Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ትምህርት 7 እኛ የምንዋጋው ጠላት • 91

ተዋጊዎች ነን። እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ የጎዱትን የክፉዎች ስልጣን ላይ ድል የተቀዳጀው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወኪል እንድንሆን ተጠርተናል። በዚህ ውጊያ ማንም ገለልተኛ መሆን አይችልም። ጠላታችን ሰይጣን የሰዎችን ህይወት በተንኮል እና በማጭበርበን ለማጥፋት በሚፈልጉ ርኩሳን መንፈሶችን ያሰማራል እንዲሁን ይመራል። ይህ የወደቀው የዓለም ስርዓት ከእኛ የውስጣዊ ስጋዊ ፍላጎት ጋር በመተባበር በእኛ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማዳከም ይሠራል። ዲያቢሎስ እኛን ለመቃወም እና እኛን ለመጉዳት የሚያደረጋቸውን ጥረቶች በሚገባ የተገነዘብን እና ንቁ የሆንን እንድንሆን ተጠርተናል። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልንቃወመው እንችላለን፤ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት አጥብቀን ስንይዝ እርሱ ወደ እኛ የሚያመጣቸውን ሐሰቶችንና ሽንገላዎችን ሁሉ ውድቅ ልናደርጋቸው እንችላለን። እግዚአብሔር መልካሙን የእምነት ገድል ስንጋደል ብርታት ይሰጠናል! የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ታሪክ እና የሰው ልጆች ሁሉ ህልውና ማዕከላዊ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው በዚህ መነጽር ልናነብበት ወደሚያስችለን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይጋብዘናል። እንደ እግዚአብሄር ቃል መጋቢዎች እራሳችንን ይክርስቶስን ማዕከላዊነትን በበላይነትና በዝርዝር ወደሚያሳየው አስደናቂው የስሉስ እግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ ማስገባታችን እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ያሳየናል- ይህም የእግዚአብሄርን አስደናቂ ታሊክወይም ድራማ እግዚአብሂረር ዓለምን ለማዳን ከእኛ እንደ አንዱ እንድሆነ ያሳየናል።ይህ የእግዚአብሄርን ሁሉን የማዳን ዓላማ- ሁሉንም የሚቀሰቅስ ቀስቃሽ ርዕስ አልያም አነቃቂ ተናጋሪዎችን ወይም ግዙፍ ቴራፒ ህክምናን ተደራሽ የሚያደርግ ሳይሆን - እንደ ቤተክርስቲያን ወደዚህ ማዕከላዊ መልዕክት መመለስ አለበን የሚል ነው። ይህ የሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ እና የመስበክ መንገድ ብቻ አልያም የጥንታዊ ቤተክርስቲያን አባቶች መንገድ ብቻ አይደለም ይልቁንም በጥንቱ መሰረት ላይ በመቆም ለወደፊቱ ጥንተ-ወደፊት አምልኮ ለመፍጠር ለሚያስቡ አብያተ ክርስቲያናትም ጭምር ነው።

~ Robert E. Webber. Ancient-Future Worship: Proclaiming and Enacting God’s Narrative. Grand Rapids, MI: Baker Books, 2008, p. 121.

ከዚህ በታች የሚከተሉት ትምህርቶች ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ነገሮችን ማጥናት ማሰላሰል ያለብህ ተጨማሪ አባሪውች ናቸው

ተጨማሪ አባሪ

የክርስቺስ ቪክቶር ሥነ-መለኮት (ተጨማሪ አባሪ 11) ክሪስስ ቪክቶር: ለክርስቲያን ሕይወት እና ምስክርነት የተቀናጀ ራዕይ (ተጨማሪ አባሪ 12) የናዝሬቱ ኢየሱስ-የመጪው ጊዜ መኖር (ተጨማሪ አባሪ 4) ኢየሱስ ክርስቶስ- የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይና ጭብጥ (ተጨማሪ አባሪ 22) እግዚአብሔር ይነሣ! ጌታን የመሻት እና የእርሱን ምህረትን የመፈለግ ሰባቱ “ሀ” (ተጨማሪ አባሪ 23)

በእናንተ መካከል ስላለው አሰቃቂ ፈተና መከራ አንድ የሚያስገርም ነገር እየደረሰባችሁ አትደነቁ (1 ኛ ጴጥ 4.12)።

ቁልፍ መርሆች

Made with FlippingBook - Online magazine maker