Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

68 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

እኛ መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ፍጥረቱ ነን (ኤፌሶን 2፡10)።

ቁልፍ መርሆች

ከዚህ በላይ በተማርካቸው ጽሑፎች ላይ ተመስርተው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ፅሁፎች በማንበብ የሚከተሉት የመከራከሪያ ሃሳቦች እና ጽንሰ ሐሳቦች ያንብቡና ያብራሩ እንዲሁም ተገቢውን መልስ ይስጡ። 1. ስንወድቅ ምን ይከሰታል? ብዙ ጊዜ አዲስ አማኞች እግዚአብሔር የእርሱ ቅዱሳን እንዲሆኑ እና የክርስቶስ አምባሳደሮች እንደሆኑ ሲነገራቸው በታላቅ ቅንዓትደስታ ሲቀበሉ ይታያሉ። ከጌታ ጋር በየዕለቱ በሚራመዱበት ጊዜ በጌታ እየጠነከሩ ይሄዳሉ ነገር ግን የዓለም ፈተናዎች፣ የዲያቢሎስ ውሸቶችና ሽንገላዎች እንዲሁም በዓለማዊ መንገድ አሮጌ ልማዳዊ አኗኗራቸውን በመከተል ምክንያት ከመንፈሳዊነት መጉደልና እና በኃጣአት ሊወድቁ ይችላሉ። በተደጋጋሚ በአንድ ዓይነት ስህተት እንኳን ሳይቀር ስንወድቅ ወይም ስንፈተን ምን እናደርጋለን? አንድ ክርስቲያን ነኝ እያለ በተደጋጋሚ የሚወድቅ ሰው - ይህ ሰው እንደ አማኝ መቀጠል ይችላልን? እኛ ደህንነታችን በተግባር ላይ በምናውልበት ጊዜ በመለኮታዊ መገኘት ውስጥ የምንኖርና ስሕተት በሰራን ጊዜ ደግሞ ሁሉም ነገር ይሰረዛልን? አማኞች አሁንም ስህተት ከሰሩና ካደረጉ በኋላ እንኳን እንደ ቅዱሳን እና አምባሳደር ይቆጠራሉ? የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያንብቡና የእርሶን የተለየ ዕይታ እና አቅጣጫ ከሌላ አማኞች ጋር ይከፋፈሉ። • 1 ዮሐንስ 1.5 - 10 2. በህብረተሰብ ውስጥ ባሉ በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ ነጠላ ክርስቲያናዊ አቋም አለ? እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳንና የክርስቶስ አምባሳደር መሆን መንፈስን ያድሳል፤ ነገር ግን ተራ ወይም ቀላል አይደለም። በአንድ ጉዳይ ላይ እኛ ያለንን አመለካከት ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋራ ግራ እንዳናጋባ መጠንቀቅ አለብን፤ እንዲሁም በተመጣጣኝ ሁኔታ የቴሌቪዥን ሰባኪያን በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደ ወንጌል እውነት ነው ብለው የሚያስተላልፉትን መለዕክት በጥርጣሬ እና በጥንቃቄ መመልከት ይገባናል። ከሁለቱም ተቃራኒ ጎኖች በየትኛውም ጉዳይ ላይ ነገሮችን በእኩልነት እና በቅን ልብ የሚመለከቱ ሁለቱም ወገኖች ጥቅሶችን በመጥቀስ እና የእነርሱ አመለካከት የእውነተኛውን “ክርስቲያን” አቋም ይወክላል ብለው አቋም የሚይዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች አሉ። አንድ ክርስቲያን በአንድ ጥያቄ ላይ የተቃረኑ አመለካከቶችን የሚያራምዱ ጠንካራ አማኞችን ሲያገኝ ምን ማድረግ አለበት? በማህበረሰቡ ውስጥ ስለ እያንዳንዳቸው ርዕሰ ጉዳዮች ሁልጊዜ አንድ ግልፅ እና “ትክክለኛ” አስተያየት ወይም አመለካከት ሊኖር ይገባልን? ሮሜ 14፡1-12 ከጌታ ጋር ስንራመድ እነዚህን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለመገንዘብ እንዴት ይረዳናል? 3. በቃላችን ከምንናገረው ይልቅ ማንነታችንን በታላቅ ድምጽ ይናገራል። ያለምንም ጥያቄ ማንነታችን ወይም ኑሮአችን ከቃላችን በበለጠ ይናገራል። ስለ እግዚአብሔር መንግስት በቃላችን ብቻ ሳይሆን እነዚህን የምናውጃቸውን እውነቶች በተግባር በመኖር ሌሎች ስለእውነት ምስክር እና ምስክርነት እንዲሰጡ ለማድረግ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ሐዋርያው ​ዮሐንስ በጻፈው የመጀመሪያ መልዕክቱ ውስጥ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግረናል • ኤች. 24.16 • ያዕቆብ 5.16 • መዝ. 32-3-5 • ኤች. 28:12-13

የናሙና ጥናቶች

Made with FlippingBook - Online magazine maker