳየውን የመጽሃፍ ቅዱሰ ክፍሎችን ያንብቡና እና የዲያብሎስን ውሸት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዴት መልስ እንደሰጠ አስተውለው በዚህ አቅጣጫ የእሱን ምሳሌ መከተል ትችላላችሁ (ማቴ 4፡1-11)። 3. መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የመንፈስ ቅዱስን ሃሳብ ለመረዳት አስተማማኝና የላቀ መንገድ ከቅዱሰ ቃሉ ጋር በጥብቅ መዛመድ ነው። መጽሃፍ ቅዱስ ስለራሱ ሲመሰክር የእግዚአብሄር ቃል ከቶ በሰው ፈቃድ እንዳልመጣምና ይልቁንም ቅዱሳን ሰዎች በእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው እንድተናገሩ ይመሰክራል (2 ጴጥ 1,20-21; 2 ኛ ጢሞ 3.15-17)። መጽሐፍ ቅዱስ ሲሰበክ ስንሰማ፤ አንብበነው ስንረዳወ፤ የመጽሐፉን መልዕክት ለማስታወስ ስናጠና ስናሰላስለው እና በህይወታችን ስንለማመደው የመንፈስ ቅዱስን አዕምሮ(ሃሳብ) ማወቅ እንችላለን። ክርስትያን ሐሰትን/ውሸትን ለመዋጋት ከፍተኛ የሆነ የማጥቂያ መሳሪያው የእግዚአብሔር ቃል እርሱም “የመንፈስ ሰይፍ”(ኤፌ 6፡ 17) ተብሎ የተገለጠው ቅዱስ ቃሉ ነው። በየዕለቱ የምንሰማቸውን ሁሉንም ሃሳቦች በእግዚአብሄር ቃል መመዘን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው (1 ተሰ 59-21 ይመልከቱ)? እንደ አዲስና እያደገ እንደሚሄድ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ የሚያምን እያንዳንዱ አማኝ ስል መንፈስ ቅዱስ ስጦታ መረዳት አስፈላጊ ነው። “ከበዓሉም የመጨረሻ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ: የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። እንግዲህ ይህን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና “(ዮሐንስ 7.37-39)። እንደ አማኝ እስከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣትና መዋጀት እስኪሆን ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል (ኤፌ 1-13-14)። የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን እና ልጆቹ ሊያደርገን አንድያ ልጁን ላከው። አሁን እኛ የእርሱ ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን “አባ! አባ! “ብለን የምንጠራበትን የኢየሱስን መንፈስ ወደ ልቦቻችን ልኮልናል (ገላ 4-6)።

ማዛመድ

Made with FlippingBook - Online magazine maker