Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 5 የምናሳየው ልዕቀት: • 69
እውነተኛ ፍቅር ምን እንደሆነ እንዴት እንደተረዳን እንግለፅላችሁ- ኢየሱስ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአል። እኛም በክርስቶስ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ዝግጁ መሆን አለብን። ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ (1 ዮሐ 3.16-18).። መጽሐፍ ቅዱስ አማኞች እውነተኛ ፍቅር እንዲገልጹ (ሮሜ 12፡ 9) ይህንንም ፍቅራቸውን በበጎ ቃላት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን በማገልገል በተግባራዊ ድርጊት (ያዕ 2:15-17) እንድናሳይ በርካታ ጥሪዎችን ያቀርብልናል። ጌታ ፍቅራችን በቃላት ብቻ ሳይሆን ሰዎች ሊያዩትና ሊለማመዱት በሚያስፈልጋቸው መልካም ተግባራት ሁሉ ላይ መታየት ስለማስፈለጉ ጌታ በጣም ብዙ ትኩረትን የሚሰጠን ለምን ይመስላችኋል? አሁን እነዚህ ሕያው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ህይወታችሁን ሊነኩ የሚችሉባቸውን መንገዶች ሁሉ ማሰብ አለባችሁ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በእግዚአብሔር የተወደዱ ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን እግዚአብሔርን እንድትመሰሉ እና በእግዚአብሔር የተቀደሳችሁ የእግዚአብሄር ቅዱሳን ተብላችሁ ተጠርታችኋል! እስቲ በአሁኑ ወቅት ማንነታችሁ የሚያገልፁባቸውን መንገዶች ማለትም እንዴት እንደምትናገሩ እና ለሌሎች ምላሽ እንደምትሰጡ፣ ከቤተሰብ አባላት እና ከጓደኞቻችሁ ጋር እንዴት እንደምትገናኙ እና ለሌሎችን እንዴት እንደምትንከባከቡ አስቡ። ለምትገናኟቸው ሰዎች እግዚአብሄርን በይበልጥ ወጥነት ባለው ህይወትን መግለጥና መምራት እንዲችሉ መንፈስ ቅዱስን ጥንካሬና ጥበብ እንዲሰጣችሁ ይጸልዩ። አብረዋችሁ ከምትኖሩባቸው ጋር ያላችሁን ግንኙነት የሚያበላሹና እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን እንዲሁም ምስክርነታችሁን በተመለከተ ሌሎች ላይ የተሳሳተ አስተዋጽዎ ሊያደርጉ የሚችሉ ነገሮችን እንድትተው የሚያስፈልጉ ነገሮች ምንድን ናቸው? በተጨማሪም ክርስቶስን እና የእርሱን መንግሥት በቃለና በተግባር እንትወክሉ የተጠራችሁ የክርስቶስ አምባሳደሮች ናችሁ። ስለ ክርስቶስ ማንነትና ስለ መንግሥቱ ምንነት ግልጽ በሆነ መንገድ ለሌሎች ሊያስተላልፉባቸው ከሚችሉ ሌሎች የላቁ መንገዶች ጋር ለመግባባት፣ ራስዎን ለማስለመድ ወይም ለማገልገል ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? እውነተኛ ወይም ሐቀኛ ለመሆን አትፍሩ። ምናልባትም አንዳንድ ነገሮችን በተወሰነ ደረጃ ማቆም ይኖርብዎት ይሆናል፤ ምናልባት የተወሰኑ ነገሮችን ማድረግ መጀመር ወይም አንዳንድ ባህሪዎችን ወይም ግንኙነቶችን ሊቀይሩ ይችላሉ። እግዚአብሔር አንድ ነገር በቀጣይነት እንዲሰሩ ወይም ምናልባት ብዙ ጊዜ እንዲያደርጉ ወይም ከሌሎች ጋር እንዲያደርጉ ምሪትን ሊሰጥዎትና ሊጠይቆት ይችላል። መንፈስ ቅዱስ ስለ ፃድቅነትዎ እና ስለ አምባሳደርነትዎ ለሚያሳይዎት ነገር ክፍት ይሁኑ እንዲሁም የሚያዝዎትንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ ይሁኑ። አስታውሱ እግዚአብሄርን እየመሰሉ መኖር በየዕለቱ በቁጥር ትንሽ የሆነችውን በትንሹ በትንሹ እየታዘዙ መኖር ነው። እርሱ እግዚአብሄር በሚናገርበት ጊዜ ምላሽ ይስጡ በአዲሱ ማንነትዎ ማለትም እንደ እግዚአብሄር ቅዱሳንና እንደ ክርስቶስ አምባሳደር ይኑሩ።
ግንኙነት
የእግዚአብሔር ኃይል በእኔ ውስጥ በመስራቱ ምክንያት የእግዚአብሔርን ባሕርይ በመግለጥ ህይወት እና ሌሎችን በፍቅር በማገልገል ህይወት በመኖር እርሱን እንደ አምባሳደርን መወከል እችላለሁ።
ማረጋገጫ
አውጉስቲን የሂፖ (354-430) በምዕራባዊው ስልጣኔ የቤተክርስቲያን እድገት ላይ በጽሁፎች ተጽዕኖ ያሳደረ የሃይማኖት ምሑር እና ፈላስፋ ነበር። እርሱ የሂፖ (የዘመናችን አልጄሪያ) ጳጳስ
ጸሎት
Made with FlippingBook - Online magazine maker