Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 5 የምናሳየው ልዕቀት: በዚህ ዓለም እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን እና የክርስቶስ አምባሳደሮች መኖር
እንግዲህ እርሱ እንደሚደሰትባቸው እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምንመስል ልንሆን ይገባናል። በፍቅር መመላለስን ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደደን እና ራሱንም ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ እንዲሁ በዚህ ዓይነት መንገድና ፍቅር ልንመላለስ ይገባናል። እንደ እግዚአብሄር ቅዱሳን *ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መጎምጅት* በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤ እነዚህ ከእናንት ጋር የማይሄዱ ናቸውና። ምክኒያቱም እነዚህ ከእናንት ጋር የማይሄዱ ናቸውና። ይልቁንም ንግግራችሁ መልካም ንግግርና ምስጋና እንጂ። ይህንን እውነት እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስትም ስምም የለውም።
~ የጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን ሰዎች (5፡ 1-5)
በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ እኛ ስለምናሳየው ልቀት የሚከተሉትን በማመን እንይዛለን • እንደ ተወደዱ ልጆቹ እግዚአብሄርን እንመስላለን • እንደ ቅዱሳን በክርስቶስ ውስጥ (ተቀደሱ) ሌሎችን እንደ እራሱ ቅዱስ እና አመስጋኝ በመሆን በሌሎች ሰዎች ፊት እግዚአብሔርን እንወክላለን። • እንደ አምባሳደሮች ለጓደኞቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ለጎረቤቶቻችን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የምስራች ወንጌልን በማካፈል እና በመልካም ስራ የክርስቶስን ፍቅር መግለጥ አለብን። ዘለዓማዊ አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ። ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ እናም ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማካፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቃለሁ (2 ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15)። እባክህ ውድ አባቴ ሆይ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እናም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ እንድሄድ ምራኝ። *መጎምጀት - መጎምጀት የአንድን ሰው ወይንም የሌላን ሰው ንብረት ለመያዝና ለማግኘት ያለ ከፍተኛ ፍላጎት ማለት ነው። አንድን ነገር ከመፈለግ የበለጠ ነገር ነው፤ ነገር ግን ከራስ ወዳድነት እና ከእግዚአብሄር ዓላማ ውጪ ዕብሪተኛ የሆነ ስግብግብነት ማለት ነው። *ቅዱሳን – ቅዱስ ማለት ለእግዚአብሔር ንብረትነት በአገልግሎት እና በአምልኮ የተያዘ ወይም የተለየ ማለት ነው። ይህ ቃል ብዙውን ጊዜ ባህሪው እጅግ የላቀ ጥሩ እና ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው በማለት በተሳሳተ መንገድ ሲተረጎም ይስተዋላል። ነገር ግን “ቅዱስ” እና “መቀደስ” ወይም “ቅድስና” የሚለው ቃል ሁሉ በአንድ ዓይነት ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ትርጓሜውም አንድ ነገር ለየት ላለ ዓላማ ሲለይ ማለት ነው። ለምሳሌ ለየት ላለ ጊዜያት የሚልብሷቸው ልዩ ልብሶች ወይም ጥንድ ጫማ ካልዎት እነዚያ ልዩ ልብሶች ለየት ላለ ክስተቶች/ዓላማዎች የሚውሉ ስለሆን “የተለዩ” (ወይም የተቀደሱ) ናቸው። በተመሳሳይም “ቅዱሳን” እርሱን ለማምለክ እና ለማገልገል በእግዚአብሄር የተለዩ ሰዎች ናቸው። *ጣዖት አምላኪ – ጣዖት አምላኪ ማለት ፈጣሪን ከማምለክ ይልቅ የፈጠራን ነገር የሚያመልክ ሰው ማለት ነው። ሰዎች ህይወታቸው መልካም እና ከችግር ነጻ የሆነ ህይወትን ስለሚፈልጉ ህይወታቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ ከማያውቁት እና ከማይረዱት ሃይል ሞገስ ለማግኘት ሞክረዋል። ስለዚህ ሰዎች የዝናብ አማልክትን፤ የአየር ጠባይን፣ ወይም የጦርነትን ድል በማድረግ ፈጣሪን ከማመን ይልቅ አማልክትን ያመልካሉ። ሌሎች ደግሞ ለራሳቸው ስግብግብ ጥቅም ሲሉ የካፒታሊዝም፣ የትምህርት፣የሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ወይም ወታደራዊ ስልቶችና ሰራዊት ላይ እምነታቸውን ይጥላሉ። ስለዚህ ጣዖት አምላኪ ማለት ፍላጎቱን ለመሙላት ከእግዚአብሄር ይልቅ በሌሎቸ ነገሮች የሚታመን ማለት ነው።
ዓላማ
የመክፈቻ ጸሎት
61
Made with FlippingBook - Online magazine maker