Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

70 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ

ነበር። በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ ነበር። በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ስራዎቹ መካከል “የእግዚአብሔር ከተማ” እና “የቤተ ክርስቲያን ኮንፌሽን” የተሰኙት ከፍተኛ ቦታ አላቸው።

እግዚአብሔርን ለማወቅ የኦገስቲን ጸሎት

ጌታ ኢየሱስ ሆይ- ራሴ እንዳውቅና አንተንም እንዳውቅ ከዚህም ውጭ የሌላ ነገር መሻት እንዳይኖረኝ አድነኝ። እኔ እራሴን በቻ እጠላለሁ እናም አንተን ብቻ ልውደድ። ስለ አንተም ሁሉንም ነገር ላድርግ ራሴን ዝቅ አድርጌ አንተን ከፍ ከፍ ላድርግህ ከአንተ በቀር ምንም ነገር አላስብ ለራሴ ፈቃድ ልሙትና ላንት ልኑር ሁሉንም አይነት ነገር ሲፈፅሙብኝ ከአንተ እንደሆነ ልቀበለው እኔነቴን አስወግጄ አንተን ልከተል እናም ሁሌም አንተን ለመከተል ፍላጎት ጨምርብኝ ከራሴ ልሽሽና በአንተ ውስጥ ልደበቅ፤ በዚያም በአንተ እከለላለሁ ለራሴ መፍራቴን አቁሜ አንተን ብቻ ልፍራ እናም በአንተ ከተመረጡት መካከል አድርገኝ በራሴ መታመኔን ትቼ ባንተ ብቻ ልታመን ስለ አንተ ሁሉን ለመታዘዝ ፈቃደኛ እንድሆን እርዳኝ እኔም ከአንተ ጋር ብቻ እንድጣበቅ ስለአንተም ሁሉን እንዳጣ እርዳኝ አንተን ብቻ እንድወድህ ወደኔ ተመልከት ጥራኝ አንተን ብቻ እንዳይህ እናም ለዘላለም ባንተ ብቻ እንድደሰት አድርገኝ።

~ Don L. Davis. A Sojourner’s Quest . Wichita, KS: The Urban Ministry Institute, 2010, pp. 93-94.

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ዘለአለማዊው እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስና የክርስቶስ አምባሳደር እንድሆን ስለጠራኸኝ አመሰግንሃለሁ። እኔ በማደርገው ድርጊት ሁሉ አንተን መወከል እንድችል፣ ለዚህ ዓለም ርኩሰት ጀርባዬን እንድሰጥ እና በመንግሥትህ ለመኖር ለሰጠኸኝ ለዚያ ታላቅ ጥሪ መድረስ እንድችል ወደፊት እንድገሰግስ እንድትረዳኝ እለምንሃለሁ። አባት ሆይ እባክህን በጽድቅ፣ በቅድስና እና በንጽህና በየዕለቱ ለመኖር እንድችል ኃይልን ስጠኝ። ከእኔ ጋር ሂድ እና እርዳኝ። መንፈስህ ከእኔ ጋር መሆኑን በመረዳት እያንዳንዱን ቀን በተስፋ ተሞልቼ በየዕለቱ ውጣ ውረዶች እና ፈተናዎች ሲያጋጥመኝ እንደሚረዳኝ በመተማመን በየቀኑ በድፍረት እንድጋፈጥ እርዳኝ። እንደ አንተ ቅዱሳን እና እንደ አምባሳደርህ ዛሬ ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙንት እንዳላጣ እና ከእኔ ጋር ምንም እንዳልሆንኩ በሁሉም በማደርጋቸው ነገሮች እኔ ለራሴ እንዳልሆንሁ እንዳስታውስ እርዳኝ። በከበረው ደምህ በዋጋ ገዝተኸኛልና እናም አሁን እኔ የአንተ ነኝ። ስለዚህ ዛሬ ምንም እንኳን የምጋፈጣቸው ነገሮች ቢኖሩም አእምሮዬንና ልቤን ጠብቅ። ሌሎች እኔ በማደርገው፣ እኔ በምሰራውና እና ምላሽ በምሰጠው እንዲሁም ዛሬ ከሁሉም ሰው ጋር በማደርገው ግንኙነት አንተን በእኔ እንዲያዩ እርዳቸው። እኔ በማደርገውና በምናገረው ሁሉ የበለጠ ክብርን ላመጣልህ

ወደ ጌታ የልብ ጩኸት

Made with FlippingBook - Online magazine maker