Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 5 የምናሳየው ልዕቀት: • 67
ንጉሥ እንደሆን ማሳየት አለብን። በወንጌል ገለፃዎቻችን አማካኝነት ንስሀ ለሚገቡ እና ለሚያምኑት ሁሉ በስሙ ያለውን ሕይወትን እንሰጣለን፤ እና በፍቅራችን እና በመልካም ስራዎቻችን ይህች መንግሥት ምን እንደምትመስል እናሳያለን። በድርጊቶቻችን በየቀኑ ለቤተሰባችን፣ ለጓደኞቻችን እና ለጎረቤቶቻችን “አሳይ እና ተናገር” የተባለውን መርህ አምላካዊ ትርጉሙ ምን እንደሚመስል እና በእግዚያብሄር መንግስት ውስጥም ምን ማለት እንደ ሆነ ሃላፊነታችንን በመወጣት ለህዝቡ እናሳያለን። ማንም ሰው በራሱ ጥንካሬ እና ፍቃድ የክርስቶስ ቅዱስ እና የክርስቶስ አምባሳደር ሊሆን አይችልም። ክርስቶስ በውስጣችን በመንፈስ ቅዱስ ይኖራል፤ እናም እርሱን ልንወክል የምንችለው ከእሱ ጋር በየዕለቱ ስንመላለስ ብቻ ነው። እኛ በፍጹም በክርስቶስ በታመንን ቁጥር፤ እርሱን ልንወክለው እንችላለን ማለት ነው።
በዚህ ክፍል ውስጥ ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች ማጥናትና ማሰላሰል የሚያስችሉንን እንመለከታለን
ተጨማሪ አባሪ
የኦይኮስ ሁኔታ/ ትግበራ (ተጨማሪ አባሪ 10) መሲሑን ለሌሎች ማስተላለፍ : የወንጌል ግንኙነት (ተጨማሪ አባሪ 19) ወደ ኋላ መለስ ብለን በመመልከት ወደ ፊት መጓዝ: ወደ ታላቁን ታሪካዊ የወንጌል ምርምር ባህል መጓዝ (ተጨማሪ አባሪ 16)
አንድ ዓለማዊ ሰው ለገንዘብ ብቻ በመስራት በጣም ደስ እንደሚለው፤ ማንኛውም ክርስቲያን በሃዘን ፊቱን አርዝሞ እና በእንባ ተሞልቶ ለክርስቶስ አንድ ነገር ለመስራት ሲያቅተው ማሰብና ማየት ያሳፍረኛል።
~ Hannah Witall Smith. Richard J. Foster and James Bryan Smith, Eds. Devotional Classics: Revised Edition: Selected Readings for Individuals and Groups. Renovare, Inc. (HarperCollins Publishers), New York. 1993, p. 239.
9d እግዚአብሔር ዛሬ ያሉትን ከተሞች የእግዚአብሄር የወንጌል ማዕከል እንድናደርጋቸ ከእርሱ ጋር አብረን እንድንሠራ ጠርቶናል። በዓለማዊው አሰራር ውስጥ ልክ ሻሎም[ሰላም] እና የመሬት አገዛዝ የሚለው የመንግስት ጭብጥ ዋናው ገጽታዎች እጅግ በጣም ወሳኝ እንደሆኑ ሁሉ እግዚአብሔርን ግድ የሚለው ዋና ሃሳብ “በትላልቅ ቪላዎች ላይ ያሉ ቁልፎች” አይደለም ነገር ግን በምድር ላይ በክርስቶስ ህይወት ሊኖር የሚችል ማህበረሰብ ነው። በመጨረሻም “ሁሉንም ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ” (ሐዋ 3፡21) ሲመጣ የእርሱን ከተማና መንግሥቱን ያመጣል፣ ክፉም ይፈረድበታል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ እና የቤተክርስቲያኑ የአሁኑ ተልእኮ ከተሞችን የፍትህ እና የሰላም ቦታ እንዲሆን ማድረግን ይጨምራል፤ በእነርሱ ላየ ከመፍረድ እና ጥሎ ከመሸሽ ይልቅ። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝ እና ሉዓላዊ ጌታ አድርጎ የማሳየት ውጤታማ ምሥክርነት ይጠይቃል።
~ Howard A. Snyder. Kingdom, Church and World: Biblical Themes for Today. Eugene, OR: Wipf and Stock Publishers, 2001, p. 48.
Made with FlippingBook - Online magazine maker