Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

58 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

ጌታ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በነፃነት እንድትኖር በእርሱ ብርታትና ጥንካሬ እንድትመላለስ እና በቃሉ እንድትረዳና እንድትባረክ ጠርቶሃል። እኛ ከክስ ከጥፋተኝነት እና ከኩነኔ ነፃ እንድንሆን ተጠርተናል። ከዚህ በኋላ በራሳችን መንገድ በመሄድ ራስ ወዳድና ኃጢአት-ተኮር መንገዶች መኖር እና ለዚያም መሰጠት የለብንም። ይልቁንም አዲስ የአስተሳሰብ ልምዶችን ማፍራት፣ አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን መክፈት እና ከሌሎች ጋር የመገናኘትን አዲስ መንገዶች መፍጠር እንችላለን። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ስለሚኖር የድሮውን ኃጢአተኛ ተፈጥሮአችንን ለመከተል ግዴታ የለብንም። ምርጫ አለን፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲሰራ በሚፈልጋቸው ነገሮች ወይም የድሮውን የኃጢያት ባህሪያት በመከተል መኖር ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ የመረጥነውን ምርጫ ውጤቱን ማጨዳችን አይቀርም (ገላ 6፡7-9)። ስለዚህም ሕይወትን ምረጥ! በመንፈስ እንጂ በሥጋ አትመላለስ። መንፈስ ቅዱስ እንዲያጠነክርህ ጠይቀው። በእሱ ቃል (በቅዱሳት መጻህፍት) ላይ ፀንተህና ከእርሱ ጋር በቋሚነት ህብረትን አድርግ። እርሱ እንድታደርገው እና እንድትፍጽመው የሚያዝህን ነገሮች ሁሉ ወዲያውኑ ታዘዝ። በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለህን ህብረት የበለጠ እየጨመረ በሄደ ቁጥር እሱን ለመስማት፣ ለመታዘዝ እና የእርሱን መሪነት ለመከተል ቀላል ይሆንልሃል።

መንፈስ ቅዱስ በእኔ በማደር የጊታን ስራ በነፃነት እና በራስ መተማመ መንፈስ ለመስራት እንድችል ምሪት እና ጥንካሬ ሰጥቶኛል በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን በአንድነት እና በብስለት ለእግዚአብሔር ክብር ታድጋለች።

ማረጋገጫ

ጆን ክሪሶስቶም (349 - 407) በቀልብ ሳቢ ስብከቶቹ እና በጀማ ንግግሩ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆን በማግኘት የሚታወቀ የጥንት ቤተክርስቲያን ዋነኛ መሪ ነበር። እንዲያውም የእሱ ቅፅል ስም (ክሪሶስቶም) “ክሪስቶስቶሞስ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ወርቃማው አንደበት” ማለት ነው።

ጸሎት

ለደኅንነት መጸለይ‑ የጆን ክሪሶቶም የሲቫኒካል የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት

በሰላም ወደ ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ ጌታ ሆይ ማረን ከሰማየ ለሆነ ሰላምና ለሰዎች ሁሉ ድነት ወደጌታ እንጸልይ ጌታ ሆይ ማረን ለዓለም ሁሉ ሰላም፣ ለክርስቶስ ቅድስት ቤት-ክርስቲያን መልካም ሁኔታ፣ ለቅዱሳን ሁሉ አንድነትና ህብረት በእግዚአብሄር ፊት እንጸልይ። ጌታ ሆይ ማረን ቅዱስ አገልግሎት ለመስጠት ስለሚችሉ ቅዱሳን ሁሉ እንዲሁም በእምነት ያሉት ሁሉ እግዚአብሄርን መፍራትና መምሰል ያድርባቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ። ጌታ ሆይ ማረን። ለ [ጳጳሶቻችን እና ሌሎች] ቀሳውስትና ለተሾሙባቸው ጉባኤዎች ወደ ጌታ እንጸልይ። ጌታ ሆይ ማረን ለሁሉም ለሃገራችን ህዝቦች እና ለሲቪል ባለስልጣናት በአደራ ለተሰጣቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ጌታ እንጸልይ። ጌታ ሆይ ማረን

Made with FlippingBook - Online magazine maker