Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
የትምህርት 4 ተቀበልነው ስጦታ: - • 59
ለዚህችም ከተማ፤ ለሌሎችም ከተሞችና አገሮች ሁሉ፤ በእነዚህም ከተሞች ስለሚኖሩ አማኞች ሁሉ ወደ እግዚአብሄር እንጸልይ። ጌታ ሆይ ማረን፤ አሜን!
~ ሮጀር ጂፌን የህዝብ የማህበር ጸሎት መጽሐፍ. ገጽ 115.
ኦ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የአብና የልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ፣ የሥላሴ ሦስተኛው አካል የሆንህ አንተ አምላክ ነህ። አንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ከአብ ዘንድ የተሰጠኸን የእውነት የፍቅር እና የቅድስና መንፈስ እንደሆንህ እናውቃለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት ምክንያት ወደ እኔ መጥተኻል እናም አሁን አወድስሃለሁ እንዲሁም በሙሉ ልቤ እወድሃለሁ። በኔ ስለምትኖር፤ የእግዚአብሄር ርስት እንድሆን ስላተምከኝ፣ እንዲሁም የእግዚአብሄርን ቃል ስለምታስተምርኝ እና እግዚአብሄርን እንዳውቅና እርሱንም የህይወቴ ብርሃንና ብርታት እንዲሆን እንድፈልገው ስለምትረዳኝ አመሰግንሃለሁ። አንት ብርታቴ ነህ። ልቤን ለጌታ ባለ ፍቅርና እግዚአብሄርን በመፍራት ሙላው። እግዚአብሄር ሆይ በጌታ መንገድ ምራኝ እንዲሁም ለኃጢአት ያለኝን ፍላጎት ማሸነፍ እንድችልና ፍቃድህንም በፍጹም ልቤ እንድፈልገው እና እንዳደርገው እርዳኝ። በሃጢአት እንዳልወድቅ ትዕግስት እና ግልጽነትን ስጠኝ፤ ከአንተ ጋር እንድጣበቅና በአንት እንድደገፍ እምነትን ጨምርልኝ፤ በአንተም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን የበለጠ እንድመስለው እርዳኝ። ስለዚህ ቅዱስ አባት ሆይ የጠራኸኝን የቅድስና ህይወት እንድኖር ህይወቴን ለውጥልኝ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች ሰማያዊ አባቴን አንተን እንዳስደስትህ እርዳኝ። ከመንፈስ ቅዱስ እና ከጌታ ኢየሱስ ጋር የነገስህ አንተ የህይወቴ ምንጭ ነህ። በኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ስም እፀልያለሁ። አሜን!
የልብ ጩኸት ወደ ጌታ
At www.tumi.org/sacredroots,በዚህ ድህረ ገጽ ለተጨማሪ ጥናት የሚያገለግሉ ተጨማሪ ጽሁፎችና ቪዲዮዎችን ታገኛላችሁ።
ለበለጠ ጥናት
ወደ እዚህ www.tumiproductions.bandcamp.com ድህረ ገጽ ይሂዱ እና የጌታን መንፈስ በህይወቶ ለመፈለግ የሚረዳዎትን “የጌታ መንፈስ” የሚለውን ዝማሬ ያውርዱና ያዳምጡ።
Foster, Richard J. and James Bryan Smith Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups . Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993.
በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የምናሳየው ልዕቀት እና የሚከተሉትን ርእሶች ጨምረን እንመለከታለን: 1. እኛ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሄርን የምንመስል ነን። 2. እንደ አምባሳደር በቅድስና እና በአመስጋኝ ህይወት እግዚአብሄርን እንወክላለን። 3. እኛ በፍቅር እና ሌሎችን በማገልገል እንኖራለን።
ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ
ፊልጵስዩስ 2፡13
ይህን ጥቅስ ያሰላስሉ
Made with FlippingBook - Online magazine maker