Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

64 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋትና ርኅራሄን፣ ምህረትን እና ፍትህን ማድረግ መለያየት አይቻልም። በዚህ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረታዊ መርህ መሰረት ቤተክርስቲያንን ወደ ርህራሄ፣ ምህረት እና ፍትህ አገልግሎት እንድትመጣ እርምጃዎች መውሰድ አለብን። ርኅራኄ በእኛ ውስጥ የእግዚአብሄርን ፍቅር ይወክላል እናም በእኛ ውስጥ ይገለጣል ይህም ለጠፉት ሰዎች ያለንን ስሜት እና አዲስ ህይወትን እንዲያገኙ መሻትን ወይም ፍላጎትን ይፈጥራል። ምህረት ለተሰበሩ ሰዎች እና ለተጎዱ ማህበረሰቦች ያለን አመለካከት ነው። ይህም ሰዎች ስላሉበት ሁኔታ ከመውቀስና ከፈራጅነት አስተሳሰብ እንድንወጣና በአዕምሮአችን እንድንልቅ ይረዳናል። ምንም እንኳን ሰዎች በመጥፎ ምርጫቸውና በመጥፎ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆኑም፤ ምህረት ከልክ በላይ በሆነ መንገድ የማይግባቸውን ምላሽ እንድንሰጥ ይመራናል። ይህ እግዚአብሄር እኛ ከእርሱ በራቅን ጊዜ በሌላ ሰው[በክርስቶስ] በኩል እኛን የሚመለከትበት መንገድ ነው።

~ Efrem Smith. The Post Black & Post White Church: Becoming The Beloved Community in a Multi-ethnic World. San Francisco, CA: Jossey-Bass, 2012, page 59.

የምናሳየው ልቀት ትምህርት 5 የመጽሐፍ ቅዱስ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን ሃሳቦች በማገናዘብ አጠር ያለ መልስ ይስጡ። 1. ሕይውታችን ከሆነው ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስለተጣበቅን መንፈሳዊ ፍሬዎችን (በቅድስና መኖርና የክርስቶስን ፍቅር ለሌሎች ማካፈልን) እናፈራለን፤ ምክኒያቱም ከእርሱ ጋር በሕብረት ስላለን (በየዕለቱም ህብረትን ስለምናደርግ)። ዮሐንስ 15:1-8 ያንብቡና የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ይስጡ

ሀ. በኢየሱስ ክርስቶስ የወይኑ ግንድ ፣ ገበሬው፣ እና ቅርንጫፉ አስተምህሮ መሰረት ክርስቶስ ማን ነው፣ እግዚአብሔር አብ ማን ነው፣ እኛስ ማን ነን?

ለ. ቅርንጫፉ በግንዱ ባይኖር ማለትም ሕይወትንና በረከትን መካፈልን ቢያቆም ፍሬን ሊያፈራ ይችላልን?

ሐ. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር አብ እኛ በምናደርገው በምን ተግባር እንደሚከብር ተናገር?

2. ማንም በክርስቶስ የሆን ሁሉ የቅድስና ሕይወትን በመኖር በሚኖርበት ስፍራ ሁሉ የክርስቶስ አምባሳደር እንዲሆን ተጠርቷል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17- 6:2 ያንብቡ

ሀ. እግዚአብሄር ምን ዓይነት አገልግልት ሰጠን (ቁ. 18)?

Made with FlippingBook - Online magazine maker