Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

66 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

6. በክርስቶስ እንዳሉ አማኞች ሃሳባችንን በላይ ባሉት ነገሮች ላይ ማኖር አለብን፤ እናም እዚህ ምደር ላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስንኖር በቅድስና ለመኖር የሚያስችለንን መመሪያ በመከተል መኖር አለብን። ቆላስያስ 3፡1-17ን ያንብቡና የሚከተለውን ይመልሱ

ሀ. እኛ አሁን ከክርስቶስ ጋር ተሰውረናል ታዲያ ራሳችን እንዴት እንረዳዋለን? (ቁ 1-4)

ለ. ስለ “ምድራዊ ተፈጥሮአችን” ምንነትስ ምን አመለካከት (አቋም) ሊኖረን ይገባል? (ቁ 5-9)

ሐ. ስለ አሮጌ እና ስለ አዲሱ ማንነታችን ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? (ቁ 9-10)

መ. አሁን የእግዚአብሄር አምላክ ምርጥ ሕዝብ እንደመሆናችን መጠን ምን ዓይነት ባሕርያ ልናዳብር ይገባል? (ቁ 11-17)

7. የእግዚአብሔር ጸጋ ለክርስቶስ ዳግም ምፅአት በምንዘጋጅበት ጊዜ እንዴት እንደምንኖር እና መልካም ስራዎችን እንድናደርግ ያስተምረናል ። ቲቶ ምዕራፍ 2.11-14ን አንብብ ባዶዎቹን ሙላ።

ሀ. ደኅንነትን ያመጣው የእግዚአብሔር ጸጋ ___________________________________________________ ክደንና፥ ________________________________________________________________ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል። ለ. መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ___________________________________________እንዲቤዠን _____________________________________________________________፟ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመ እንደ ተወደዱ የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔርን በመምሰል እና እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎችን በፍቅር ለመንከባከብ ተጠርተናል። ቀድሞም እንደነበረው አሁን እኛ በዚህ ዓለም ውስጥ የእርሱ አካል ሆነን ልክ እርሱ በምድር ላይ እንደሆነው እና እንደተመላለሰው እኛም በእምነት እርሱ በውስጣችን ስለሚኖር እርሱ እንደኖረው እንኖራለን። ስለዚህ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ጽድቅን የተቀበልን የእግዚአብሔር “ቅዱሳን” (ቅዱስ) ተብለን ተጠርተናል። በጌታ ፊት ንጹህና ቅዱስ ኑሮን ለመኖር ተለይተናል። እኛ ለመቀደስ (ለእግዚአብሔር ንብረትና መገልገያ ለመሆን) በመለየት፤ የክርስቶስ እንደሆንን ለማሳየት እና ለሌሎች ለማሳወቅ እነሱም እኛ በተለወጥንበት ወንጌል ሊለወጡ እንደሚችሉ ምስክር ለመሆን ተለይተናል። በእርግጥ እግዚአብሔር አምላካዊ ላልሆነ ኑሮ እና ርኩስ እንድንሆን አልጠራንም፤ ይልቁንም በቅድስና እና በጽድቅ እንድንኖር ጠርቶናል። ቅዱሳን ለመሆን ከመጠራታችን በተጨማሪ፤ በአኗኗራችን እና በግንኙነታችን ለኢየሱስ ክርስቶስና ለእግዚአብሔር መንግሥት አምባሳደሮች በመሆን እርሱን እንድንወክለው ተጠርተናል። እኛ የመንግሥቱ መሪዎች፣ የሰማያዊው የእግዚአብሔር ንግሥት ዜጎች፤ እና እግዚአብሔር በስሙ ሌሎች ሰዎችን ወደ ራሱ እንድንጠራ በስሙ ኃይል የተሰጠንና የተሾምን ነን። ይህንንም በግልፅነት፣ ከፍ ባለ ልቀት እና በድፍረት ለማድረግ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። በቃልም ሆነ በድርጊታችን የናዝሬቱ ኢየሱስን እንደ ጌታ እና ክርስቶስ እንዲሁም ዳግምኛ ወደ ዓለም የሚመጣው የዓለም

ማጠቃለያ

Made with FlippingBook - Online magazine maker