Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

62 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ። የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገርና ለቁጣ ግን የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ ሃሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።

በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ። ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቃለሁ አሜን።

1. “ይህን ለማድረግ ብርታት የማገኘው ከየት ነው፡ እግዚአብሄርን ለመምሰል ማለቴ ነው?” በጌታ ከመሆኑ በፊት አንድ ወጣት ክርስቲያን የአንድ የተወሰነ ዘርን ማለትም “ነጭ” ሰዎችን የሚጠላ የወሮበሎችና አባል ነበር። የጭካኔ ድርጊቶቹ ሁሉ፣ የሚናግሩት ንግግር ሁሉ፣ እና ሊግቧቧቸው የሚፈልጉት ነገሮች በሙሉ ነጮች በታሪክ ውስጥ በሌሎች ሰዎች ላይ የሰሩትን እና ያደረጉትን በመንቀፍ ነው። ወሮበሎቹ ነጮቹ ላደረጉት ድርጊት ሁሉ ለመበቀል በፈለጉበት ጊዜ፣ ባገኙት አጋጣሚና በሁሉም መንገድ እነርሱን ለመበቀልና ለማዋረድ ገንዘብን በመክፈል ለመጉዳት ቆርጠው ተነስተው ነበር። ይሁን እንጂ ንስሃ በመግባት ወደ ክርስትና በመለወጥ እና በክርስቶስ በማመን ይህ ወጣት ክርስቲያን ይህን ቡድን ትቶ እና በነጮች ላይ ያለውን ጥላቻ አስወግዶ በጌታ ቤት ይኖራል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለረዥም ዘመን ወደኖረው አሮጌውና ጥንተ ባህሪው የመመለስ እና ስለእነርሱ ክፉ የመናገር ጉዳይ ያሳስበው ነበር። ለተወሰነ ጊዜ ከአዕምሮው ጋር መታገል ከጀመረ በኋላ “እኔ እንደ ድሮው መሆን አልፈልግም፤ ጌታ እንደ እርሱ እንድሆን እንደሚፈልግ የበለጠ ተረድቻለው። ይሁን እንጂ በእውነት ይህን ለማድረግ ማለትም ጌታን ለመምሰል ብርታት የማገኘው ከየት ነው?” በዚህ ጉዳይ ላይ ለሚታገለው ለዚህ ወጣት ክርስቲያን የምትሰጠው ምክር ምን ይሆናል? 2. “ከዚህ በፊት በቅድስና አልኖርኩም፤ ወደፊትም እንደዛ አይነት ሰው የምሆን አይመስለኝም እና እኔ ቅዱስ ነኝ?” ከአንድ ወጣት ክርስቲያን (መካከለኛ እድሜ ያለው ሰው) ጋር መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ቅዱሳን (በክርስቶስ ቅዱሳን ሆነን) እንድንኖር ይጠብቅብናል በሚለው ትምህርት ላይ እንነጋገር ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እኛ በምናደርገው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔርን የምንወክል መሆኑን ሌሎች እንዲያስተውሉ ማድረግ እንዳለብን በግልጽ ያሳየናል። እኛ የተቀበልነው ህይወት ለእግዚአብሄር ዓላማና ስራ እንደተለዩ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ እና አመስጋኝ ህዝቦች እንድንኖር ተጠርተናል። ነገር ግን ወጣቱ ክርስቲያን እርሱ ያደረጋቸውን ሁሉ እና ቀደም ሲል ስለኖረበት መንገድ ሲያስብ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደሚችል ማየት አልቻለም ነበር። እግዚአብሔር “ቅዱስ” ብሎ እንደሚጠራው ሲያውቅ እጅግ ተገርሞ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ተግባሮች እያሰበ እግዚአብሄር “ቅዱሳን” ብሎ ሊጠራን እንዴት ይችላል? 3. “ክርስቲያን መሆን ልክ እንደ ዓለም መንግስት ለእግዚአብሄር መንግስት ምስጢራዊ ተወካይ መሆን ማለት ነው!” ምናልባት የውጭ አገር ተወላጅ የሆነ አንድ ምስጢር ተወካይ/ሰላይ/ በአንድ ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የአገሩን ፍላጎት ሲያገለግል የሚያሳይ ፊልም አይተው ይሆናል። ወይም ደግሞ አንድ አምባሳደር የአገሩን አመለካከት እና የአገሩን ፖሊሲ በተመለከተ ለሌሎች ሃገሮች ሲናገር ሰምተው ወይም ይህንን የሚያሳይ ዜናን ተመልክተው ይሆናል።

ማዛመድ

Made with FlippingBook - Online magazine maker