Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 5 የምናሳየው ልዕቀት: • 63
እሱ/እሷ ሲናገሩ የአገራቸውን አቋም የአገራቸውን ህዝብና መንግስት በመወከል በአጠቃላይ አገራቸውን በመሆን እና ለዚያ ጉዳይ የበኩላቸውን አስተያየት በመስጠት ሃገራቸውን ወክለው ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የአምባሳደርን ጽንሰ ሃሳብ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያን እንደ እግዚአብሄር መንግስት አምባሳደር በመሆን የሚያገለግላቸውን ቤተሰቦቹን፣ ጓደኞቹን፣እና ማህበረሰቡን በማገልገል የክርስቲያንን ድርሻ እና ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ለመረዳት እንዴት ይጠቀማል? ባለፈው ክፍለ ጊዜ (እኛ የምንቀበለው ስጦታ) በሚለው ርዕስ ስር እንደተማራችሁት በዳንበት ጊዜ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን አካል ለመገንባትና ለማነጽ የሚያገለግል የጸጋ ስጦታን እንደሰጠ ተመልክተናል። አሁን መልካሙን የእምነት ገድል በምንጋደልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት በዚህ ዓለም ውስጥ በአግባቡ እና በጥልቀት እርሱን ሊወክሉ እንደሚችሉ እንዴት እንደሚጠቀሙበት ይዳስሳሉ። እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሄር ልጆች እንደሆንን (1 ኛ ዮሐንስ 3፡1-3) እንደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመመላለስ፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል፣ የእርሱን ፍለጋ ለመከተል እና እርሱ እዚህ ምድር ላይ በእኛ ውስጥ በመኖር ሌሎችን ለመውደድ ተጠርተናል። እኛ በክርስቶስ በኩል ባለን እምነታችን ጻድቃን የሆነን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጢአት የተቀደስንና ንጹሃን የሆንን የብቸኛው የእግዚአብሔር “ቅዱሳን” ተብለን የተጠራን ቅዱጽሕዥብ ነን። እግዚአብሔር የእኛን ቅድስና (ለእግዚአብሔር ንብረትነትና አገልግሎት መለየት) በሁሉም የህይወታችን ክፍል ውስጥ - በአስተሳሰባችን፣ በባህሪያችን፣ በንግግራችን፣ በምግባራችን እና ግንኙነታችን - እኛ የክርስቶስ እንደሆንን እና መንግሥቱም በመካከላችን ማለትም በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ይታይ ዘንድ ፈቅዷል። እኛ እንደ አማኞች በተለያዩ የህይወታችን ክፍል ውስጥ የቅዱሳንን ድርሻ ልንወስድ ይገባናል፤ እናም መንፈስ ቅዱስ በጊዜ እና በዲሲፕሊን እኛ አብ እንደሆን ያሰብልንን እንድንሆን ይስራን። እግዚአብሄር እያንዳንዳችን ራስ ወዳድነት እና በክፉ ምኞት ሕይወት እንድንኖር ስላልጠራን የልቁንም ለታላቅ ቅድስና እና የሚያምር አዲስ ህይወት - እርሱን ለሚያከብረው ህይወት ስልጠራን እራሳችንን በቅድስናና በክብር ለማኖር ራሳችንን እንዴት መግዛት እንዳለብን መማር ያስፈልገናል። ከዚህም በተጨማሪ እኛ የክርስቶስ አምባሳደሮች ስለሆንን፤ እግዚአብሔር አሁን በእኛ በኩል ለሌሎች ይማልዳል። ኢየሱስን እንደ ጌታ ስናውጅ እና በስሙ በማመን የሚገኝወን የዘላለም ሕይወት ለሚያምኑ ሁሉ ስናካፍል መልእክታችንን በአኗኗራችን፣ በንግግራችን፣ እና በተግባራችን ህጋዊ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን። አሁን የእርሱ አምባሳደሮች እንደመሆናችን መጠን የእርሱን ፍቃድ/ መሻት/ ለመወከል፣ ቃሉን ለመናገር እና እርሱን ከማያውቁት ይልቅ የተለየ ባሕርይ እንድናሳይ ተጠርተናል። የተቀረው ዓለምን ከመምሰል ይልቅ በክርስቶስ የተለወጠና አመስጋኝ ህዝብ መሆናችንን እናሳያለን። እኛ የክርስቶስ አምባሳደሮች ነን። ጀርባችንን ለዓላማዊነት፣ አምላክ የልሽ ለሆነ የህይወት ዘይቤ እና በኃጢያት ለተሞላ አኗኗርን በመስጠት፤ በእግዚአብሔር በተሞላ፣ለእግዚአብሄር ክብርን በሚያመጣ ህይወት በአምላካችን እና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልነውን ሕይወት ለሌሎች እናካፍላለን። እኛ እርሱ አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካም ስራ በተለያየ መልካም ስራዎቻችን በመግለጥ እርሱን ለማክበር በእግዚአብሔር የተለየን የእርሱ ሰራተኞች ነን። ሌሎችን ልንወድና ልናገለግላቸው፣ የእርሱን ታሪክ ልንነግር እና ሌሎችን በተለይም ቤተሰቦቻችን እና ጓደኞቻችንን ከእኛ ጋር እንዲገኙ መጋበዝ አለብን።
ይዘት
Made with FlippingBook - Online magazine maker